ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ Continue reading

Posted in አዲስ ጽሑፎች | 13 Comments

አምስት:- ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ፤ ነገረኛነትን እንዴት እንገራዋለን?

 መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2005

ሳይንሳዊ ውይይትም ወይም ክርክር የሚመራው በሕገ-ኀልዮት ወይም በእንግሊዝኛ ‹‹ሎጂክ›› በሚባለው የአስተሳሰብ መመሪያ ነው፤ ይህንን አዚህ ለመዘርዘር ከባድ ነው፤ ግን ሁለት መሠረታዊ ቁም-ነገሮችን ማንሣት እንችላለን፤ አንደኛው የሕገ-ኀልዮት መንገድ ከዝርዝር ተነሥቶ ወደማጠቃለል የሚሄድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ Continue reading

Posted in አፈናና ከአፈና መውጣት | 7 Comments

የአቶ አስገደ ልጆች ምን ወንጀል ሠሩ? (አሕለፎምና የማነ አስገደ)

መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2005

አቶ አስገደ ከቀደሙት የወያኔ ታጋዮች አንዱ ነው፤ ወያኔ ለሥልጣን እስከበቃበትና ከዚያም አልፎ አባል ሆኖ ቆይቶአል፤ በኋላ ግን የተመለከተውን አሠራርና አካሄድ እየተመለከተ ወያኔ ዱሮ የነበረውን ዓላማ በሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ከሚደረገው ጋር ሲያነጻጽር መነሻውን እየሳተ መሆኑን በመገንዘቡ የወያኔን አሠራር በቁጭት መተቸትና መንቀፍ ጀመረ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፎችንም ደረሰ፤ አጫጭር ጽሑፎችም በጋዜጦችና በመጽሔቶች ላይ ጻፈ፤ ከጓደኞቹ ከቀድሞ የወያኔ አባሎች ጋር በመሆን አሬና የሚባል ተቀናቃኝ ፖሊቲካ ፓርቲ አባል ሆነ፤ ይህ ሁሉ እንደሰውም፣ እንደዜጋም Continue reading

Posted in አዲስ ጽሑፎች | 1 Comment

አራት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2005

 እንደሚመስለኝ ከነፍጠኛነት ይልቅ ነገረኛነት ጥሩ የዴሞክራሲ መሠረት ሊሆን ይችላል፤ በእርግጥ ነገረኛነት ለኢትዮጵያውያን የባህል መሠረት አለው ቢባልም በነፍጠኛነት ስር እየታሸ ነው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ከነፍጠኛነት ጫና ስር ሲያመልጡና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመደራጀት ሲሞክሩ ሁሌም ነገረኛነት ያይላል፤ በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያውያን ማኅበሮች መሀከል ሕግንና ሥርዓትን ተከትሎ የተዋጣለት ማኅበር ብርቅ ነው፤ አብዛኛዎቹ እየተነታረኩ ሲከፋፈሉና ሲዳከሙ የሚታዩ ናቸው፤ የችግሩ መነሻም ሁልጊዜም ሥልጣን፣ ገንዘብና ዝና ናቸው፤ Continue reading

Posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት | 12 Comments

ሦስት:- ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

እስካሁን ድረስ ያሳየነው ችሎታ የማጥፋት ወይም የማክሸፍ እንጂ አዲስ ነገርን ወይም አዲስ ሥርዓትን የመፍጠር አይደለም፤ በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ቢያንስ ሦስት የአስተዳደር ሀሳቦች መቅረባቸውን አውቃለሁ፤ አንዱ በአቶ ሀዲስ አለማየሁ፤ ሁለተኛው በኤንጂኒር-የሕግ ባለሙያ ደመቀ መታፈሪያ፣ ሦስተኛው የኔ ናቸው፤ አእምሮአቸውና ልባቸው በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጦር ተቀስፎ የተያዘባቸው ወጣቶች ሌላ ሀሳብን የማይሰሙበት ጊዜ ነበር፤ ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ጥራዝ-ነጠቅነት ብቻ የሁሉም ዓይነት የእውቀት ምንጭ ነው ብለው በጭፍን የሚያምኑ ወጣቶች በተለይም ከኢትዮጵያዊ የፈለቀ ሀሳብን ለማጥላላት ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን አይቆጥቡም ነበር፤ የሌኒን የጡት ልጆች እርስበርሳቸው ተፋጁና ያሸነፉት ዛሬም ከፋፍለው ይገዙናል፤ የት እንደሚያደርሱን ገና አላወቅንም። Continue reading

Posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት | 12 Comments

ሁለት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

  ልክ ወያኔ/ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን መገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ለአንድ የወያኔ ዓላማ ብቻ እንዲውል እንዳደረገው ኢሳትም የኢትዮጵያን ሕዝብ ለአንድ ቡድን ዓላማ ተገዢ ለማድረግ የታሰበ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፤ እስቲ ማስረጃ ቁጠሩ ሲባሉ ከስሜትና ከጥርጣሬ በቀር ምንም ተጨባጭ ነገር አይወጣቸውም፤ የተለያዩ ቡድኖች፣ በትጥቅ ትግል ውስጥ ነን ከሚሉ ጀምሮ በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል ተወስነናል የሚሉና በተገኘው በማናቸውም መንገድ ወያኔ/ኢሕአዴግን እንታገላለን የሚሉ ሁሉ በኢሳት መድረክ እንዳገኙ ይታያል፤ ኢሳት የራሱ የፖሊቲካ እምነት የለውም፤ ወይም ሁሉንም የፖሊቲካ እምነቶች ይደግፋል ማለት ይቻል እንደሆነ አላውቅም፤ ዝም ብሎ እምነት የሌለው መድረክ ነው እንዳይባል ወያኔን ተቃዋሚነቱ ጎልቶ የወጣ ነው፤ ኢሳት የጸዳ የዴሞክራሲ መድረክ ነው ከተባለ ጸረ-ዴሞክራሲ አቅዋም ያላቸውን፣ ወያኔንም ጨምሮ ማስተናገድ የሚኖርበት ይመስለኛል፤ ይህ ግን ጎልቶ እየታየ አይደለም።

ዋናው የዴሞክራሲ ችግር ዴሞክራሲ መሆኑ የታወቀ ነው፤ ዋናው የነጻነት ችግር ነጻነት ነው፤ ዴሞክራሲንና ነጻነትን አልፈልግም የሚል ሰው የለም፤ በቅርቡ ከወጣው የመርስዔ ኀዘን ትዝታዬ የሚል መጽሐፍ ውስጥ አንድ እንቊ የሆነ ነገር አገኘሁ፤ እንደተጻፈ ልጥቀሰው፡-

በአእላፍ ሰገድ ኢያሱ ዘመን፣ በ1672 ዓ.ም. ጥቅምት 10 ቀን የሃይማኖት ጉባኤ ቆሞ ነበርና የቅብዓቶች አፈ ጉባኤ አባ አካለ ክርስቶስና የተዋሕዶዎች አፈ ጉባኤ አባ ኒቆላዎስ በየበኩላቸው ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በንጉሡ ፊት በብዙ ተከራከሩ፡፡ በክርክሩም ላይ አባ አካለ ክርስቶስ ተረትቶ ጳጳሱና እጨጌው አወገዙት፡፡ ንጉሡ አእላፍ ሰገድ ዮሐንስም የተዋሕዶዎችን መርታት የቅብዓቶችን መረታት አይተው ‹‹ከበረ ሥጋ በተዋሕዶ›› ተብሎ ዐዋጅ እንዲነገር አደረጉ፡፡ እርሳቸው ራሳቸው ግን የግል እምነታቸውን ሲገልጡ ‹‹እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ›› ብለው ተናገሩ ይባላል፡፡

አእላፍ ሰገድ ኢያሱ ከሦስት መቶ ሠላሳ ዓመታት በፊት ሦስት ቁም-ነገሮችን ያስተማረናል፤ አንደኛ ፍትሕ-ርትዕ ከሥልጣን ነጻ መሆኑን የሁለት ወገኖችን ክርክር አዳምጦ፣ የጳጳሱንና የእጨጌውን በውግዘት የተገለጸ ውሳኔ ተቀበለ፤ ሁለተኛ የግል እምነት ከዳኝነት ነጻ መሆኑን ሲያሳይ አሸናፊው ተዋሕዶ መሆኑን አወጀ፤ ሦስተኛ ሃይማኖት የግል መሆኑን ለማሳየት ‹‹እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ፤›› በማለት የራሱን እምነት አሳወቀ፤ እነዚህ ሁሉ ቁም-ነገሮች ከሽፈው ዛሬ፣ በሚያዝያ 2005 ዓ.ም. ከሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመታት በኋላ ከባድ ችግሮቻችን ሆነው ለተዋሕዶውም ለእስላሙም ተደንቅረውብናል! ይህ ባለህበት ሂድ! አይደለም፤ ቀኝ-ኋላ ዙር! ነው።

ከላይ ዋናው የዴሞክራሲ ቸግር ዴሞክራሲ፣ ዋናው የነጻነት ችግር ነጻነት መሆኑን ገልጬ ነበር፤ ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት በአጼ አእላፍ ሰገድ ኢያሱ ዘመን የተወሰነም ቢሆን የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትና ነጻነት በመኖሩ በአደባባይ በሙሉ ነጻነት ክርክር ተደርጎ አሸናፊና ተሸናፊ በይፋ ተለዩ፤ ዛሬ ግን ያንን ያህል የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትና ነጻነት ስለሌለ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቃለች፤ የኢትዮጵያ እስልምናም የመሰንጠቅ አደጋ እያንዣበበበት በመሆኑ እንዳይሰነጠቅ አጥብቆ እየታገለ ነው።

ከዴሞክራሲና ከነጻነት የሚወለደው ችግር በውይይትና በክርክር፣ በሕጋዊ ሥርዓትና በሕግ ልዕልና ይፈታል፤ በአምባ-ገነን አገዛዝ ያለው አፈና ነው፤ ነገር ግን ዴሞክራሲንና ነጻነትን የሚያፍኑ አምባ-ገነኖችና ሎሌዎቻቸው ሁሉ አፈናቸውን የሚያከናውኑት በዴሞክራሲና በነጻነት ስም ነው፤ በደቡብ አፍሪካ አፓርቴይድ መሠረት የነበረው ለነጮቹና ለጥቁሮቹ ለየብቻ ዴሞክራሲና ነጻነት ይበጃል በሚል ነበር፤ ማነው ይበጃል ብሎ የሚወስነው? ሲባል መልሱ ነጮቹ ናቸው ነው፤ ነጮቹ በዴሞክራሲና በነጻነት ለነጮች ብቻ ሳይሆን ለጥቁሮችም ይወስናሉ! ኢትዮጵያም ውስጥ እነአሜሪካ ባርከው የተቀበሉት ክልል-በዘር ከተመሠረተ ሃያ ዓመታት አለፉ፤ ውጤቱ እያቆጠቆጠ ነው፤ ዴሞክራሲንና ነጻነትን እየደፈጠጠ ነው፤ ኢትዮጵያም እየደበዘዘች ነው፤ ከዚህ የአንድ አገር ውርደት የሚጠቀሙት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው፤ እነዚህም ሰዎች ቢሆኑ ለሢሶ ዕድሜያቸው አንኳን አይጠቀሙም፤ ለልጆች የሚተላለፍ ጥቅምም አይኖራቸውም፤ ከኢትዮጵያ ውጭ እንደልብ ተንደላቅቀው የሚኖሩበት አገርም መኖሩ ያጠራጥራል፤ ዛሬ እየተጠቀሙ እንዳሉት ነገም እንጠቀማለን ብለው ማሰባቸው ቂልነት ነው፤ ነገ ራሱን የቻለ ጣጣ ይዞ ይመጣል።

Posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት | 8 Comments

አንድ ፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

በአለፉት ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ እንደኢሳት (የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ) ያለ ኃይል የትኛውንም የኢትዮጵያ አገዛዝ አጋጥሞት አያውቅም፤ በመሠረቱ የኢሳት መሣሪያነት ከባህል ውጭ ቢሆንም የባህል ይዘት አለበት፤ ይህንን ወደኋላ አመለክታለሁ፤ ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ታሪክ በመሠረቱ ሁሌም በኃይል ላይ ቆሞ በኃይል የሚሽከረከር ነው፤ Continue reading

Posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት | 11 Comments