መጨካከን አይበጀንም!

መጨካከን አይበጀንም!

ሐምሌ2004

1983 ዓ.ም.

ጥላቻ ተዘርቶ ጥላቻ በቀለ፤

ልብ መግል ይዞ መንፈስ ተበከለ!

ሰው መሆን ምንድን ነው! እንዲህ ከቀለለ!

ጥላቻ — ተዘራ– ተዘራ– ተዘራ፣ በቀለ፣ አበበ፣ አፈራ፣ አስፈራ!

 

2004 ዓ.ም.

ጥላቻ ጎመራ፤

ዘር ሆነ ለሌላ ጥላቻ፤ ነጋሪት ተመታ ለስክስታ፤ ነፍስ ስትንገላታ!

ጊዜ ይሄዳል፤ ጊዜ ይመጣል፤ በጥላቻ ጥላሸት እያስረጀ ሲያሸብት!

በጥላቻ መግል ሲጨማለቅ ሲረበሽ! ሲጨነቅ! መማርን ሳያውቅ፤ መማርን ሳያውቅ፤

ጥላቻን እያስረገዙ በቀልን እያስወለዱ፣ እየተመረዘ ትውልዱ፣ ቁልቁለቱን ሲወርዱ!

ሰው ሲሰቃይ እልል! በሉ፤ ፎክሩ-ሸልሉ! እግዜር ያያል ይህን ሁሉ! በተራችሁ ሲጠራችሁ ምን ልትሉ!

ይመጣል እንግዳ፣ ዱብ-ዕዳ! ዘመድ አይል ባዳ፣ እየቀሰፈ በመደዳ!

ርኅራኄ ዘሩ ጠፋ! ዲያብሎስ ተንሰራፋ! ዓየሩ በክፋት ከረፋ!

ኧረ ተመለሱ፤ እንመለስ፤ ቢጠጋን ቅዱስ መንፈስ!

 

ለኃጥአን የመጣ መዓት ነው ይተርፋል ለጻድቃን፣ አምላክ፣ ይቅር ባንልም ይቅር በለን!

ይቅር ማለትን እስክንማር!

   

 

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች and tagged . Bookmark the permalink.

One Response to መጨካከን አይበጀንም!

  1. Pingback: መጨካከን አይበጀንም! « Amsalutamirat's Blog

Comments are closed.