ሰሞኑን …

ሰሞኑን በእስላሞችና በአገዛዙ መሀከል ያለው ግብግብ አልገባኝም፤ ሊገባኝም አይችልም፤ እስላሞቹ ሃይማኖታቸውን በፈቀዱት መንገድ ለማምለክ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ምንም አይጠረጠርም፤ ታዲያ እስላሞቹ ምርጫችንን በየመስጊዳችን እናደርጋለን ሰሉ በግድ በቀበሌ ውስጥ ምረጡ ማለት ከምን የተገኘ ሥልጣን ነው፤ ያላጥርጥር ከሕገ መንግሥቱ አይደለም፤ ለምንድን ነው ባለሥልጣኖቹ በጡንቻ እየተማመኑ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚሉት! ይህ ግብግብ መቼ ይቆማል? የምን ያህል ሰው ሕይወት ይበላል? ምን ያህል ሀብት ያወድማል? ማንን ይጠቅማል? ግብግቡ ከቀጠለ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ ይሆናል፤ በጊዜ የእርምት እርምጃ መውሰድ ግዴታ ይመስለኛል፡፡

https://www.facebook.com/mesfin.woldemariam.5/posts/232920660169541

Advertisements
Aside | This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች and tagged , . Bookmark the permalink.