በአለፉት ሃያ አንድ የወያኔ አገዛዝ ዓመታት ብዙ ተብሏል፤ ብዙም ተደርጓል፤ አሁን በአቡነ ጴጥሮስና በአጼ ምኒልክ ሐውልት ላይ የተሰነዘረው ጥቃት ግን በዓይነቱም በድፍረተም በጣም የተለየ ነው፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደሌለችና እንዳልነበረች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚባሉ ዜጎችም ዋጋ የማያውቁና ዋጋ የሌላቸው መሆናቸውን ማረጋገጫ ነው፤ የእነዚህን ሁለት ታላላቅ መሪዎች ሐውልት ማስጠቃት የከፈሉትን መስዋእትነት መደምሰስ ነው፤ የዚህ ትውልድ ታሪክ የሚሆነው የሐውልቶቹ መኖር ነው? ወይስ የሐውልቶቹ መደምሰስ?

https://www.facebook.com/mesfin.woldemariam.5

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

3 Responses to

 1. Mekonnen Amare says:

  ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም ደፋርና ያመኑበትን በአደባባይ የሚገልፁ independent ምሁር መሆናቸውን አውቃለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት የዘወትር አድናቂያቸው ሆኛለሁ (ስንት ሆዳም ምሁር በበዛበት አገር ማለቴ ነው)
  ሰሞኑን ዳንኤል ክብረት በመጽሃፋቸው ላይ ለሰጠው ሂስ ፕሮፌሰሩ የጻፉት ምላሽ ግን አስደንግጦኛል፡፡ ፕሮፌሰሩን የማውቃቸው ጠመንጃንና ጉልበትን አጥብቀው ሲቃወሙና የሃሳብ ሙግት የበላይነትን ሲያቀነቅኑ ነው፡፡ ዳንኤል ክብረት ለሰጠው ሂስ የፕሮፌሰሩ ምላሽ ተራ ስድብ እንጂ ሃሳብን በሃሳብ መሞገት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ በነገራችን ላይ እንዳለመታደል ሆኖ በባህላችን ሂስን አምርረን እንጠላለን፡፡ ጀብደኛው ደራሲ አቤ ጉበኛ በየድርሰቱ መግቢያ “ ለስራ ፈት ተቺዎቼ ሆይ!” የምትል አንቀጽ ያስገባ ነበር፡፡ ይህ ሂስ ላይ ያለን ‘የከሸፈ’ የባህል ዉርስን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማርያም ብዙ መንግስታትን አይተዋል፡፡ የንጉሱን መንግስት፤ የደርጉን አገዛዝ፤ እንዲሁም አሁን የታጋዩን መንግስት አይተዋል፤ ምናልባትም አሁን ንጭንጭና ስድብ እያበዙ ያሉት አራተኛው ማለትም መለኮታዊው መንግስት ስለቀራቸውም ይሆናል።

 2. rasekebed says:

  ፕሮፌሰር በዕውነት እርሶ የኢትዬጽያ አድባር ኖት አሁን አሁን ወጣቶች በሙሉ ከልብ እርሶን የሚሉትን መስማት ጀምረዋል ይሀሄን ስል ምን ማለት ፈልጌ መሰሎት ያው የወያኔ ስረዓት እንደርሶ በእድሜ የገፉ በዕውቀት የካበተ ልምድ ያላቸውን አባቶቻችንን የህዝብ መገናኛ በመጠቀም በጠላትነት ፣ በነፍጠኝነት ብቻ ወያኔ ስድቡ ብዙ ነው ሌላም ሌላም ከያለበት ካድሬው ሰለሚወረውር ወጣቱም እውነትን ከመፈለገግና ከማጥራት ይልቅ ወያኔ የሚነዛው ፕሮፓጋንዳ በፍረሃት ቆፈን ተሸብቦ የከረመበት ሁኔታ ነበር አሁን ሁኔታው ተለውጧል ትውልዱ ደፋር ሆኗል በዚህም እናንተን የሚያዳምጠው ወጣት በዝቷል ሰስዚህ እኔ ለዕርሶ እረጅም እድሜ ፈጣሪ እንዲያድሎት እመኛለው የሚያራምዱት የፀዳ ሰላማዊ ትግል በጣም ይማርከኛል ኢትዬጽያቸን በዚህ መንገድ በአጭር ጊዜ ለውጥ እንደምታመጣ አምናለሁ ለሁላችንም ወያኔንም ጨምሮ የጴጥሮሳዊነትን መንፈስ ያድለን ፡፡ ሌላው በሀገር ውስጥ ገዢው መንግስትን የምትቃወሙ ተቋሚዎች ለ45 ዓመት ልብ ያላላችሁት ሁልጊዜ ከህዝብ ተነጥላችሁ ፖለቲካን ለመጫወት የምታደርጉት ሙከራ የትም አያደርሳችሁም የህዝብ ድጋፍ የሌለው ተቋውሞ የትም አይደርስም ለእኔ አገዛዙን ጉድለቱን በተለያዩ መንገዶች ገበናውን እየገለፃቹ የህዝብ ድጋፍን መሸመት ይቻላል ለምሳሌ የቅርቡን እንይ መንግስት ለ21 ዓመት ያልደፈረውን የሁለት ታላላቅ አባቶቻችን ሀውልት ውስጥ ውስጡን ሲሄድ ከርሞ ዛሬ በ21ኛው ዓመቱ ላይ በልማት ስም ሀውልቱን ወደ ማፍረስ ደረጃ ተቃርቧል ገዢው መንግስት የህዝብንም የናንተንም ልብ እየፈተነው ነበረ ታዲያ ተቋሚዎች ይሄን ህዝብን በጋራ የሚያስተሳሰር ጉዳይ ለምን አጀንዳቹ አላደረጋችሁም ነገሩ የግል ሚዲያዎችም ከናንተ በምንም አይሻሉም በዚህ ዙሪያና ሌሎች ጉዳዮች ሁሌም ግንባር ቀደሞች ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም የሁልጊዜም ግዴታቸውን እየተወጡ ነው እድሜ ይስጥልን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከመኢአድ ውጪ እስቲ ማነው የአድዋን በዓል አክብሮ የሚያውቅ ተቋዋሚች ታዲያ እንዴት ነው የህዝብ ልብ መግዛት የምትችሉት ስረዓቱን እራቁቱን እናስቀረው ካላችሁ ብዙ ጉድለቶች ያሉበት ስረዓት ስለሆነ ምንም እንኳን ብዙ መሰናክሎች እንዳለባችሁ ባውቅም ባለችው ጠባብ መንገድ ህዝብ ጋር የሚያደርሳችሁን ስራ መስራት ትችላላችሁ ለምሳሌ በቤቶች ግንባታና እደላ ዙሪያ ያለው ችግር ፣ የንሮ ውድነቱ ፣ በየመንግስት መስሪያ ቤት ዜጎች ወያኔ ካልሆኑ ስራ አለማግኘት ፣ በየመንግስት መስሪየ ቤት የሚሰሩ ሰራተኞች በግዴታ 1ለ5 መጠርነፍ ፣ የመለሰን እራዕይ ዕውን እናደርጋለን በሚል ግልገል ካድሬዎች ሰራተኛውን ከጉሮሮው ላይ እየነጠቁ በግድ ለአባይ ግድብ እንዲያዋጣ በፋይናንስ ሹሙ በኩል ከፔሮል ቆርጦ መውሰድ አረ ብዙ ብዙ ስለወያኔ ድክመት ማውራት ይቻላል እናንተ ብቻ ከመከፋፈልና በየመንደሩ ማላዘን ትታችሁ የተግባር ሰዎች ሁኑና ወያኔም እናንተም ያላችሁን አማራጭ ገበያ ይዛችሁ ውጡ እኛ ለውጥ የምንፈልግ ወጣት ዜጎች አወዳድረን እንገዛለን እባካችሁ ፍጠኑ……….

 3. ነጻነት አሸናፊ says:

  ምን ይደረግ?????????? አደባባይ ብንወጣ ወንበዴዎቹን ደምስሰን ሀገር እንታደጋለን ወይ???????….. ወያኔ በዘር የከፋፈለውን ኢትዬጽያዊ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ እርስ በርስ ከመጣላት ማን ያግዳል???……. ችግሩ ወንበዴዎቹን መደምሰስ ላይ አይደለም……..ከዚያስ ምን ይከተላል የሚለው ነው…….???

Comments are closed.