ፕሮፌሰሩ ከፍርድ ውሳኔ በፊት የሰጡት ብይን

…ጊዜው ምናልባትም ከዛሬ 33 እና 34 ዓመት በፊት ይሆናል። በአምባገነኑ የደርግ ሥርዓት ወቅት። ታዲያ በእዚያን ወቅት አምባገነኑ መንግሥቱ ኃይለማርያም የሀገራችንን ዜጎች በኢህአፓ ስም ሲጨፈጭፉ አጠገባቸው ከሚገኙት አማካሪዎች ለአንዱ መራር ጥያቄ ያቀርባሉ። እኚህ ሰው በአንድ ወቅት የአንድነት ፓርቲ አባል ሆነው መሃል ላይ በሥልጣን ጥማታቸው ምክንያት ፓርቲውን መልቀቃቸው የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ናቸው።

እናም የሰው በላው ሥርዓት መሪ ፕሮፌሰሩን «እያስቸገሩን ነው። ምን እናድርጋቸው?» ሲሉ ይጠይቋቸዋል፡፡ የዛሬው ዴሞክራት መሳይ ፕሮፌሰርም ቀልጠፍ ይሉና «ታዲያ እኛን ምን አድርጉ ትሉናላችሁ፣ መሳሪያው ያለው እናንተው ጋ አይደለም እንዴ?» የሚል ጥያቄን በጥያቄ የሚመልስ ምክር አይሉት ምላሽ እንደሰጡ በቅርበት የሚያውቋቸው ግለሰቦች ይናገራሉ፡፡ እንግዲህ ይህ አባባላቸው «ሌባ ተይዞ ዱላ አይጠየቅም» የሚለውን ይትብሃል የሚያመላክት ብቻ ሳይሆን፣ ‘መሳሪያ የታጠቃችሁት ለጌጥ ነው እንዴ?’ በሚል አንድምታ በደንብ ጨፍጭፏቸው የሚዘገንን ምክርን ያዘለ ነው፡፡

እርግጥ ይህ የፕሮፌሰሩ በገዛ ወገን ላይ የተሰጠ ጭካኔ የተሞላበት ምክር ሰቅጣጭ ነው፡፡ ገዳይን ከመኮነን ይልቅ የተኩሰህ ግደል አማካሪነት ምንኛ ሰብአዊነት የጐደለው ተግባር እንደሆነም ልብ ማለት ይገባል፡፡ እኚህ ፕሮፌሰር በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ላይ ሆነውም ይህን መሰሉ ጥያቄ እንዲቀርብላቸው ሳይመኙ የሚቀሩ አይመስለኝም፡፡

ይህን አባዜያቸውን ደግሞ በምርጫ 97 ወቅት ገቢራዊ አድርገውታል ሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ በሞከሩበት ወቅት። እርሳቸው ሥልጣን ለማግኘት ካላቸው የጋለ ፍላጎት በመነሳትም የአንድነት ፓርቲ መፍትሔ አፈላላጊ ምንትስ እየተባባሉ በየጎዳናው የሽማግሌ ወገብ በማይችለው መልኩ በከዘራ ተለጣልጠዋል፤ ተዠላልጠዋል። ድንጋይ አንስተውም ተፈረካክሰዋል።

ውድ አንባቢዎቼ እነዚህን ዕውነታዎች ለመንደርደሪያነት ያህል ያወጋኋቸሁ የሰውዬውን ማንነት ይበልጥ እንድትገነዘቡ ብቻ አይደለም። ይልቁንም ቋሚ አምደኛ ሆነው በሚሰሩበት በአዲስ ታይምስ መጽሔት የወርሐ ታኅሣሥ 2005 ዓ.ም ዕትም ላይ «ሃይማኖት እና ሕገ-መንግሥት» በማለት የከተቡት የተለመደ «የእናናውጠው» ጽሑፍ ቀደም ሲል ከጠቀስኩላችሁ ከነባሩ ማንነታቸው ጋር ስለተመሳሰለብኝ ነው፡፡

እርግጥ የሰውየው ማንነታዊ ስብዕና ከትምህርት ደረጃቸው ጋር ሲነፃፀር እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ፕሮፌሰሩ ለሀገር እና ለሕዝብ የሚበጁ ጥናት እና ምርምር ማድረግ ሲገባቸው ከዓፄው ሥርዓት ጀምሮ ለሥልጣን እየቋመጡ፣ ከፍ ሲልም «የግደለውን» ምክር እየሰጡ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያን ለመበታተን በሚደረገው የጠላቶቻችን ድብቅ ሴራ አካል ሆነው ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ፡፡

እኚህ ፕሮፌሰር በአንድ ወቅት ሕገ-መንግሥቱን «ሕገ-አራዊት» እያሉ ሲጠሩ እንደነበር ከማናችንም የተሰወረ ጉዳይ አይደለም። ዛሬ ግን ደርሰው የሕገ-መንግሥቱ ተቆርቋሪ መሆናቸው በጥቂቱም ቢሆን ያስፈልጋል። ግና ትናንት ሕዝቦች በፈቃዳቸው ተስማምተው እና ተፈቃቅደው ያፀደቁትን ሕገ-መንግሥት፤ የሰዎች ሳይሆን የአራዊት ሕግ ነው ብለው ሲያበቁ፣ ይህን ‘ኢትዮጵያውያን በህገ-አራዊት እየተዳደሩ ናቸው’ የሚል ፈሊጣዊ ፍልስፍናቸውን በውል ለሚረዳ ማንኛውም ሰው የግለሰቡን የተሳሳተ ግምት ለመረዳት አይከብደውም፡፡

ታዲያ ትናንት ከስያሜው ጋር አንዳችም ግንኙነት በሌለውና «ፍትሕ» በተሰኘ ጋዜጣ ላይ የሥልጣን ጥማቸውን ለመወጣት ሲፅፉ የነበሩት ፕሮፌሰሩ፤ ዛሬ ደግሞ «ዳግማዊ ፍትሐቸው» በሆነው«አዲስ ታይምስ»ያልነካኩት ጉዳይ የለም። ጥቂቶቹን ብናነሳ እንኳን «የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ አራት ጠቅላይ ሚኒስትር ተሹመዋል፣ የፓትርያርኩ ሞት ግን ገና ምንዛሪ አልተገኘለትም» በሚሉ ርዕሶች ለመሞነጫጨር ሞክረዋል። ጽሑፋቸው በጥቅሉ እንደ ድሪቶ የተተበተበ እንዲሁም እንደ ተፋሰስ መያዣና መጨበጫ የሌለው ነውና።

መቼም ነገሩ «ካረጁ አይበጁ» ነውና አዛውንቱ ፖለቲከኛ ከአቶ መለስ በኋላ «አራት ጠቅላይ ሚኒስትር» ሀገራችን ውስጥ እንደምን እንደተሾሙ የሚያውቁት እርሳቸውና ሥልጣን አምላኪ ዛራቸው ብቻ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ያሉት አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሳለ እርሳቸው ሦስት ተጨማሪ «ጠቅላይ ሚኒስትሮችን» መሰየማቸው ለማንም ግልጽ አይደለም።

እያንዳንዷን የመንግሥት የሥልጣን አወቃቀርን ለሥልጣን ካላቸው ጉጉት በመነጨ በአንክሮ የሚከታተሉት እኚህ ሰውዬ በጠቅላይ ሚኒስትር፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሚሉትን የሥልጣን እርከኖችን አያውቋቸውም ማለት አይቻልም።

ያም ሆነ ይህ ግን፤ እርሳቸው ዕውነታውን አወቁትም አላወቀት ፕሮፌሰሩ ያነሱትን ትችት ከሕገ-መንግሥቱ አኳያ መመርመር ተገቢ ነው፡፡ በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 75 ላይ ስለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተግባር እና ኃላፊነት አስመልክቶ የተደነገገውን እንመልከት፡፡ በእዚሁ አንቀጽ ስር ባለው ንዑስ አንቀፅ አንድ ላይ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ሀ) «በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል» (ለ) «ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶት ይሰራል» ሲል፣ በንዑስ አንቀጽ ሁለት ላይ ደግሞ «ም/ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል» ይላል፡፡

በእዚሁ መሠረት የአቶ መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ህልፈተ- ሕይወትን ተከትሎ በሕገ- መንግሥቱ መሰረት የተመረጡት ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንጂ፣ ፕሮፌሰሩ ያከሏቸው ሦስት ተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ምንጩ አሉታዊ አስተሳሰባቸው ብቻ ነው፡፡

ከፕሮፌሰሩ ከሃቅ ያፈነገጠ አባባል የምንገገዘበው ነገር ቢኖር አቶ መለስ ዜናዊ የተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ብቻ ነው፡፡ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምክትል ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው፡፡ እናም ፕሮፌሰሩ ያነሱት ሃሳብ መንግሥት ካከናወነው ሹመት ጋር በፍፁም የማይገናኝ አራምባና ቆቦ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

እናም ፕሮፌሰሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን እንጂ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ እንዲሁም የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዘርፎች አስተባባሪ ሆነው የተሾሙት ባለስልጣናት አለመሆናቸው ልብ ማለት ይገባቸዋል ባይ ነኝ፡፡

ለነገሩ የእርሳቸው ነገር «ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል» እንደሚባለው ሆኖ ነው መሰል መንግሥት ያከናወነው የሥልጣን ሹመት ግልፅ ሆኖ ሳለ፤ አውቀው እንዳላወቁ መስለው ሌላውን ለማደናገር የሚያደርጉት የተለመደ ሁከት ጠቀስ አስተሳሰብ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ሰውየው በእዚሁ ጽሑፋቸው አክለውም «የፓርትርያርኩን ሕልፈተ- ሕይወት ተከትሎ የተደረገ የሥልጣን ድልድል የለም ብለዋል፡፡

ልብ በሉ! በእርሳቸው የተለመደ ጽሑፍ፤ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብቷል ማለታቸው ነው። መቼም ሽሙጥ መናገራቸው ሳይሆን አይቀርም። በሃይማኖታዊ ሹመት ውስጥ መንግሥት ጣልቃ እንደሚገባ አስመስለው የጻፉት ከአሉባልታ ውጪ አንድም እውነት የለውም። ለነገሩ የአሉባልተኞች መናኸሪያ ላይ የሚጽፍ ሰው እውነት የሚባለውን ውድ እሴት እንደተላጠ የኤሌክትሪክ ሽቦ ስለሚፈራ ያሻውን ቢዘላብድ አይፈረድበትም- ለእርሱ ሁሉም ነገር ስማ በለው ነውና።

ያም ሆነ ይህ የኢፌዴሪ ሕገ- መንግሥት ሃይማኖት በመንግሥት፤ መንግሥትም በሃይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ ይደነግጋል፡፡ እየተደረገ ያለውም ይኸው ነው። እናም ፕሮፌሰሩ የአሉባልታ ምንዛሪያቸውን በእዚህ መልኩ ቢያስተካክሉት በጄ ነው፡፡

ሰውየው ከዚህ ቃርሚያ ሃሳባቸው ለጥቀው ያመሩበት ወደ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ነው-በስሚ ስሚ የለቃቀሙትን አሉባልታ በማስፋፋት። እናም «በቅድሚያ በእስላሞቹ ልጀምር» ብለው ይነሱና፣ አክለውም «የኢትዮጵያ እስላሞች ችግር ሁለት ነው፡፡ አንዱ እነርሱ እንደሚሉት አልአህባሽ የሚባለውን የእስልምና ዓይነት ተከተሉ መባላቸው ነው፡፡ ይህ ትልቅ ድፍረት ነው፡፡ ሁለተኛ የራሳችንን ካህናት እኛው በየቤተ መስጊዳችን እንመርጣለን እንጂ እንደ ፖለቲካ ካድሬዎች በየቀበሌው አንመርጥም ማለታቸው ነው» በማለት ጉዳዩን በጭፍን እሳቤ መንግሥት ላይ ለመለጠፍ ይዳዳሉ፡፡

ፕሮፌሰሩ ትናንት በዓፄውና በደርግ ሥርዓቶች የሃይማኖት ነፃነትና እኩልነት እንዲደፈጠጡ እንዳልመከሩ ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የትናንት የፀረ-ዴሞክራሲያዊነት ካባቸውን ለይስሙላ አሽቀንጥረው በመጣል ደርሰው ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቆርቋሪ መስለው እየቀረቡ ነው፡፡

ሰውየው አስቀድመው ያነሱት ነጥብ አልሀበሻ የሚለውን የእስልምና እምነትን ሙስሊሞች የግድ ተከተሉ ተብለዋል በመባላቸው አመፁ ተነስቷል የሚል ነው። አስከትለውም የእምነቱ መሪዎች በመስጊድ ምርጫ ላይ እንዳይከናወን ስለአገዱ ሙስሊሙ አመፅ ለማንሳት እንደተገደደ ያወራሉ።

እኔ እስከሚገባኝ ድረስ በመጀመሪያ ደረጃ በድፍረት እንዲህ ዓይነት ያልተረጋገጠ ነገርን ለመፃፍ ስለ እምነቱ በቂ እውቀት መያዝ የግድ ይላል፡፡ በቅድሚያ አልሀበሻ የሚለውን ቃል ከየት እንደመጣ እንመልከት፡፡ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያትቱት፤ ሼክ አብደላ ሀሪሪ በኢትዮጵያ እስልምና ፈለግ ውስጥ የጠለቀ እውቀት ከነበራቸው የሃይማኖት አባቶች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አረቦቹም እኝህን የሃይማኖት አባት በአዋቂነታቸው ያደንቋቸው ነበር፡፡

እናም አረቦቹ ሀበሻ መሆናቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት «ሼክ አብድላ አልሃበሽ» ብለው እንደጠሯቸው ታሪክ ያወሳል፡፡ እናም ቃሉም ሆነ ሃይማኖታዊ ቀኖናው አዲስ አይደለም። ለዘመናት የኢትዮጵያ ሙስሊም ሕዝብ ሲጠቀምበት የነበረ ሃይማኖታዊ ሥርዓትም ነው፡፡ ታዲያ ይህን በርካታ ሙስሊሞችን የሚያግባባ ሃይማኖት ወደ ጐን በማለት የተለያዩ ስያሜዎችን እያወጡ በገንዘብ ኃይል ከውጭ የመጣ አዲስ የሃይማኖት መስመርን የግድ መቀበል አግባብነት ያለው አሠራር ይመስለኝም፡፡

በእዚህ ሁኔታ ፕሮፌሰሩ በፍርድ ቤት የተያዘን ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ለማወክ መጣራቸው ብቻ ሳይሆን፤ በሰላም ሀገር አዋራ ማንሳት የፈለጉበት ዋነኛ ምክንያት ለእኔም ሆነ ለእዚህ ጽሑፍ አንባቢ ግልጽ ነው፡፡ ይኸውም በሀገራችን ውስጥ ያልነበረው እንደ ወሃቢያ ዓይነት የአክራሪዎች እምነት ተስፋፍቶ ሰዎች በጠራራ ፀሐይ ሲገረፉ፣ ሲሰቃዩና ሲገደሉ ማየት ነው፡፡

በመሰረቱ የዛሬ ዓመት ገደማ የተነሳው ሁከትን የማቀጣጠል ሴራ ድብቅ ፖለቲካዊ ዓላማን የሰነቁ ጥቂት አክራሪ ኃይሎች ያቀነባበሩት መሆኑ አይዘነጋም። ዓላማውም ፖለቲካዊ እንጂ ቅንጣት ታህል ሃይማኖታዊ መሰረት የለውም። እናም የራሳቸው ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎች የሚመሩትና የፖለቲካ ትርፍ ለማካበት የሚንቀሳቀሱ እፍኝ የማይሞሉ ጽንፈኛ ኃይሎች ያስነሱት እንጂ፤ ፕሮፌሰሩ እንደሚያወሩት ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የአልሀበሻ እምነትን ተከተል ስለተባለ አይደለም፡፡

ፕሮፌሰሩ ግጭት ቀስቃሾቹ «በኢትዮጵያ ከሚገኘው ሕዝበ ሙስሊም ከግማሽ በላይ ናቸው» ማለታቸው የሰውዬው ጽሑፍ ሦስተኛ ለመሆኑ ሁነኛ አስረጅ ነው፡፡ ያለምንም ማስረጃ በእዚህ ዕድሜያቸው አይናቸውን በጨው ታጥበው ይህን ለማለት መድፈራቸው፤ አንድ ተምሬያለሁ ከሚል ፊደል ቆጣሪ የሚጠበቅም አይመስለኝም። ለመሆኑ ‘የፅንፈኞቹን ቁጥር ያሰሉት በምን ቀመር ነው?’ ተብለው ቢጠየቁ እንደተለመደው ከመዘላበድ በስተቀር ምንም ለማለት አይቻላቸውም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፕሮፌሰሩ ሃይማኖትን ከሕገ-መንግሥቱ ጋር ለማላተም በማሰብ ያነሱት ነጥብ ሁላችንንም ያስደመመ ነው፡፡ በእዚህ ሃሳባቸው የተካተተው አርቲ ቡርቲ እሳቤያቸው በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 12 የተደነገገውን ከመፃረር ይነሳል፡፡

ሰውዬው እንደ አብነት የአፄዎቹን ዘመን ጠቅሰዋል፡፡ እናም እንዲህ ብለዋል፡፡… በአፄዎቹ የአገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በቤተ መንግሥት ላይ ከባድ ጫና ስታኖር ነበረች፣ ያለ ቤተክርስቲያኒቱ ሙሉ ፍቃድ መንገስ ከቶም አይታሰብም፣ እንዲሁም አብዛኛዎቹ የሀገሪቱ ሥራዎች የሚከናወኑት በሃይማኖት ሰዎች ነበር። አሁን ግን ይህን የሚሽር ሕገ-መንግሥት ፀድቋል፣ እናስ ለምን?» በማለት የራሳቸውን ውስጣዊ ስሜት ይጠይቁና ራሳቸው ይመልሳሉ፡፡

ይህ ብቻም አይደለም። «በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ዜጐች እኩልነት ለማስከበር ነው፤ ነበር፤ አሁን እንደሚታወቀው ግን ሃይማኖቶችን እየለያዩ ለማድከምና ለማስገበር ነው» በማለትም አስነብበውናል። እናም እነዚህን ተጨባጭነት የጎደላቸውን አባባሎች መመርመር ተገቢ ይመስለኛል፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ፕሮፌሰሩ ያነሱት ሃሳብ እርስ በርሱ የሚፋለስ እንጂ አንዱ የሌላኛውን ነጥብ የሚደግፍ አይደለም፡፡ እርግጥ ኢትዮጵያ በዘመነ ንጉሳውያን አገዛዝ ወቅት የነበራት መንግሥት ሃይማኖታዊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ምናልባትም ይህ አካሄድ በወቅቱ ተመራጭ ነበርም ማለት ይቻላል—ከነገስታቱ አንፃር ስናየው።

ሆኖም ይህ ሃይማኖታዊ መንግሥት በሃይማኖት ሽፋን ሀገር ለመግዛት «ስዩመ እግዚአብሔር» እያለ፣ የሌላውን ሕዝብ መብትና ነፃነት ገፈፈ እንጂ ለምስኪኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም። ምናልባት ፕሮፌሰሩ የኖሩበትን ሥርዓት ለማንቆለጳጰስ ካልፈለጉ በስተቀር በማንኛውም ጤነኛ ሰው ዕይታ ሃቁ ይኸው ነው።

ይህ ሁሉ የግፍና የሰቆቃ ዘመን ታልፎም በውድ የሕዝብ ልጆች መስዕዋትነት በተገኘው የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት ላይ «መንግሥት እና ሃይማኖት ተለያይተዋል» ተብሎ የመደንገጉን አስፈላጊት ለፕሮፌሰሩ እየመረራቸውም ቢሆን መንገሩ ተገቢ ነው። ይኸውም በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ መንግሥት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው ለማረጋገጥ ነው፡፡

የንጉሱ ዘመን አገዛዝ አንድን ሃይማኖት ተመርኩዞ ሀገርን ሲመራ ነበር፡፡ ሆኖም ይህቺ ሀገር የብዙ ሃይማኖት ባለቤት ነች፡፡ እናም አንድ መንግሥታዊ ሃይማኖትን ማስፈን ማለት የሌላውን ሕዝብ የእምነት ነፃነት መንፈግ ነው። ስለሆነም የተገነባው ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ይህንን የሕዝቦችን መብት ረገጣ የሚኮንነው ብቻ ሳይሆን አምርሮም የሚዋጋው ነው። ለእዚህም ነው ፕሮፌሰሩ በጽሑፋቸው የሚያሞካሿቸውንና “ሃማኖታዊ መንግሥት እንመሰርታለን» የሚሉ ጥቂት ተጠርጣሪ ፅንፈኞችን መንግስት ለሕግ ያቀረባቸው።

መንግሥታዊ ሃይማኖት ያላስፈለገበት አንዱ መሰረታዊ ነጥብ ደግሞ በሃይማኖቶች መካከል አድልዎ እንዳይፈጠርና በእዚህም ምክንያት የሃይማኖት ግጭት እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል ነው፡፡ በሃይማኖት ስም የሚጋጭ ኅብረተሰብ ለልማት ይነሳሳል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ለእዚህ ደግሞ የትኛውም ሃይማኖት ያለ አንዳች ልዩነት ነፃነቱና እኩልነቱ እንዲጠበቅለት ተደርጓል።

ፕሮፌሰሩ በግልፅ ባይነግሩንም ትክክለኛ ፍላጎታቸው አሁን በሀገራችን ያለውን የሃይማኖት መከባበር እና መቻቻልን ቢችሉ ለማደፍረስ መሯሯጣቸው ነው። የሃይማኖቶችን እኩልነትና ነፃነት መሸራረፍ ይገባል ብለው ለአክራሪዎች ጠበቃ የሆኑትም ለእዚሁ ነው። በማያገባቸው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ከፍርድ በፊት ብይን ለመስጠት የሚከጅላቸውም፤ የተፈጠረው ሀገራዊ የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዞ ፈጽሞ ስለማይታያቸው ነው፡፡

ግና አንድን ሃቅ ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ። እርሱም የሀገራችን የዕድገት ውጤት ምክንያታዊ ምስጢሮች ውስጥ አንዱ የሕዝባችን መቻቻል እና መከባበር መሆኑን ነው፡፡ ይህን የሀገራችንን ሕዝቦች መቻቻል እና መከባበር ለመቀልበስ ፖለቲከኞች ሃይማኖትን እንደ ሽፋን በመጠቀም አክራሪዎችን እየደገፉ የያዙት ቀለምና ወረቀት እስኪያልቅ ድረስ ያሻቸውን ቢለቀልቁም፤ያረጀ ያፈጀ እሳቤያቸውን አሜን ብሎ የሚቀበል ሕዝብ የለም። በእጅ አዙር አመፅን ለማቀጣጠል የሚደረግ ማናቸውም የቀቢፀ-ተስፋ ሙከራ ሰላም ወዳዱን ሙስሊሙን የኅብረተሰብ ክፍል ጨምሮ በሌላው እምነት ተከታይ ዜጋ ሲከሽፍ በዓይናችን በብሌኑ እየተመለከትን ስለመጣን ነው፡፡

ምንም እንኳን እነዚህን አክራሪ ኃይሎቹ የሁከት ሱሰኞች በሀገራችን በሚገኙ አንዳንድ የግል ፕሬሶችና መጽሔቶች ሕዝበ ሙስሊሙን እርስ በርሱ ለማጋጨት ያልፃፉት ነገር ባይኖርም፤ የሀገራችን ሕዝብ ጨዋና ሚዛናዊ በመሆኑ፤ በቅብብሎሽ የሚረጩትን የቅጥፈት ወሬ ከመጤፍ አልቆጠረውም።

በመጨረሻም ምክር ቤጢ ለሰውየው ማካፈሉን መረጥኩ። ፕሮፌሰር ሆይ! ቤተ-ክርስቲያን በሚስሙበት በእዚህ ዕድሜዎ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከፍርድ ውሳኔ በፊት ብይን እየሰጡ ዕውነትን ለመደፍጠጥ ባይባትሉ ምንአለበት? አበቃሁ።

Advertisements
This entry was posted in ውርጅብኝ and tagged . Bookmark the permalink.

11 Responses to ፕሮፌሰሩ ከፍርድ ውሳኔ በፊት የሰጡት ብይን

 1. Thank you for your questions and comments.
  Response to above comments: Please note that this site is not accessible in Ethiopia– which means that Professor Mesfin is unable to read/respond to all comments or questions. With respect to questions re: accusations and for those who truly seek the truth, the facts do exist in the archives of the times, and the Professor has addressed some of these questions in his book አገቱኒ፣ ተምረን ወጣን . Therefore enough information exists for those who seek it.

 2. Kassa says:

  Professor,
  With due respect, let me ask you the following: what is your intentions posting it? what do you want us to learn from this? Is there any good lesson we can learn from this? Or you just want to expose the stupidity of the writer and his government allowing him spend public resources on such useless piece. I would also say, it would be better if you add your perspective to it.

 3. Kolotemari says:

  I eagerly want to hear professor Mesfine explanation any thing he want to say about red terror and how his name is mentioned there?

 4. lila says:

  ይህ ዘአማን የተባለ የወያኔ ጅላንፎ ካድሬ (ምናልባትም ወዲ ኤሪ፤ በረከት ታንክ ግንባር እየጠራው በዚህ በዚህ ርእስ ላይ የስድብ ጽሁፍ ጻፍ እያለ የሚያዘው ሰው) በአይጋ ፎረምና የስኳር መጠቅለያ በሆነው አንሶላው አዲስ ዘመን ላይ ለፍርፋሪ መብያ ሲቀበጣጥር ይታያል። ወያኔን እድለኛ ከሚያደርጉት አጋጣሚዎች አንዱ ዘአማንን የመሳሰሉ አጋሰስ ቀባጣሪያንን ሀገሪቱ ፈልፍላ ማስረከብ መቻሏ ነው። ታንክ ግንባሩ በረከት ከሚጠላቸው ሰዎች አንዱ በሆነው ደፋርና ብርቱ ብእረኛ ተመስገን ደሳለኝም ላይ ዘአማንና አጋሰስ ጓደኞቹ የስድብ፤ የዛቻና የማስፈራሪያ ልቅምቃሚ በመሰንዘር ወያኔ በሰጣቸው የፍርፋሪ ሳህን መጠን ሲያቀረሹ ቆይተዋል። ድንቁርና ቤቱን የሰራበት ዘአማን ከዚህ በሽታ የሚገላግለው ጸበል ስለሌለ ዛሬም እነሆ ፕሮፌሰር መሥፍን ሰዎች እንዲረሸኑ ምክር ሲያቀብሉ አውቃለሁ እያለ በአንሶላው ጋዜጣ ላይ ያቀረሻል። እውቀትና እውነት ከሽፍታው ወያኔ ጋር ዓይንና ናጫ በመሆናቸው ዘአማንን የመሰለ አጋሰሶችን መሰብሰብ መቻሉ ብዙም አያስገርምም። እዚህ ላይ ዘአማንንና ቢጤዎቹን ከአጋሰስ ረድፍ መመደብ ያስፈለገው አጋሰስ በተፈጥሮው አንዴ የተመገበውን መልሶ የማያመሰኳና እንብርት የሌለው ስለሆነ እነዚህኖቹም የሰው አጋሰሶች ለሚያደርጉትና ለሚጽፉትነገር መላልሰው የሚመለከቱበት ኅሊና የሌላቸው፤ ውሸት ሰለቸኝና በቃኝ የማይሉ የአእምሮ እምብርት ያልፈጠረባቸው ስለሆኑ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል።
  ስለዚህም ዘአማን በአንሶላ ጋዜጣው ላይ ያወጣው ጽሁፍ ፕሬፌሰር መሥፍንን ለመስደብና ለማንኳሰስ ካልሆነ በስተቀር የጽሁፉን ጭብጥ ተአማኒ ለማድረግ አንድም አስረጂ ያልቀረበት ተራ ዲስኩር ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም። ወያኔ ሀገር የሚመራው በህገ መንግስት ሳይሆን በህገ አራዊት የመሆኑን የአደባባይ ምስጢር ዘአማን አጋሰሱ ሊክድ ይፈልጋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ እያለ የውሸት ጓዳው የወያኔው ቲቪ በአደባባይ እየተናገረና ለሶስት ሰዎች እየሰጠ ሳለ ሌላውን ይህንን ሲሞግት የሚዋሽ አድርጎ ስም አጥፊና ህገ መንግስቱን ጣሽ አድርጎ ለማቅረብ ይመኛል። አይ ዘአማን አጋሰሱ! ያልታደልክ ለማዳ እንስሳ!
  ናቡከደነጾር በአንድ ወቅት እንደሆነው፤ አንተም ወያኔ የሚጥልልህን የሀሰት ገለባ ከመብላት ወጥተህ ሰው እንድትሆን አምላክ ኅሊና ይሰጥህ ዘንድ እመኝልሃለሁ። ታንክ ግንባሩ በረከት እንደሆነ ወይ ከጎንደር፤ ወይ ከኤርትራ፤ ወይ ከአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ከአንዱም መሆን ያልቻለና ሁሉም ያልተቀበሉት ስለሆነ የዲፕሬሽን ተጠቂ ስለሆነ እሱን ካለሞት በስተቀር ወደሰዋዊ ኅሊና የሚመልሰው መድኃኒት የለውምና ከጥፋት መንገድ መቼም አይመለስም። ይብላኝላቱ ለሚስቱ ያን ታንክ ግንባሩን በቲቪ ሳየው ልጆቼ በፍርሃት እንዳይበረግጉ ቲቪውን ቶሎ አጥፍቼ አገላገላለሁ። ዘአማን አጋሰስ አገልጋዩን ደግሞ ማን ከዚያ አንሶላ ጋዜጣ ላይ ይገላግለን?

 5. elias says:

  አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያዉ ከስጋ መጠቅለያነት ወደ ሸሆና መጠቅለያነት ወረደ! ያሳዝናል!

 6. ነፃነት አሸናፊ says:

  የፅሁፉ አላማ ምን ይሆን?? ብሎ የሚጠይቅ ሞኝ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ወቸው ጉድ!! አለ የሀገሬ ሰው፡፡ እናንተዬ ለካ አለማወቅ ያሰክራል….. በርግጥ መጨረሻው ሲመጣ ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ ብዙ ነገር ይባላል ይደረጋል፡፡ ወያኔም የመጨረሻው መጨረሻ ላይ በመሆኑ ሆድ አምላኩ የሆኑ በአለማወቅ የሰከሩ ካድሬዎቹ በድንጋጤ የሚሰሩት ስራ ነው፡፡ ገና ሌላም አስገራሚ ነገር እናያለን፡፡ ከፅሁፉ የገረመኝን ግን ላካፍል፡፡ የዛሬ 33 34 አመት በፊት ይሆናል የምትለው መግቢያ ሳቅ ታጭራለች፡፡ ፀሀፊው በዚያን ግዜ የነበረ የዐይን እማኝ ነው ማለት ነው.. ወይስ (ጋሼ መስፍንን እንደሚከሰው ሁሉ) በስሚ ስሚ የሰማውን ነው የሚነግረን…… ወገኖቼ አንዘን ሳይጨልም አይነጋም፡፡ ኢትዮጵያዬ ብዙ የጨለማ ዘመናት አሳልፋለች፡፡ ንጋቱን ሁሉን አድራጊ የሆነው ጌታ በቶሎ ያምጣልን፡፡ እድሜና ጤና ለጋሼ መስፍን ሰላም ፍቅር ጤና አንድነት ስኬት ለምወዳችሁ ወገኖቼ የምወደው አምላኬ ይስጥልኝ ይስጠን፡፡ አሜን!!!
  ጤና ይስጥልኝ፡፡

 7. Tegbaru Misikr says:

  A dirty comment from a dirty hooligan who hardly completed his elementary studies. We know what is going on in this country. No amount of pile of lies can cover up the truth except exposes the shabby character of such persons.

 8. Eshetu Legesse! says:

  ምን አይነት መዘላበድ ነው፡፡ ጹሁፉን ከአውዱ አውጥቶ የራስን ትርጉም በመስጠት ጸሀፊውን በማሳጣት ትርፍ ለማግኘት ሞክሩል አልተሳካለትም እንጂ፡፡ ይልቅስ በራሱ ትርጉም የራሱን ማንነት ይበልጥ ገልጡል፡፡ ከንደዚኅ አይነት ዘላባጆችየይሰውረን!!!

 9. Merga says:

  የማነው ቆሻሻ ባካችሁ ዝም ብሎ ያስታዉካል እንዴ
  ቢያንስ ቢያንስ ፕሮፌሰር ናቸው ትልቅ ስራ ሰርተዋል ስለዚህ ክብር ይገባቸዋል ደግሞ የትኛው ህገ መንግስት ነው 3 ምክትል ጠ/ሚኒሰትር የሚለው? ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ሀ) «በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል» (ለ) «ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ተክቶት ይሰራል» ሲል፣ በንዑስ አንቀጽ ሁለት ላይ ደግሞ «ም/ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል» ይላል እንጂ ምክትል ጠ/ሚኒሰትሮቹ አይልም በደንብ አንብበው ራስክ የተፋከውን፡፡

 10. Kiyya says:

  Expected from Addis Zemen. ቤተ-ክርቲያን መሳም እንጂ ሌላ ምንም መስራት ያቃታቸውን ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዘደንት አድርጎ ከሚሾም መንግስት የተሰጠ አስተያየት. ምናለበት ስለምታውቀው ነገር ብትጽፍ?

 11. ohio says:

  who is this writer addis zemen or bereket kebt.?

Comments are closed.