ፍሬ-አልባ ጩኸት

አንሰ እቤ አምግዕዝየ ኵሉ ሰብእ ሐሳዊ ውእቱ!

(የዳዊት መዝሙር 115)

መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2005

አቶ ዳንኤልን አላውቀውም፤ ለካ ብዙ ጭፍሮች ያሉት ሰው ነው፤ በጣም ተንጫጩለት፤ የሎሌ ነገር ሆነና ጩኸታቸው አንድ ነው፤ ጉዳዩን ጭራሽ አያውቁትም፤ ያንገበገባቸው መሪያቸው መነካቱ ነው፤ ለሎሌዎቹ መልስ መስጠት ባልተገባ ነበር፤ ነገር ግን ያደረጉት ትክክል መስሎአቸው እንዳይኩራሩና በያዙት የመክሸፍ መንገድ አንዳይቀጥሉ አንዳንድ ነጥቦችን ላብራራላቸው ፈለግሁ፤ ውጤት ይኖረዋል ብዬ ሳይሆን ለኔው ለራሴና ለማኅበረሰባችን ጤንነት ነው፤ ራሴን ከአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ለመከላከል ፈልጌ እንዳይመስል፤ አትኩሮት በጉዳዩ ላይ እንዲሆን ለመሞከር ነው።

አንዳንዶቹ ዲያቆን የሚል ቅጽል ባለመጨመሬ ሆን ብዬ መስሎአቸዋል፤ ባለማወቅ ነው፤ ራሴን ተጠራጥሬ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከፈትሁና የማውቀውን ነገረኝ፤ — የተካነ፣ ምሥጢር ያየ፤ ቀዳሽ — የሚል፤ በዚህ መስፈርት እኔም ዱሮ ዲያቆን ነበርሁ፤ ዛሬም ይህንን የሚያሙዋሉ ወጣቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚልዮን ባይሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ይኖራሉ፤ በዚያ ላይ እኔ እንደማውቀው ዲያቆን ሦስት ደረጃዎች ሲኖሩት የዲያቆኖች አለቃ ሊቀ ዲያቆናት ይባላል፤ አቶ ዳንኤል ሊቀ ዲያቆናትም አልሆነም፤ የአቶ ዳንኤል ዲያቆንነት የቱ ዘንድ እንደሚወድቅና ምን ማለትም እንደሆነ አላውቅም፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም እንዲህ ያለ ማዕርግ መስጠት ጀምራ እንደሆነና ለነማን እንደምትሰጥ አላውቅም፤ እኔ ዱሮ የማውቀው ዲያቆን የቅስና ሥልጣን (በምድር ያሰራችሁት በሰማይም የታሰረ ይሆናል፤) ሲያገኝ መምሬ መባሉን ነው።

ወደተነሣሁበት ጉዳይ ልግባ — አንድ መጽሐፍ አሳተምሁ፤ አውቃለሁ የሚለው አቶ ዳንኤል ተነሥቶ ስለመጽሐፉም ስለሌላ ሌላም የማያውቀውን ጻፈ፤ ስድስት የግድፈት ነጥቦችን ለቅሜ በማስረጃ እያስደገፍሁ የማያዳግም መልስ ሰጠሁት፤ ይህንን ያደረግሁበት ምክንያት ጭፍሮቹ እንዳሉት ሥራዬን አትንቀፉት በማለት በመታበይ አይደለም፤ ማናቸውም ሥራ አደባባይ ሲወጣ መነቀፉ አይቀርም፤ ስሕተትም አይጠፋም፤ አንድ ሰው በአንድ የአገር ወይም የማኅበረሰብ ጉዳይ ላይ ሲጽፍ ወይም በአደባባይ ሲናገር ራሱን ማጋለጡ ነው፤ የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች ይህንን የማያውቁትን ጉዳይ ለእኔ ለማስተማር መከጀላቸው ጨቅላነታቸውን ያሳያል፤ በእኔ ላይ ባወረዱት ውርጅብኝ እንኳን ጉድጓድ ቆፍረው ራሳቸውን ቀብረው ነው፤ እውነተኛ ማንነታቸውን ደብቀው ነው፤ እነዚህ ጭፍሮች ስለመጋለጥ የሚያውቁት የለም፤ ስለዚህም ጉርጓድ ውስጥ ተቀብረው ስለማያውቁት ነገር መጮሁ የመጀመሪያው ስሕተታቸው ነው፤ ለነገሩ ስሕተት አይደለም፤ ወኔ-ቢስነት ነው።

እነዚህ ሁሉ ጭፍሮች ለጩኸት ከመጠራራታቸው በፊት መጽሐፉን ለማንበብና የክርክሩ መነሻ የሆኑትን ነጥቦች ለመጨበጥ አልሞከሩም፤ ወደው አይመስለኝም፤ ንዴታቸውን ለመግለጽና ግዳይ ለመጣል ስለቸኮሉ ለእነሱ ችሎታ የሚቀልለውን

‹‹የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፣

ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!

በማለት በአደባባይ አቅራሩ፤ የችሎታ ማነስና ችኮላ ተለውሶ ያንን ጫጫታ አስከተለ፤ ገና ይቀጥላል፤ ባገኙን ቦታ ሁሉ ይህንን ጀብዱአቸውን ሊገልጹልኝ የሞከሩም አሉ፤ ከመሀከላቸው አንድም አንኳን ጉዳዩን ለመገንዘብና በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሞከረ አለመኖሩ የአስተሳሰብ ደረጃቸውን በግልጽ ያመለክታል፤ የሁሉም ዘገባ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው።

 • ከመሀከላቸው ስለመጽሐፉ የተናገረ አንድም የለም፤
 • ከመሀከላቸው አንድም ሰው አቶ ዳንኤል ስለጻፈው የተናገረ የለም፤
  • መጽሐፉን ሳያነቡና የአቶ ዳንኤልን ጽሑፍ ሳያነቡ እንዴት ብለው   እኔ በጻፍሁት ብቻ እንደዚያ ያለ የንዴት ጫጫታ ማሰማት ቻሉ?

ለጭፍራዎቹ በመጽሐፉና በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ መሀከል ምንም ግንኙነት እንዳላዩበት ግልጽ ነው፤ ሊያዩበትም አይችሉም፤ ስለዚህ የእውቀት ጉድለታቸውን በንዴት ተኩት፤ እነሱው ራሳቸው የተገነዘቡትን የእውቀት ጉድለታቸውን እያጋለጡ ስለመጽሐፉ ለመናገር ወኔ አላገኙም፤ የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ማምለጫና መብለጫ በሆነው የብልጣብልጥ ዘዴ ተጠቅመው በእነሱ ግምት እነሱን ከፍ እኔን ዝቅ አድርገው ለማሳየት ሞከሩ፤ ጭፍሮቹ በሙሉ እውቀቱ ስለሌላቸው መጽሐፉን ረሱት፤ ስለዚህም ራሳቸውን የሥነ ምግባር ሊቃውንት አደረጉና ትንሽነታቸውን ወደበላይነት ለመለወጥ ጣሩ፤ ይህ ብልጣብልጥነት እንደማያዋጣ ስለገባቸውና የእውቀታቸውንም ጎዶሎነት ስለተገነዘቡ ማንነታቸውን ሳይገልጹ ስማቸውን ደብቀው በአደባባይ ደነፉ፤ ደስ አላቸው፤ አስደሰቱ፤  ‹‹ያንን ፕሮፌሰር ነኝ ብሎ የሚኮፈስ ሰውዬ ልክ ልኩን ነገርነው! ልኩን እንዲያውቅና ከእኛ የማይሻል መሆኑንም ነገርነው!›› አንዳንዶቹ የእውቀት ደረጃቸውን አዘቅት ሲያወርዱ ከመስፍን ጋር ፕሮፌሰርነትንም አብረው ይኮንናሉ! አይ ፕሮፌሰርነት! እንዲህ ከሆነ ይቅርብን! እያሉ ዘላበዱ።

ተመካክረው የተነሡት በእነሱ ሚዛን ስለመስፍን ወልደ ማርያም ምግባረ-ብልሹነት ለዓለም ለመንገር ነው፤ አዋጃቸውን እንቀበለው፤ ስለመስፍን ወልደ ማርያም አንድ እውቀት ያስጨብጠናል፤ ዋናው ጉዳይ ግን መስፍን ወልደ ማርያም አይደለም፤ ዋናው ጉዳይ መጽሐፉ ነው፤ እንግዲህ ስለመጽሐፉ ምንም የማያውቅ ሰው ስለመስፍን ወልደ ማርያም መናገር የሚችለው ስንት ገደሎችን ዘልሎ ነው? ሁሉም ያሉት መስፍን ወልደ ማርያም ለአቶ ዳንኤል የሰጠው መልስ ስድብ ነበር የሚል ነው፤ ነገር ግን ከመሀከላቸው አንድም ሰው ስድቡ ምን እንደነበረ አልተናገረም፤ አንዴም ደህና አድርጎ ያላነበበውን ደጋግሜ አንቤዋለሁ ብሎ ሐሰት የተናገረን ሰው ሐሰት ተናግረሃል ማለት፣ የማያውቀውን አውቃለሁ ብሎ የተናገረ ሰውን አታውቅም ማለት፣ የማያውቀውንና ያልሆነውን ነገር ሲለጥፍብኝና የተናገረውን መልሶ ምሥጢር በማድረጉ የደብተራ ተንኮል ማለት፣ ለእኔ ስድብ አይደለም፤ እውነትን መናገር፣ ወይም ፈረንጆች እንደሚሉት አካፋን አካፋ ብሎ መጥራት ነው፤ ማሰብ የሚችል ሰው ለተናገርሁት ማስረጃ እንዳይጠይቀኝ ማስረጃዎቼን ሁሉ ቁልጭ አድርጌ አቅርቤአለሁ፤ እንዲያውም ትልልቅ ግድፈት የምላቸውን ነገሮች አልገባሁባቸውም፤ እዚያ ብገባ የበለጠ አንጫጫ ነበር፤

ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን መጽሐፉን ያነበበ አይመስለኝም፤ ከጭፍሮቹ አንዱም እንኳን በአቶ ዳንኤል ጽሑፍ ውስጥ ምንም እንከን አላዩም፤ ሊያዩም አይችሉም፤ ከስድብም አልፎ ወንጀል ሊለጥፍብኝ ሲከጅለውም አልታያቸውም፤ ወንጀልን በሰው ላይ መለጠፍ አላዋቂነት፣ ተንኮል፣ ውሸት ቢባል ስሕተቱ ምኑ ላይ ነው? እውነት ከማይከበርበት ቤት የወጡ ጭፍሮች እውነትን አላዩም ብሎ መውቀስ ባይቻልም አለማየታቸውን መናገር ግን ተገቢ ነው።

የአቶ ዳንኤል ጭፍሮች የመጽሐፉን ቁም-ነገር መጨበጥ ስላቃታቸው የሥነ-ምግባር ጉድለት የመሰላቸውን የመመጻደቅ ስብከት አወረዱት፤ ነገራቸው ሁሉ እንደአህያ መልክ አንድ ዓይነት ነው፤ ራሳቸውን አፋፍ ላይ እኔን ደግሞ ገደል ውስጥ ጨምረው እንደናዳ ሊያወርዱብኝ ሞከሩ፤ ከጭፍሮቹ መሀል አንድም እንኳን እሱም ራሱ ሆነ ጓደኞቹ የጻፉት የምግባረ ብልሹነት መግለጫና ማረጋገጫ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ ያለው አልተገኘም፤ በነዚህ ጭፍሮች የማሰብ ችሎታ እውነት መናገርን እንደስድብ ከመውሰዳቸው በላይ እነሱ ግን ለመሳደብ ልዩ ፈቃድ ያላቸውና የሥነ ምግባር ደረጃቸውም  የተለየ ነው፤ እነሱ ሲሳደቡ የሥነ ምግባር ብልሽት አይታያቸውም! እውነትን በደረቅ ቋንቋ ከመስማት ይልቅ ውሸትንና ተንኮልን በለስላሳ ቋንቋ መስማት የሚበልጥባቸው ጭፍሮች አቶ ዳንኤል ለተናገረው ዓይኖቻቸውን ሸፍነው እኔ በሰጠሁት መልስ ላይ ማተኮራቸው ያጋደለ የሆዳምነት ሚዛናቸውን በገሀድ ያሳያል፤ ውሸት የተናገረን ውሸታም ማለት፣ ተንኮልን የሸረበን ተንኮለኛ ማለት ትክክል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእውነት የተራበ፣ ለእውቀት የተራበ ሆኖ ለብዙ ሺህ ዓመታት ባለህበት ሂድ ሲል የኖረው በእንደነዚህ ያሉ የእውነትና የእውቀት ጸር የሆኑ ጭፍሮች እየታገተ ነው።

ሳያውቁት የመክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ ዋናውን መልእክት በተግባር አሳዩ፤ እውነትንና እውቀትን (ሁለቱን መለየት አይቻልም፤ እውነትን የማይቀበል እውቀትን አያገኝም፤ እውቀትን የማይቀበል እውነትን አያገኝም፤) አርክሰው እነሱ ጨዋነት የሚሉትን አወጁ፤ አንዱ በማያሻማ መንገድ ገልጦታል፤ መስፍን ኃይለ ማርያም ነኝ የሚል እንዲህ አለ፤‹‹ከእርስዎ ምሁራዊ ስድብ የዳንኤል ክብረት ጨዋዊ መሃይምነት በእጅጉ ይሻላል፡፡›› ይህ ሰው እሱና ጓደኞቹ በያዙት ሚዛን ‹‹ስድብ›› ያሉትን ተቀብሎ ከመታረምና ወደእውነትና ወደእውቀት መንገድ ከመግባት ይልቅ ‹‹ጨዋዊ መሃይምነትን›› መርጦ ለመኖር መወሰኑ ያሳዝናል፤ የዳንኤል ክብረትን አስመሳይነት፣ ደፋርነት፣ አላዋቂነትና ተንኮል በማያሻማ ቋንቋ ለመግለጥ የወሰንሁት በእንደዚህ ያሉ ምስኪን ‹‹ጨዋዊ መሃይሞች›› ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ገምቼ ልከላከልላቸው ብዬ ነበር፤ ተመችቶናል ስላሉ እግዚአብሔር ያውጣቸው፤ ሌሎች ሕመሙ እንዳይጋባባቸው ይጠንቀቁ!

በመጨረሻ በእውቀት ጉዞ ይሉኝታ፣ መግደርደር፣ መሸፋፈን፣ ማድበስበስ፣ መቀላመድ፣ የተጠሉና የእውቀት ጸር በመሆን የሚፈረጁ ዝንባሌዎች ናቸው፤ ሀ ማለት ሁለት ነው፤ ለ ማለት ሦስት ነው፤ ከተባለ ሀ+ለ አራት ነው ሲል የተጻፈውን አላነበብህም፤ ወይም አልገባህም፤ ስለዚህም መልስህ ልክ አይደለህም ማለት መማር ለፈለገ ነውር አይደለም፤ እውነትንና እውቀትን ለማራመድ መንገዱ ይህ ነው፤ የተገነዘበው ይራመዳል፤ እውነትን የሚፈራው ወደኋላ ይቀራል፤ መክሸፍ ማለት እንዲህ ነው።

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

44 Responses to ፍሬ-አልባ ጩኸት

 1. diganka haway says:

  ፕሮፍ
  መጸሃፉን በመጀመሪያ ከልብ ወድጀዋለሁ ልምን ቢባልም አንዳንድ ያሉኝን ጥያቄዎች ከታሪክ ተመራማሪ ሰዎች ያላገኘሁትን ምላሽ ሰጥቶኛልና፡፡ የትኛዎቹን ጥያቄዎች ከተባልኩ ወደፊት በሰፊው እጥቅሰዋለሁ ለዛሬው ማለት የምፈልገው ፕሮፍ እንደዚህ ዓይነት መጸሃፍ ይደጋግሙን፡፡

  የእርሶ አክባሪ

  ዲጋንካ ሃዋይ

 2. henok says:

  ወንድም አንትነህ መጀመሪያ
  1ኛ መጽሐፉን አንብበው
  2ኛ የዳንኤልን አስተያየት አንብበው
  3ኛ የፕ/ር መስፍንን መልስ አንብብ (በዛውም የተሰጣቸውን አስተያየት(comment) አንብብ)
  4ኛ ይሄን ጽሑፍ አንብብ(በዛውም ለማን እንደተጻፈ እና ለምን እንደተጻፈ ተረዳ)
  በተጨማሪም ስድብ ነው ያልከውን የቱ እንደሆነ ተናገር

 3. devatasol says:

  እውነት የመናገር ድፍረት ይኑረን

 4. Kolotemari says:

  Thank you professor,
  I clearly understand what you are saying. Ato Daniel is lucky to get a blessing from professor, who is 86, who witnessed our country life for more than 60 years. I wish i am a beginner(of social writer) like Daniel(compared with Professor Mesfin and other Ethiopian seniors) and acknowledged by this brave old man.

  I look forward reading your articles in the coming days, weeks, years, 5 years, more than 15 years. I look forward reading the articles of young Ethiopians who obey truth and have edging knowledge

 5. ነፃነት አሸናፊ says:

  እኔ በጣም አዝናለሁ፡፡ ጋሼ መሽፍን አከብርዎታለሁ ግን ይሄ ምልልስ ይብቃ፡፡ ከዚህ ቀደም ለዳንኤል “ሂስ” በቂ እና (መፅሀፉን ላነበበ) አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እኛም (መፅሀፉን ያነበብን ማለቴ ነው) የሁለታችሁንም ሰምተን የየራሳችንን ፍርድ ሰጥተናል፡፡ ዲን. ዳንኤል መፅሀፉን ከመተቸቱ በፊት ቀረብ ብሎ ቢያናግሮት ካልተስማማም “አናግሬያቸው ነበር ግን አሁንም….” ብሎ ቢተች ከብዙ ስህተቶች ይድን ነበር፡ ግን አልሆነም፡፡ ዲን. ዳንኤን ትችቱ ቢከሽፍበትም አንድ ነገር ተሳክቶለታል መፅሀፉን ዋጋ ማሳጣት!!!! ጉዳዩ(መፅሀፉ) ወደ ግለሰብ እሰጥ-አገባ መውረዱ አሳዛኝ ነው፡፡ የግለሰብ ታሪክ እና ማንነት ያው ከግለሰብ ታሪክነት አያልፍም፡፡ ለአንድ ሰው ዳኛው ህሊናው እና ፈጣሪ ነው፡፡ የአደባባይ ሰው ከሆነ ደግሞ ህዝብም ዳኛ ይሆናል፡፡ በርግጥ እየከሸፈ ያለን ነገር መታደግ መልካም ነው፡፡ ግን አውቆ እንዳላወቀ በተንኮል ሌላውንም ወደ ጥፋት ይዞ የሚጉዋዘውን ግን ለመመለስ መድሀኒቱ መመላለስ ሳይሆን የሚታደገውን ብርቱ እና ትጉህ ትውልድ መፍጠር ማጎልበት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው በማስተማር መንገድ በመቀየስ ነው፡፡ ጋሼ መስፍን እባኮትን አሉባልተኞቹን ይርሱዋቸው፡፡በንፁህ ህሊና ወደ ዋናው ጉዳይ እንመለስ፡፡ ስለ መፅሀፉ እንወያይ ስለ ሀገራችን እንወያይ፡፡ በውድ ጊዜዎት እውቀትን፣ እውነትን ለሚሻው ትውልድ ተግተው ያስተምሩ፡፡ የተማረ ይለውጣል ሌላውንም ይታደጋል፡፡ እድሜና ጤና ይስጥልኝ፡፡
  አክባሪዎ
  ነፃነት አሸናፊ

 6. men says:

  ፕሮፌሰር ሥለ እርስዎ ጭፍሮችስ የሚሉት ነገር የለም?

 7. Ewnet says:

  “ከመሀከላቸው ስለመጽሐፉ የተናገረ አንድም የለም፤ ከመሀከላቸው አንድም ሰው አቶ ዳንኤል ስለጻፈው የተናገረ የለም፤ መጽሐፉን ሳያነቡና የአቶ ዳንኤልን ጽሑፍ ሳያነቡ እንዴት ብለው እንደዚያ ያለ የንዴት ጫጫታ ማሰማት ቻሉ? እነዚህ ሁሉ ጭፍሮች ለጩኸት ከመጠራራታቸው በፊት መጽሐፉን ለማንበብና የክርክሩ መነሻ የሆኑትን ነጥቦች ለመጨበጥ አልሞከሩም፤ ወደው አይመስለኝም፤ ንዴታቸውን ለመግለጽና ግዳይ ለመጣል ስለቸኮሉ ለእነሱ ችሎታ የሚቀልለውን
  የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፣
  ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!
  በማለት በአደባባይ አቅራሩ፤ የችሎታ ማነስና ችኮላ ተለውሶ ያንን ጫጫታ አስከተለ፤ ገና ይቀጥላል፤ ባገኙን ቦታ ሁሉ ይህንን ጀብዱአቸውን ሊገልጹልኝ የሞከሩም አሉ፤ ከመሀከላቸው አንድም አንኳን ጉዳዩን ለመገንዘብና በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሞከረ አለመኖሩ የአስተሳሰብ ደረጃቸውን በግልጽ ያመለክታል፤ የሁሉም ዘገባ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው።” Professor Mesfin Woldemariam

 8. Dagim says:

  I do not know prof. Mesfin W/Mariam in person. I am and has been a geography student. I have read some of the books the professor wrote. I will , here, take the liberty of saying that i am a good
  reader. My friends! it is very easy to see who the professor is through his writings- it only takes the ability of examining, scrutinizing and trying to competently evaluate the relations and logical unity of the diverse claims embodied in the writings of the intellectual we are talking of. He has managed
  to sufficiently convince me that he is possessed with the ingenuity of rendering meaning and life to
  the objects of intellectual inquiry…….What he put forth as objects of argument in his latest book are most appropriate …the argument he mounts against the thesis of the incumbent party is neatly intellectual and demonstrably cogent hence never out of prejudice or hatred…the issues he touches upon are reflective of the wishes he has for the state where he belongs…what i am writing here is not enough about his beauty….I only wish that he stays alive and writes more since i believe that he is a giant Ethiopian philosopher!!!!!!!!!! His health is more important not for him but for you Guys !!! Stay better reading!!!!

 9. Heruy says:

  Nice prof. don’t west time by responding for these “debtera”

 10. elias says:

  ማንበብ ለሚችል እያንዳንዷ መስመር በቁም ነገር የተሞላች ነች እንዲህ ዓይነት ጽሁፎችን ልመዱ እንጂ ወይስ ገና ሌላ ሺህ ዓመታት ያስፈልጋል? ደብተራንም አታሰድቡ እንጂ (ወርቄም እኮ ደብተራ ነበረ )! በግሉ በመከሩት የሚትለዉ የግል ጉዳይ አስመሰልከዉ አቶ ዳንኤል ባደባባይ ‘ጨዋነቱን’ እኮ አስመሰከረ ስለማያቀዉ ተናገረ እና ሚስጥር አደረገ ባደባባይ ካልጻፈዉ ልክ እንደሳችዉ እንዴት ማወቅ እንችላለን ? ልብ ዉስጥ ያለዉን ማንበቢያ በሳይንሱ እስካሁን አልተሰራም በድብትርናዉ እንዳለ አላዉቅም ስለዚህ ኢንተርኔት ተገኘ ተብሎ ዝም ብሎ ከመንጫጫት ሰከን ብሎ ማሰብ እና ፕ/ር ምን ለማለት ፈልገዉ ነው? ምክንያታችዉ ምንድር ነው ብሎ መመርመር መጠየቅ ያስፈልጋል እንዴ እያሰብን እንጂ ወገን ጋሽ መስፍን እኮ ከ14 በላይ በምርምር ላይ የተመረኮዘ ዕዉቀት ጠገብ መጽሃፍትን ለኛ ለሚወዱን ኢትዮጵያዉያን አበርክተዋል አሁንም አልሰነፉም እየለፉ ነዉ አመስግኑኝ ባይሉም በጠብ የለሽ በዳቦ ልንወርፋቸዉ አይገባም አሳዳጊዎቻችን እና የቆምንበትን የስነ ምግባር መርህ አያሳየን ይመስላል እኛ ለሃገራችን ምን አበረከትን አንተን ጨምሮ ? ይህንንም መጠየቅ ያስፈልጋል ለራስ
  እሳቸዉ እኮ ስለ ልማት ስለ ርሃብ ስለ ግጭት ስለ ባህል የመሳሰሉትን ስራዬ ብለው ያገባኛል ብለው አዉሮፓ እና አሜሪካ ቁጭ ሳይሉ እዚሁ ህመሙንም አብረዉ እየታመሙ አጥንተዉ እነሆ በረከት ብለዉናል! ሊገባን ይገባል ሊሰማን ይገባል ስለ ልፋታቸዉ ቢያንስ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅብዎ ብቻ እንኳ ብንል ይበቃል ኧረ እኛ ምን ጉዶች እንደሆንን አይገባኝም ያደለዉ ሙሁሮቹን አቀማጥሎ ይይዛል እኛ ደግሞ ያሉንን ለምን ብቅ አሉ እያልን እንጨፈጭፋለን እንሰድባለን እናንጓጥጣለን ያሳዝናል በጣም ያሳዝናል አቶ Bewketu የጭቃ ጅራፍህን እዛዉ ከ እኩዮችህ ጋር አድርገዉ!

 11. በእኔ እይታ ፕሮፌሰሩ በመጀመሪያው ጽሑፋቸውም ቢሆን ለዳንኤል መልሱን የሰጡት ስድቡን ትተው ቢሆን መልሳቸው አስደናቂ መልስ ይሆንላቸው ነበር፤ ሆኖም ‹አንተ አላዋቂ አርፈህ አትቀመጥም!› ዓይነት አቀራረባቸው ቅልብጭ ያለ መልስ ሊሆን የሚችለውን መልሳቸውን አጠፋባቸው፤ ውይይቱንም መሳደባቸው ትክክል ነው ወይስ አይደለም ዓይነት አደረገው፤ ይህም ስለሆነ ነው መጽሐፉ የተረሳው፡፡ ይሁንና ስገምት ግን በመጽሐፋቸውም ሆነ በጽሑፋቸው ዙሪያ ውይይትና ክርክር እንዲቀጣጠል የፈለጉ ይመስለኛል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል፤ በማኅበራዊ ድራተ ገጾች ብዙ አስተያየቶች ተጽፈዋል፤ በመጽሔቶችና በጋዜጦች ላይ ትችቶች እየጎረፉ ነው፤ ወደፊትም ብዙ የሚያነጋግሩ ሐሳቦች በመጽሐፉ ዙሪያ የሚነሣ ይመስለኛል፤ በግል እንኳን ከጓደኞቻችን ጋር ስንት እንደተሟገትን የምናቀው ራሳችን ነን፤ ችግሩ የተከሰተው መስመር ስቶ ወደ ግለሰቦች የቲፎዞ እንካ ሰላንቲያ በመግባቱ ነው እንጂ!፡፡
  እኔ እንደሚገባኝ ዳንኤልም ቢሆን ብዙ ውርጅብኝ ከፕሮፌሰርም ሆነ ከአወዳሾቻቸው የወረደበት የመሰለውን አስተያየት በማቅረቡ ነው፡፡ ጎበዝ የሆነ እሱን ከመኮነን ነጥቦቹን እየበለ ማቅረብና ከመጽሐፉ አንጻር መተቸት እንጂ በጥቅሉ ጠላሁት ደግ አረጉት የመሳሰለ አስተያየት ጥቅምም ትርጉምም የለውም፡፡ እንደ እኔ አረዳድ በቀድሞ ጽሑፋቸው ፕሮፌሰሩን ያስቆጣቸው የዳንኤል ከመጽሐፉ ርእስ ጀምሮ ያደረገው ሒስና የውስጠ ወይራዊ ጉሽሚያ ይመስለኛል፡፡ የዳንኤልን አቀራረብ ከተመለከትነው መጽሐፉ የሚያሚያጠነጥንብትን የኢትዮጵያን ታሪክ የመክሸፍ ጉዳይ ስቶታል ይላል፤ የታሪክ ጸሐፊዎቹን መተቸትም ትክክል አይደለም በሚል የሞራል ጥያቄን ያነሳል፤ በዚህ አቀራረብ አንጻር ከተመለከትነውና የዳንኤልን ትችት በትክክልነት ከተቀበልነው፤ የፕሮፌሰሩ መጽሐፍ ትርጉም የሌለው ሐተታ ይሆናል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ዳንኤል በመደምደሚያው ላይ በሸወርኔ አቀራረብ ‹ቤተ መንግሥቱን ዓየሁት› በማለት ይወጋቸዋል፤ ይህ ምን ያህል ሊስቆጣና ሊያበሳጭ እንደሚችል ለመገመት ፕሮፌሰርን መሆን አይጠበቅብንም፤ ስለ ቤተ መንግሥት ያተተው ታሪክም ቢሆን የሚከነክን ጥያቄን የሚያጭር ነው፤ የዳንኤልም ትልቅ ስህተትና በመነሻው ላይ ያስቀመጣቸውን ነጥቦች የሸፈነበት ይህ አስተያየቱ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ የጻፉትን ዋጋ አሳጥቶና ‹ማን ነዎትና ነው!› ዓይነት የቃላት ጦርን ሰብቆ ያገኙትን ጽሑፍ አንብበው ባይናደዱ ነበር የሚደንቀው፡፡ ፕሮፌሰር አልተሳደብኩም ‹አካፋን አካፉ ነው ያልኩት› ማለታቸው ግን አጥጋቢና እውነታነት ያለው አይመስለኝም፤ እንደ እውነቱ ቢሆን ኖሩ የዳንኤል ጽሑፍ እየበለቱና እየነጠሩ መልስ ቢሰጡበት ብቻ ለሌሎችም መልካምነት ይኖረው ነበር፤ ያን ያደረጉ አይመስለኝም፤ አቀራረባቸው ‹አላዋቂ ስለሆነ ነው የተቸኝ› ዓይነት ነው፡፡
  በነገራችን ላይ እኔ በግሌ በፕሬፈሰሩ መጽሐፍ ላይ ብዙ የማልስማማቸው የአቀራረብ፣ የመነሻና የአተያይ አስተያየቶች አሉኝ፡፡ ለምሳሌ (1) የመጽሐፉ ርዕስ ብዙ አጨቃጫቂነት አለበት፤ የኢትዮጵያ ታሪክ ከሽፎ አልቋል በሚል ታሪክ ለሌላ ጉዳይ ማነጻጸሪያ በመሆን የተጠቀሰ ይመስልበታል፡፡ (2) የመጽሐፉ ዋና ማጠንጠኛ ትልቅ ምሰሶ ያለው ከምዕራፍ 5-6 ውስጥ ይመስለኛል፤ ይህንን እንደዋና ማጠንጠኛ ከተመለከትነው ከዚያ በኋላ የገቡት ምዕራፎች ትርፍ አንጀቶች ናቸው፤ እንዲሁም (3) ‹ከሸፈ› የሚለው የኢትዮጵያ ታሪክ የትኛው እንደሆነ ግልፅ አያደርግም፤ የጥንቱ ታሪካችን ነው ወይስ ዘመናዊ ታሪካችን? ሁሉም ከተባለ ከመቼ እስከ መቼ ነው የከሸፈው? ነው ሲከሽፍ ነው የኖረው? በማን የተሠራውን ታሪክ ማን አከሸፈው? እንዴት? ነው አዘጋገቡ ነው ያከሸፈው? … (4) እንደገናም የፕሮፌሰር ዓይን በኢትዮጵያ ውስጥ ጭላንጭልም አይታየው ሁሉንም (ባህሉን፣ ሃይማኖቱን፣ ታሪኩን፣ አስተዳደሩን፣ ጦርነቱን…) በዘመናዊ ጥላ ጨለማ አልበሶ ነው የሚያደናብረን፤ ለነገሩ በብሔራዊ ትያትር እንደተናገሩት ‹ያልከሸፈ አጣሁ› ብለዋል፤ ያልከሸፈ ከሌለን ታዲያ ምን ተስፋ አለንና እንለፋለን? ተስፋ ቆርጠን እንቀመጥ እንጂ! እንደ እኔ አረዳድ ምንም ዓይነት ተስፋ አስቆራጭ ነገር ቢያጋጥመን የተስፋ ጭላንጭሎችን መቃኘት ይኖርብናል እንጂ ሁሉንም ዳፍንት አድርገን መውሰድ አግባብ አይመስለኝም፡፡ (5) ምንም እንኳን ሥልጣንን መግራት አለብን በሚሉት ብስማማም ሁሉንም ከሥልጣንና ከፖለቲካ ቅኝት የሚያደርጉት ትንታኔ የአንድ ጉዳይ ማጣንጠኛ ተፅዕኖ አለቃቸው ያለ ይመስለኛል፤ የ1950-60ዎቹ የተማሪዎች የፖለቲካ ንቅናቄና ኡ! ኡ!ታ ቅኝት፡፡ … ለማንኛው ይህን ጉዳይ ወደፊት በሰፊው ከመጽሐፉ ነጥቦች ጋር እያገናዘብኩ በግሌ ያለኝን ትዝብት የምቃኝበት ቢሆንም መጽሐፉን ከርዕሱ ጀምሮ ሲያስተውሉትና ይዘቱን እያበጠሩ ሲቃኙት በመክሸፍ አዝማች ተቃኝቶ፤ ብዙ ጉዳዮችን አጭቆ በሚጥም የቋንቋ ችሎታና ፍሰት የቀረበ ነው፡፡
  በአንድ ነገር ላይ እንስማማ ይመስለኛል፡፡ ምንም ይሁን ምን ይህንን አስተሳሰቤን የቀሰቀሱት እሳቸው ይህን አስደናቂ መጽሐፍ በድፍረት ስለጻፉ ነው፤ ዳንኤልም ወቀሳና ስድብ የደረሰበት ደፍሮና መዝኖ ስለተቻቸው ነው፤ ብዙዎችን ለመወያየት ያስቻላቸውም ንቀው ዝም ሳይሉ መልስ በመስጠታቸው ነው፤ ሌላ ቢሆን ‹ዝም አይነቅዝም› ብሎ ይቀመጥ ነበር፡፡ ምንም ቢሆን በደባባይ ወጥቶ ካልተተቸ አሳብ በሕዝብ ዘንድ ቀርቦ የተነቀፈ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ይህንንም መሰለኝ ፕሮፌሰር በመጽሐፋቸው ‹ራስን ማጋለጥ› ያሉት፡፡ ለማንኛውም የዳንኤልንም ውስጠ ወይራዊ ትችት፤ የፕረፌሰሩንም ‹አካፋን አካፋ› ብያለሁ ዓይነት ውረፋ በቀለለ ዕይታ ተመልክተን በመጽሐፉ መሠረታዊ መከራከሪያና ዕይታ ዙሪያ መወያየት መልካም ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያ በስድድብ ቀለበት ውስጥ መሽከርከር ይሆናል፡፡

 12. Mesfin Hailemariam says:

  ይመችወት! እንኳንና በእርስዎ ዕድሜ ያሉ ይቅርና እንደ እኔ ገና በጎልማሳነት ውስጥ የምንገኝ የመጻፍ ወኔውን ወይ ሸጥን በልተነዋል አለዚያ ደግሞ ኖሮም አያውቅም፡፡ ምንም ነገር ቢፅፉ አስተማሪነቱ የጎላ ነው፡፡ ለማንኛውም ሐሳቤንም ጸሎቴንም አንስቻለሁ- ለምን እንደ ማቱሳላ ዕድሜውን አያረዝመውም !!!
  “ስድብ” በሚመስለው ፅሑፍዎ ውስጥ እንኳ ስንት ቁምነገር አለ!!!

 13. Bewketu says:

  ምነው ፕሮፌሰር::

  ባለፈው (27/01/2013) ለዳንኤል ክብረት ጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ለማንበብ ሞክሬአለሁ: በተጨማሪ የራሴን ሐሳብም አካፍያልሁ:: (Bewketu says:January 28, 2013 at 12:20 pm ):: አሁንም ቢሆን ጽሑፎ አልተመቸኝም:: በባለፈው አስተያየቴ ለምን እርስዎ ቁጣ እንዳበዙ አልገባኝም ነበር:: ያኔ ስድቡ ዳንኤል ላይ ነበር ዛሬ ደግሞ እኛ ላይ ሆነ? ምንድን ነው ችግሩ:: እርስዎ ከዳንኤል ጋር ችግር ካለብዎት ለምን እንደተማረ ሰው ተቀምጣችሁ አትግባቡም:: እኔ እዚህ ላይ ከወገንተናዊነት ወጥቼ ነገሮችን ለማየት ሞክሬአለሁ:: እንደ እኔ ከሆነ ዛሬም የሰጡት ምላሽ ምንም ሚዛን አይደፋም:: ጥቂት ምሳሌዎች ለማንሳት ልሞክር::

  1) ከርዕሱ ብንጀምር “ፍሬ-አልባ ጩኸት” ይላል: እርስዎ ባለፈው የሰጠነውን አስተያየት ጩኸት ብለው ጠርተውታል:: በየቦታው የዳንኤል ጭፍሮች እያሉ የገለጹት አገላለጽ በጣም ደስ አይልም:: መጀመሪያውኑ ሁሉንም አስተያየት ሰጪ በጅምላ መውቀስ በጣም አሳፋሪ ነው:: እራሴን እንደምሳሌ ማንሳት አይሁንብኝ እንጂ : እኔ የሰጠኹት አስተያየት ለምን ሃሳቡ ላይ አይከራከሩም ነበር ሃሳቤ (ተመልሰው ያንቡት)::

  2) በባለፈው ጽሑፎ ማስረጃ ብለው ያቀረቡትን 6 ዝርዝሮች ሲያቀርቡ ማሳየት የፈለጉትን ሲገልጹ “ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡” እንዲህ ብለው ነው የጀመሩት:: ይህ ለእኔ እርስዎን ማቅለል ይመስለኛል:: ታዲያ ስህተት አለ ብለው ካሰቡ ለምን በሃሳቡ ላይ ብቻ ለመሞገት አይሞክሩም:: እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቆት:- የዳንኤልን ተንኮለኛነት: መሰሪነት ማሳወቅ ምን ይጠቅማል? ወደ እኔ ላምጣውና እኔ ስለመጽሐፎ አስተያየት ስሰጥ ስለ በእውቀቱ የችሎታ ማነስ መናገር ለአንባቢያን ምን ፋይዳ አለው????

  3) ሁሉም ይቅርና ዳንኤል ያቀረባቸው ሃሳቦች በእርስዎ እይታ ሚዛን ካልደፋ. ለምን በዚህ በዚህ ምክንያት አቶ ዳንኤል ተሳስተሃል:: ይሄን የመጽሐፍ ክፍል አንበው::እዚህ ላይ ለማለት የተፈለገው ይሄ ነው:: ብዙ ትህትና የተሞላቸው ቃላትን መጠቀም የሚቻል ይመስለኛል:: ስለ አዲሱ መጽሐፍ የተሰጠ አስተያየትን መነሻ አድርጎ ሌላ ነገር መቀባጠር ግን እርስዎን ቀላል ያደርግዎታል:: እርስዎ ተመራማሪ የሚደርስበትን ትልቁን ቦታ ፕሮፌሰርነት ደርሰዋል:: ለዝና ለስም እንደማይሰሩ ይታወቃል:: ግን አሁንም ወደፊትም ቢሆን ለምን ተነካሁ አይነት አስተያየቶ የሚገባኝ አይመስለኝም::

  በመጨረሻ አንድ ወሳኝ ነገር ላንሳ:: የእኛ የመተራረም ባህላችን እንዴት ነው? አስተያየት የመቀበል ባህላችን እንዴት ነው? የሚሉትን ሳስባቸው በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ አዝናለሁ:: አንዳንዶቻችን ሃሳብ ስንሰጥ ወይም የአበበ ወይም የከበደ: ወይ የኢሕአዴግ ወይም የቅንጅት:: ማለት የፈለግኩት አስተያየቶችን የምንሰጠው ሚዛናዊ በሆነ መልኩ አይደለም:: በፌስቡክ በፓልቶክ; በብሎጎች አንዳንዴ እኛ አበሾች [ሁሉን ለማለት ፊልጌ አይደለም] የምንሰጣቸው አስተያየቶች ሚዛናዊ አይደለም:: ስድብ እናዘወትራለን [በእውነት ነው የምላችሁ በሃሳብ መማገትን መልመድ አለብን ይህም በብስለት: መረጃን በማስደገፍ]:: እንደ እኔ በስድብና በቡጢ ለማሸነፍ መሞከር ትልቅ ውድቀት ነው:: በአሁኑ ዘመን በጠረጴዛ ላይ ውይይት ችግሮችን መፍታት ነው የሚጠበቀው:: ይሄ ሁሌም የሚያንገበግበኝ ነገር በእርስዎ ላይ ሳየው: ምን ተስፋ አለን አልኩኝ:: ይህ ትውልድ እኮ ከመስመር እየወጣ ነው:: ጠባብነት እየተጠናወተው ነው:: አርቆ አሳቢነት: ነገርን ሰፋ አድርጎ ማየት እያጣ ነው:: እርስዎ ነገሮችን አስፍተው ያያሉ ብለን በምናስብበት ሁኔታ የጽሑፎን መጀመሪያ የሰውን ታናሽነት ለማሳየት ነው ጽሑፍን የጻፍኩት ማለት ምን ይሉታል::

  ነገር እንዳበዛሁ ይገባኛል:: ለማጠቃለል: በጅምላ አስተያየት ሰጪዎችን አይውቀሱ:: በተሰጠው ሃሳብ ላይ ያተኩሩ:: በፓለቲካ ፓርቲዎች ውይይት: በየዩኒቨርሲቲዎች በተማሪና በአስተማሪ ውይይት መልካም እንዲሆን እንደምሻ በፕሮፌሽናል ጸሐፊዎች ዘንድ ችትቶች እንዴት እንደሚጎለብት ያሳዩን:: አስተምሩን:: ዳንኤል ጋር ችግር ካለብዎት እባክዎትን እዛው ይጨርሱት:: በብሎግም: በአካልም መግለጽ የራስዎ ምርጫ ነው:: ነገር ግን ሰው ሞያ ብሎ ስለአዲሱ መጽሐፎ አስተያየት ሲሰጥ: ሃሳቡን ብቻ ይከራከሩ::

  አበቃሁ:: አምላክ ሆይ ይህንን ጽሑፍ ፍሬ አልባ ጩኸት ከመባል ሰውረው::

  • meyisawu says:

   wedaje anitem enide daniel yetsafut aligebahim eniji anite endemitilewu arigewu newu eko yetsafut….engidih ewuket endiwu zim bilo ayigegn….yezih hulu neger menesha eko yemetsihafun hasab aliteredahewum….silizih tesasitehal….yeewuket chigir alebih…..lezih demo masirejawu yihewu newu yetebalewu…..silizih chigiru yalewu daniel ena jeliewoch gar newu….anite minahin ley…

  • Alazare says:

   Tekekele…Afe sikefete Chenekelate Yetalale profsseru …Chenekelatachew Taye .

 14. alebe says:

  ፕሮፌሰር እኛ ስለ ዳንኤል አያገባንም! ጥሩ ጸሐፊ መሆኑን ግን አንረሳም፡፡እርስዎ ግን እንደ እድሜዎ ብዛት(›80)ቢያስቡና ቢናገሩ ጥሩ ነው፡፡ዝም ቢሎ መቦትለክ ጥሩ አይደለም፡፡ስለዳንኤል ክብረ-ክህነት ማውራት ለምን አስፈለገ? ስለግለሰብ ታሪክ እኛ አያገባም እርስዎም በመፅሐፍዎ ሊያነሱ የሞከሩት የሃገር ታሪክ ሆኖ ሳለ ውደ ግለሰብ ጉዳይ መውረድዎ ብድር ለመመለስ ይመስላል ወይም እርሱ (ዳንኤል) በጽሑፉ መጨረሻ ያነሳው ምስጢር ያብከንንነዎት ይመስላል፡፡አይበሳጩ! እርስዎ እንዳሉት ሁላችንም ስለከሸፍን ነው ብለው የለ? ስለዚህም የእርስዎን መክሸፍ ስለሚያረጋግጥ በሚቀጥለው ዕትምዎ ከከሸፈው የሰብአዊ መብት ምናምን ድርጅት ቢያካትቱት ይበጃል እንጂ መበሳጨትዎ የመጽሐፍዎን ጭብት ሚዛናዊነት ያሳጣል፡፡
  በተረፈ ከመጽሐፍዎ መቅድም ውጭ ያለው ታሪክ ሙሉ በሙሉ ባልቀበለውም በጣም ተመችቶኝ አንብቤዋለሁ፡፡ሌሎች የጻፉትን እንዳነብ ስልገፋፋኝ ሳላመሰግንዎት አላልፍም፡፡
  ሚዛናዊ ጽሑፍ እንዲጽፉ ፈጣሪ ይርዳዎ!

  • ለማስታወስ ያህል፣ ስለግለሰብ እኮ የተነሳው ጽሑፉ ላይ አቶ ዳንኤል ለምን «ዲያቆን» ዳንኤል በሚል ማዕረግ አልተጠራም የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ በመቅረቡ ነው።

   • Bewketu says:

    I wish this was not in to the discussion. I may be wrong but, I think some readers have to be a little bit broad minded (please tebab atihunu). I am orthodox and understand the rank/status Deacon in our church heirarchy. But we should not forget this, this is a title given by the church. This is public domain, any one can read the blog. As to me, guys we should stop commenting about whether we should keep the Deacon title or not. Rather the issue should have been, “are we giving a person a respect which he deserves?” Did prof Mesfin give respect to Daniel? Why do you think people call each other Sir [in English conversation], it is about respect, professors in the developed world are called by their first names. They like it that way, does this mean it is disrepecting them? NO IT IS NOT. Just generally, a person has to give a person to another person. It is just nice to do that, something which comes from good moral.

    Neverthless, professor Mesfin’s reply about Deacon’s definition, and others I strongly disagree. I am okay when prof does call him Ato daniel (explained above), but will really appreciate if prof can keep respect in the whole of his discussions.

 15. Lila says:

  ፕሮፌሰር የእውቀት ዐመዳሞችን ለመግረፍ አለያም የእውቀት ጽምዕ ያጠቃቸውን ለማርካት ቦዝነው አያውቁም። እንደዚያም ሆኖ ሰው በሁሉ ነገር ምሉዕ ባለመሆኑ የፕሮፌሰሩን ጉድለት አይቶ ለመተቸትና ለመንቀፍ እውቀትን መሠረት አድርጎ ለመተቸት ራሱ እውቀት ይጠይቃል። በባለፈው ጽሁፍ ላይ ዳንኤል ከጻፈው ይልቅ ያስገረሙኝ የጭፍራዎቹ ሂስ ወይም ጭብጥ ያለው ነቀፋ የማቅረብ ድኩምነት የስድብና ማሽሟጠጥ ብቃት ከፍተኛ መሆኑ ነበር። አሁንም የዳንኤል ጭፍሮች ይህንን የእውቀት ጉድለት ዐመዳቸውን እዚህ መጥተው ያራግፋሉ። ገሚሶቹ ዳንኤልን የኃይማኖት ጠበቃ አድርገው ስለሳሉት እሱን ከየትኛውም ጥቃት መከላከል የጽድቅ ስራቸው አድርጎ መቀበላቸው ነው። ገሚሶቹም እውቀት ማለት በዳንኤል ልክ ነው ብለው ስላሰቡ ከዚያ ያልገጠመውን ሁሉ ማንም ይሁን ማን በየትኛውም ማእረግ ይገኝ እንደአላዋቂ ይወቅጡታል። ፍልጥ እውቀታቸውን በፍልጥ ስድቦቻቸው ለማሳየት በጋራ ይጮሃሉ። አንድ የሚያደርጋቸው አለማወቃቸው ብቻ ሳይሆን አንድ ዓይነት ስድብ ማውጣት መቻላቸው ነው። እንግዲህ እነዚህ ናቸው የኃይማኖት ጠበቃ፤ የዳንኤል ተሟጋችና የማኅበረ ቅዱሳን ሞጋቾች አድርገው ራሳቸውን እዚያም እዚያም ጥልቅ የሚያደርጉት። ግእዝ ኦን ላይን እንዳለው፤
  (ዮምሰ መምህራነ ኮኑ በበደወሉ፤ ፊደላተ ዘኢኈለቍ ኲሉ) «አፍ ያለው ወይስ ጤፍ ያለው» ስትባል ፤አፍ ያለው ያግባኝ እንዳለችው ማለት ነው። ዛሬ አፍ ያለው እውቀት ያለውን በልጧል።

 16. ንጋቱ says:

  “….የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእውነት የተራበ፣ ለእውቀት የተራበ ሆኖ ለብዙ ሺህ ዓመታት ባለህበት ሂድ ሲል የኖረው በእንደነዚህ ያሉ የእውነትና የእውቀት ጸር የሆኑ ጭፍሮች እየታገተ ነው።” ከመንጋ አስተሳሰብ ከአጨብጫቢነት መቼ ይሆን የምንወጣው፤ በራሳችንስ ሀሳብ የምንቆመው

 17. mekonnen t. says:

  ፕሮፈሰር በእውነት የሚገርም ፅሁፍ ነው ያሳተሙት። እኔ ታሪክን በዩንቨርስቲ ደረጃ ተምርያለሁ ነገር ግን በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚተነትን ምሁር ኣላጋጠመኝም። እርስዎ ስራዎትን ይቀጥሉ በእውነት ኣገርን የማዳን ስራ ነው እየስሩ ያሉት። ስለ ስራዎ በእጅጉ እናመሰግናለን። እድሜና ጤና እግዚኣብሔር ይስጥልን።

 18. hyder zeediogenes says:

  ከመካከላች ሁ ማንም ወንድሙን የሚያስት ቢኖር የወፍጮ መጅ አንገቱ ላይ ታስሮ ባህር ቢጠልቅ ይሻለዋል።በኔ እይታ አካፋን አካፋ ብየ አልፈው ነበር፣በጣም የሚገርመው ነገርና ገሃድ ሊወጣ የሚገጋው መስጢር የሚድያ ሽፋን ባገርዎ ምድር ላይ ባለመሰጠቱ፣የርስዎንም አስተያየትና መልስ በማናይበት ሁኔታ፣በዙ ይባላል፣ምሳሌ ትናንት ቅዳሜ ሰባት ሰዐት ላይ የ ኤፍ ኤም አዲሱ ዘነበ ወላም ቢሆን፣እንዲህ ነው የሆነው፣ለኔ ደስ ያለኝ ርስዎ በመጻፍዎ ብዙውን ኮርኩረዋልና ገና ብዙ እንጠብቃለንግን ግን፣መቸውን ም ቢሆን ሁሉንም ተማሪ ማሳመን ስለማይቻል፣ለሚገባው ብቻ ውጤት ይስጡ።እንፈልጎታለን እኛ ማለፊያ መጽሃፍ ነው።ከቻፊዎቹም እንዲሁ፣ለአቶዳንኤል እባክዎ እየተናደች ያለችዋን ቤተ ክርስቲያን ከቀይአፋዊ ፍርድ ትወጣ ዘንድ ጸልዩለት፣የጻፍ። ጤና ይስጥዎ።

 19. Gomej says:

  I have read Daniel’s commentary and your response. I discussed with my friends in detail about it. In my view, you have done a wonderful job to give him and other tiraz-netekoch a good lesson. Whatever, the followers of Daniel say, we know you alliance is with truth. That is what we all value. Leave the opportunists bark like a dog, as you rightly put it, they are in the darkness of ignorance.

  Egzabher edmewon yarzimilin. egnam bizu enamaralen kersewo. God bles you, Prof.

 20. Wellabu G. says:

  Ato Mesfin!
  Stop barking!

 21. gedewon admassu says:

  Interesting

 22. geezonline says:

  “የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከፈትሁና የማውቀውን ነገረኝ፤ — የተካነ፣ ምሥጢር ያየ፤ ቀዳሽ — የሚል፤ በዚህ መስፈርት እኔም ዱሮ ዲያቆን ነበርሁ…”

  ርስዎማ እንዲህ የጸና መሠረት ስላለዎ ነው ኢትዮጵያዊእነት፥ ሰብእናም እንጂ—ፈርጡ—ምን እንደኾነ በትምርትም በተግባርም ወለል አድርገው እያሳዩን ያሉት። ይኹንና የዲ/ን ነገር እንዲህ ነው፦ ማርክሲስቶቹ ሃይማኖትን ሲያጣጥሉ የዲቁናና ቅስና ተግባር በመናቁ ማዕርጉን የያዙት ሲያፍሩበት ያዩ የኔ ቢጤ ዘመናውያን፤ ክህነትን እናስከብራለን በሚል “ያላባት ያለመጣፍ”ም ቢኾን በየቦታው የሚጠሩበት ዐዲስ ባህል ኾኗል። አጀማመሩ በቅንነት ነበር። አኹን ግን…

  አዬ ረ የዲያቆኑ ባልከፋ ውድ ፕሮፌሰር፤ በዚህ ዘመን’ኮ ከላይ እስከ ታች፦

  መምህራነ ኮኑ በበደወሉ
  ፊደላተ ዘኈለቍ ኵሉ። [ወዘኢኈለቍም እንጂ!… ማጋነኔ አይደለም፤ እስኪ እነ “ኰ፥ ኵ፥ ኲ”ን የሚቆጥር ማን ነው?]

 23. Alem Ashebr says:

  Ato Pro Mesfin, you wrote your personal dream. Look—— you r called Professor, senior (aged), Hstorian, But still you are licking with one tinny book. Please tell our people the right history. leave about Menellik, Yohannes …write about the three Governments which you have been working with them, specially you were the KEY person of Mengistu (look your videos posted in youtube). why are you afraid of saying I made a big mistake working with Mengistu,…..If you want to say the truth should be called truth. SO DON’T POISON OUR NEW GENERATION!!! why makes you scarey hearing Muslims or christian protest or oppositions??? you said this constitution is HIGE ARAWIT. I made you down my shoes when you said Hige Arawit. If this is called hige arawit, what about the constitution you were using with Mengstu??? TELL us please. so made a confession to your people & then write like senior historian.

  • Habtamu Getahun says:

   DEAR the protectorate of the constitution why you say here and their around the bush u act like that bull shit Mengistu H/Mariam first of all give your confession as u r pure woyane . Following your blind head Master Daniel you also forwarded an allegation without any credible evidence by citing you tube which is so circumstantial and which can be edited at any time. if u know history for yr reference the constitution which was used by Mengistu was formulated and written by . Fasil Nahom who is Man of all time and who is the known prostitute intellect. then pls utilize your intelligence think twice before you shout loud one’s ለወደፊቱ ይጠቅመዎታል

 24. elias says:

  @Anteneh (ዳንኤል) ምን አናደደህ ታድያ ?

  • Anteneh says:

   ብዙ ነገር የምጠብቅባቸው ፕሮፌሰሩ ስራ እንዳጣ ሠው ሁለት ጊዜ ዳንኤልን ለመሳደብ (ከተገባውም በግሉ በመከሩት) ትልቅ ጉዳይ አድርገው ለዚህ ሲተጉብኝ ጊዜ ነዋ! ይሄ ጽሁፍ እኮ በየጊዜው የሳቸውን ቁምነገር ፈልገን ለምንመጣው ሠዎች ፋይዳ ቢስ ዘለፋ ብቻ ነው የያዘው!! የታል ቁምነገሩ?? ለዛ ነው!!

   • elias says:

    ማንበብ ለሚችል እያንዳንዷ መስመር በቁም ነገር የተሞላች ነች እንዲህ ዓይነት ጽሁፎችን ልመዱ እንጂ ወይስ ገና ሌላ ሺህ ዓመታት ያስፈልጋል? ደብተራንም አታሰድቡ እንጂ (ወርቄም እኮ ደብተራ ነበረ )! በግሉ በመከሩት የሚትለዉ የግል ጉዳይ አስመሰልከዉ አቶ ዳንኤል ባደባባይ ‘ጨዋነቱን’ እኮ አስመሰከረ ስለማያቀዉ ተናገረ እና ሚስጥር አደረገ ባደባባይ ካልጻፈዉ ልክ እንደሳችዉ እንዴት ማወቅ እንችላለን ? ልብ ዉስጥ ያለዉን ማንበቢያ በሳይንሱ እስካሁን አልተሰራም በድብትርናዉ እንዳለ አላዉቅም ስለዚህ ኢንተርኔት ተገኘ ተብሎ ዝም ብሎ ከመንጫጫት ሰከን ብሎ ማሰብ እና ፕ/ር ምን ለማለት ፈልገዉ ነው? ምክንያታችዉ ምንድር ነው ብሎ መመርመር መጠየቅ ያስፈልጋል እንዴ እያሰብን እንጂ ወገን ጋሽ መስፍን እኮ ከ14 በላይ በምርምር ላይ የተመረኮዘ ዕዉቀት ጠገብ መጽሃፍትን ለኛ ለሚወዱን ኢትዮጵያዉያን አበርክተዋል አሁንም አልሰነፉም እየለፉ ነዉ አመስግኑኝ ባይሉም በጠብ የለሽ በዳቦ ልንወርፋቸዉ አይገባም አሳዳጊዎቻችን እና የቆምንበትን የስነ ምግባር መርህ አያሳየን ይመስላል እኛ ለሃገራችን ምን አበረከትን አንተን ጨምሮ ? ይህንንም መጠየቅ ያስፈልጋል ለራስ
    እሳቸዉ እኮ ስለ ልማት ስለ ርሃብ ስለ ግጭት ስለ ባህል የመሳሰሉትን ስራዬ ብለው ያገባኛል ብለው አዉሮፓ እና አሜሪካ ቁጭ ሳይሉ እዚሁ ህመሙንም አብረዉ እየታመሙ አጥንተዉ እነሆ በረከት ብለዉናል! ሊገባን ይገባል ሊሰማን ይገባል ስለ ልፋታቸዉ ቢያንስ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅብዎ ብቻ እንኳ ብንል ይበቃል ኧረ እኛ ምን ጉዶች እንደሆንን አይገባኝም ያደለዉ ሙሁሮቹን አቀማጥሎ ይይዛል እኛ ደግሞ ያሉንን ለምን ብቅ አሉ እያልን እንጨፈጭፋለን እንሰድባለን እናንጓጥጣለን ያሳዝናል በጣም ያሳዝናል አቶ አንተነህ ልብ ካለህ ልብ በል የጭቃ ጅራፍህን እዛዉ ከ እኩዮችህ ጋር አድርገዉ!

 25. Judiath says:

  የተከበሩ ፕሮፌሰር፣ ዳንኤል ክብረት በርሶ መጽሐፍ ላይ ያቀረበዉን ሒስ ተከትሎ የጻፉዋቸዉን ሁለት ተከታታይ ጽሁፎች አነበብኩዋቸዉ። ከጽሁፎቹ የቀሰምኩት ይህ ነዉ የሚባል ቁም ነገር ፈልጌ ፈልጌ ምንም ላገኝ አልቻልኩም። ምክንያቱ ደግሞ ጽሁፎቹ፣ ከቁም ነገር ይልቅ ዘለፋና ስድብ የሚበዛባቸዉ እንቶ ፈንቶዎች በመሆናቸዉ ነዉ። ይሄ የአሁኑ ጽሁፍ እንኩዋን የመጀመሪያዎቹን ሶስትና አራት አንቀፅ በዳንኤል ወይም እርሶ “ጭፍሮች” ባሉዋቸዉ ግለሰቦች በተነሱ ጭብቶች ላይ ምንም ያሉት ነገር የለም። ከስድቡ ቀነስ አድርገዉ ከወደ ቁም ነገሩ ቢበረቱ፣ እንዴት መልካም በሆነ።

  • tom says:

   ወንድም አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ይባላል:: ለነገሩ እንዳንተ አይነቱ እኮ ቁም ነገር ማለት ምን ማለት እንደሆን አልገባህም በመጀመሪያ
   1ኛ መጽሐፉን አንብበው
   2ኛ የዳንኤልን አስተያየት አንብበው
   3ኛ የፕ/ር መስፍንን መልስ አንብብ (በዛውም የተሰጣቸውን አስተያየት(comment) አንብብ)
   4ኛ ይሄን ጽሑፍ አንብብ(በዛውም ለማን እንደተጻፈ እና ለምን እንደተጻፈ ተረዳ)
   በተጨማሪም ስድብ ነው ያልከውን የቱ እንደሆነ ተናገር
   እስኪ ማንበብ ከቻልክ መጽሀፉን እያቃጠለህም ቢሆን አንብበዉ ከዚያ በኋላ ህሊና ካለህ ቁም ነገር ታገኛለህ :: በርግጠኝነት ግን ይህንን አስተያየት የሰጠህዉ ጓደኛህ ሲያወራ ለዳንኤል ተቆርቁረህ ነው እንጂ መጽሀፉንን አንብበህ ሂስ ለመስጠት አይመስለኝም::

  • loveethio1 says:

   ወንድም አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ይባላል:: ለነገሩ እንዳንተ አይነቱ እኮ ቁም ነገር ማለት ምን ማለት እንደሆን አልገባህም በመጀመሪያ
   1ኛ መጽሐፉን አንብበው
   2ኛ የዳንኤልን አስተያየት አንብበው
   3ኛ የፕ/ር መስፍንን መልስ አንብብ (በዛውም የተሰጣቸውን አስተያየት(comment) አንብብ)
   4ኛ ይሄን ጽሑፍ አንብብ(በዛውም ለማን እንደተጻፈ እና ለምን እንደተጻፈ ተረዳ)
   በተጨማሪም ስድብ ነው ያልከውን የቱ እንደሆነ ተናገር
   እስኪ ማንበብ ከቻልክ መጽሀፉን እያቃጠለህም ቢሆን አንብበዉ ከዚያ በኋላ ህሊና ካለህ ቁም ነገር ታገኛለህ :: በርግጠኝነት ግን ይህንን አስተያየት የሰጠህዉ ጓደኛህ ሲያወራ ለዳንኤል ተቆርቁረህ ነው እንጂ መጽሀፉንን አንብበህ ሂስ ለመስጠት አይመስለኝም::

  • elias says:

   ጥያቄ ልጠይቅሽ ዋናዉ ቁምነገር እሱ በመሆኑ ለመሆኑ መጽሃፋቸዉን አንብበሽዋል? ከተቻለሽ አስተያየት ከመስጠትሽ በፊት መጽሃፉን አንብበሽ ወደ አስተያየቱ ብትገቢ የተሻለ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ!

 26. elias says:

  እርስዎ ለእኛ እዉቀትን መንገድ ለማሳየት ሁሌ እንደጣሩ ነዉ ለእኔ የምንግዜም አርአያዬ ኖት እርሶም ስለ እዉቀት ደብተራዉም ለመክፈልት

 27. Anteneh says:

  በጨዋ አንደበት ቢነገርዎትም ይገባዎታል ብየ በማሠብ ይችን አስተያየት ላንሳ!

  አሁንም ቢሆን ይህን አተካራ ለመጻፍ መትጋትዎ ገርሞኛል! ይሄኔ ሌላው የዳንኤል ጭፍራ ብለውኛል – እንደ አምባገነኑ TPLF ሲመዳድቡኝ:: ካላሉም ደግ! ነገር ግን ለምን ጉዳዮን ሁለት ጊዜ ጻፉበት, ፕሮፌሰር?? ባለፈው ከጻፉት የተለየ ነገር ዛሬ አላነበብኩም:: ግን ለምን? ናቅ ያረጉት የመሠለኝ ዳንኤል እኮ ምንም ሲል አልተሠማም:: በእውነት እሱ ያላከበረዎት እንኳን ቢሆን እርስዎም አንባቢዎችዎትን የማንፈልገውን እና የማይጠቅመንን ጉዳይ (ለምሳሌ ለእኔ) አንስተው ሁለት ጊዜ በማድረቅዎትና አስተያየት ሠጭዎችንም እንደ ‘ጭፍራና’ የራሳቸው ሃሳብ የሌላቸው ‘ሎሌዎች’ (አይሻልዎትም ‘አሸባሪዎች’?) አርገው በማሰብዎት ያከበሩን አይመስልም:: በእውነት ሙድ የለውም!! ዛሬም ተሳሳቱ!

  ስለ ዲቁና ማዕረግ ሊያብራሩ የሞከሩት አልገባኝም:: የገባው ሠው አስተያየት ከሰጠ እከታተላለሁ!! ሌላው ‘የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ማምለጫና መብለጫ’ ብለው ያነሡት ነጥብ አስቀያሚና ጭፍን ማጠቃለያ ስለሚመስል ቢያንስ ‘አንዳንድ’ የሚል ቃል ከፊቱ ይጨምሩበት! አሉ እኮ በየቦታው ሲበልጡም፣ ሲበለጡም ሲያሸንፉም፣ ሲሸነፉም ሲተቹም፣ ሲተቹም የሚያውቁበትና የሚመቹ!!

  ሌላው ደሞ ዳንኤልን የተቹበት ስሜት እና ትኩረት ብቻ አስተያየት ለመስጠት ያስችላል ባይ ነኝ:: መጽሃፍዎን ያላነበብነውን አያሳቅቁን!!

  በርቱልኝ, ፕሮፌሠር!!

  • Habtamu Getahun says:

   Antenehe እኛ እያልክ እምቡር የምትለው እናንተ እነማን ናችሁ የዳንኤል አምላኪነታችሁ በድርጅት ነው እንዴ ወይንስ እራስህን መሆን አትችልም
   እውቀት አልቀሰምኩም አልክ ማን እውቀት ቅሰም አለህ አንብበሀል መዝንና ሀሳብህን ስጥ እንጅ እውቀት ለመቅሰም እኮ መጀመሪያ የድብትርና አባዜን ማስወገድ ያሻል ድብትርና ሽምደዳ እና ማነብነብ ስለሚበዛው ማለት ልክ እንደ ዳንኤል
   ደግሞ በጨው ነው በጨዋ አንደበት ነው እያልክ ያለከኽው ጨዋነት ሆይ ወዴት ነሽ
   የኔታ እግዚሐብሔር ጤናዎትን ጠብቆ ያቆይልኝ

   • Anteneh says:

    ግልጽ ካልነበረ ‘እኛ’ ያልኩት እንኳን የእርሳቸውን ጽሁፍ ለመከታተል ድረ-ገጻቸው ላይ የምንመጣውን ወገኖችን ነው:: ሆኖም በሁላችንም ስም ‘እምቡር’ ያልኩት ነገር አልነበረም::

    ደብተራነትን እንዳንት ባላንጓጥጥም እኔ ግን ደብተራ አይደለሁም:: ይሄ እኮ ነው ችግሩ, በራሳችን ባዶ ግምት እና ትንሽ እውቀት ሰዎችን/ስራዎችን የሆነ ስም እንለጥፍባቸዋለን:: የሠዎችን ሃሳብ ከመረዳትና ከመሞገት ባለፈ የሆነ ቡድን ጭፍን ደጋፊ አርገን እንቆጥራለን, ከዛም ስድብ ጥላቻ ንቀት ይወረናል!! መሻሻል አለብን, ጎበዝ! ….ያው እንዲህ እያልን!!

    ቸር ይሠንብቱልኝ ጌትዬ!!

  • Engdawork Tadesse says:

   Antneh tinish atafrim. Akafan akafa kalalut yetebalewu eko le ende ante ayinetu choma ras newu. Endewu tinish ayikebdihim sataneb asteyayet mestetih. Yihe yigermhal Alawaki yamayaneb edme likun yisakekal.

  • jhon says:

   ወንድም አንትነህ መጀመሪያ
   1ኛ መጽሐፉን አንብበው
   2ኛ የዳንኤልን አስተያየት አንብበው
   3ኛ የፕ/ር መስፍንን መልስ አንብብ (በዛውም የተሰጣቸውን አስተያየት(comment) አንብብ)
   4ኛ ይሄን ጽሑፍ አንብብ(በዛውም ለማን እንደተጻፈ እና ለምን እንደተጻፈ ተረዳ)
   በተጨማሪም ስድብ ነው ያልከውን የቱ እንደሆነ ተናገር

 28. Kiyya says:

  ያሁኑ ይባስ

 29. Habtamu Getahun says:

  የራሴን ግንዛቤ ላስቀምጥ አሁንም እርግጠኛ ነኝ ዳንኤል ቅርንጫፉ ላይ ነው ያለው መጽሀፉን ስለማንበቡ እርግጠኛ ለመሆን ይከብደኛል ምክንያት ጽሁፉ ላይ የዘባረቀው በጠቅላላ የግል ቅዠት እንጅ እተቻለሁ ከሚል ምክንያታዊ ሰው የተጻፈ አይመስለኝም ሌላው ዳንኤል በእውር ድንብር ሰው ወነጀለ የሚያውቀው ነገር ካለው እኛ አንባቢዎች ሳይጨንቀን ስለቤተ መንግስቱ ያወራውን ለምን አላብራራውም ሲቀጥል ሀይማኖት እምነት እና ሞራልን እንዴት እና በምን እንዳገናኛቸው ለማስረዳት ዳንኤል እንደ ጨቅላ ህጻን ሲያምቧች ተመልክቻለሁ ለዚያውም በዶለዶመ ብዕር እና ማጠልሸትን ዓላማው ባደረገ ሁኔታ
  ወጣም ወረደም ዳንኤል እንደ ለማጅ ዋናተኛ ለተንቦራጨቀበት ጽሁፍ አጭር እና ግልጽ መልስ ተሰጦታል ያውም የተከሸነ በተራ ቁጥርም የተሰደረ እሚለው ካለው ላንብብ ከዚያ ቀጥሎ መመዘን የራሴ ፋንታ ጋሼ መስፍን ከተሳሳቱ ተሳሳቱ ለማለት ምን አስፈርቶኝ ራሳቸው ያስተማሩኝን መጠየቅ መመርመር ሲሳሳት ተሳሳትክ ማለት ለእኔ አይሰራም እንደማይሉ በእርግጠኝነት አውቃለሁ እናም የኔታንም ለመተቸት እኔ ችግር የለብኝም
  ሳሳርግ አሁንም ዳንኤል ትችትህ እና ውንጀላህ ውሃ አላነሳልኝም ስለዚህ ያስቀረኽውን ጨርሰህ ተናገረው እና ፍርዱን ለኛ ብተወው

Comments are closed.