https://www.facebook.com/pages/Prof-Mesfin-Woldemariam/120300297984572?ref=stream

It is becoming clearer everyday that Ethiopia is less livable. What I experienced yesterday at Wabi Shebelle Hotel is very similar to what happened to me in 1956 in Knoxville, Ten.. I could never have imagined that a large number of Ethiopians who have paid for dinner would be denied entry into the dining room, simply because they have a different political conviction.
The owner of the hotel took the responsibility for violation of our rights. His reason interesting, it is the same reason that the President of Ethiopia gives, with an authentic sense of humour, for not being able stand up — technical!

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

4 Responses to

 1. dereje says:

  (አንድ አድርገን መጋቢት 5 2005 ዓ.ም)፡- በዚህ ሰሞን የብዙዎች መነጋገሪያ ከሆነው ጉዳይ ውስጥ የዲ/ን ዳንኤልና የፕሮፌሰር መስፍን ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ፕሮፌሰሩ በ83 እድሜ ዘመናቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያዩትንና ያስተዋሉትን በመጽሀፍ መልክ ለንባብ አብቅተዋል ፡፡ ዲ/ን ዳንኤልም ፕሮፌሰሩ የጻፉት መጽሀፍን በራሱ እይታ ተችቷል ፡፡ ይህ ጽሁፍ መጻፉ ፤ ለሂስ መቅረቡና ሰዎች የራሳቸው አስተያየት መስጠታቸው ተገቢ ቢሆንም ጥቂት አስተያየት ሰጪዎችና ሂስ አቅራቢዎች “ዲያቆን” የሚለውን ማዕረግ ከየት እንደተገኝ ፤ ለዲ/ን ዳንኤል ማን እንደሰጠው ያላስተዋሉ የፕሮፌሰሩን ወይም የዲ/ን ዳንኤልን ሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ወደ ሰዎቹ ማዕረግ እና ስብዕና ላይ ያተኮረ አስተያየት ሲሰጡ ተስተውሏል ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍንም የፕሮፌሰርነትን መአረግ ከመሬት ወድቆ እንዳላገኙት ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም የዲያቆንነት ማዕረግ ዝም ብሎ አይሰጥም ፡፡ ትንሽ ቢመስል ዋጋ ተከፍሎበታል ፡፡ ቤተክርስቲያን ለአንድ አገልጋይ የምትሰጠውን ማዕረግ አንቋሾ ፤ አውርዶ ፤ እንደማይገባው አድርጎ አስተያየት መስጠት “ባለቤቱን(ማዕረግ ሰጪውን) ካልናቁ ….” ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ሰው ስለ ዲ/ን ዳንኤል በሰጠው አስተያየት ላይ የፈለገው ማለት ይችላል ፤ ማዕረጉን ግን ከፍ ዝቅ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም ፡፡ ለማንኛውም የዲ/ን ዳንኤል አስተያየትን በአንባቢያ ጥያቄ መሰረት ከላይፍ መጽሄት ላይ በመውሰድ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

  ላይፍ፡- በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በብሔራዊ ቲያትር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ባዘጋጁት ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በተሰኝ መጽሀፍ ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡ በውይይቱ ግምገማቸውን ከሚያቀርቡ ሰዎች አንተ አንዱ ስለመሆንህ ተነግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን በእለቱ በስፍራው አልተገኝህም፡፡ ምክንያትህ ምንድነው ነበር ?

  ዲ/ን ዳንኤል፡- ይህንን ነገር ካነሳህው እናውራው፡፡ መቼም አንድ ፕሮግራም መጋበዝህ ለሦስተኛ ወገን ከመነገሩ በፊት የአንተ ፈቃደኝነት ይጠየቃል፡፡ ፕሮግራምህ እንዴት ነው? በዚያ ወቅት ነጻ ነህ ወይ ? አገር ውስጥ ትኖራለህ? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን ለእኔ አልተደረጉም፡፡ ስለ ፕሮግራሙ መጀመሪያ ደውሎ የነገረኝ ብርሀኑ ደቦጭ ነበር፡፡ እሱም ያለኝ “በፕሮፌሰሩ መጽሀፍ ዙሪያ ውይይት ተዘጋጅቷል ከቻልክ ሄደን የሚደረገው ነገር እንመለከታለን” ነው ያለን፡፡ ከዚህ ውጪ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ አርብ እለት አንድ ሰው ከአሜሪካ ደውሎ “በውይይቱ ላይ የምታቀርበውን የመጽሐፍ ግምገማ ቀድተህ ላክልኝ” አለኝ፡፡ እኔ እኮ አልተጋበዝኩም አልኩት ፤ “ኧረ ተው መጋበዝህን ከፌስ ቡክ ላይ አይቼ ነው የደወልኩልህ” አለኝ ፤ እኔም “እስኪ ላከውና እኔም ልየው” አልኩት፡፡ እኔም በፕሮግራሙ ጥናት አቅራቢ መሆኔን ከፌስ ቡክ ላይ ተመለከትኩኝ፡፡ ቅዳሜ ቀን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ስሜ ወጥቶ አየሁትኝ፡፡ የዚያን እለት የፕሮግራም አዘጋጅ ነኝ ያለ ሰው ስልክ ደውሎ ‹‹ነገ ጽሁፍ ታቀርባለህ›› አለኝ፡፡ እኔም “እንዴት ያለ እኔ ፍቃድ ስሜን በጋዜጣ በማውጣት ፈቃደኝነቴን ዝግጁነቴን ባልተጠየኩበት ሁኔታ ፕሮግራም ትይዛላችሁ?” ስለው ብርሀኑ ደቦጭ አልነገረህም እንዴ አለኝ፡፡ ብርሀኑ ከእኔ ውጪ ከሶስተኛ ወገን ከመስማቱ ውጪ መጽሀፉን በመገምገም እንደምናቀርብ የሚያውቀው ነገር እንዳልነበረ መጀመሪያ በደወለልኝ ቀን ከነገረኝ ነገር በመነሳት ከማወቄ ውጪ ብርሀኑ ከዚህ ወዲህ አልደወለልኝም፡፡ ሰማያዊ የሚባል ፓርቲ የዝግጅቱ አዘጋጅ መሆኑን ያወኩት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ መቼም አንድ ፓርቲ ሰውን ሲጋብዝ በይፋ የፓርቲው ማህተብ በማስፈር እንዴት ደብዳቤ እንዲደርስ አያደርግም? ለአንድ ሰው መብት መከበር እታገላለሁ የሚል ፓርቲስ ያልጋበዘውን ሰው እንዴት እከሌ በፕሮግራሙ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀርባል በማለት በጋዜጣ ያስነግራል? ለእኔ ነገሩ በጣም አስገራሚ ሆኖ አልፏል፡፡

  ላይፍ፡- ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በተሰኝው መጽሀፍ ዙሪያ በመጦመሪያ ብሎግህ ላይ የራስህን ግምገማ ካወጣህ በኋላ ፕሮፌሰሩን ጨምሮ የተለያዩ ምላሾች ተሰንዝሮብሀል፡፡ ነገር ግን እንዴት ጠጠር ከወረወርክ በኋላ በዝምታ መዋጥህ ብዙዎች ከመጀመሪያው አስተያየቱ ስህተት እንደሆነ በማወቁ ነው ይሉሀል?

  ዲ/ን ዳንኤል፡- በተሰጡት ምላሾች ዙሪያ ብዙ ነገር የምለው ነበረኝ፡፡ እሳቸው እንዳሉት ሳይሆን መጽሀፉን በደንብ አድርጌ አንብቤዋለሁ፡፡ እንኳን አነስተኛ የገጽ ብዛት ያለው መጽሀፍ ይቅርና ብዙ ሺህ ገጾች ያላቸው መጻሕፍት አነባለሁ፡፡ ከመጽሀፉ ያወጣኋቸው ሁለት ነገሮች ነበር፡፡ አንደኛ ታሪክ አይከሽፍም፡፡ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እኔ ይህን ቢሮ ለመስራት እቅድ ነበረኝ ፤ ነገር ግን አልሰራሁትም ከሸፈ፡፡ ይህ የቢሮ ክሽፈት ተብሎ ሊነገር አይችልም፡፡ ክሽፈቱ የዳንኤል ቢሮ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ታሪክ ከሸፈ ሊባል አይቻልም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ የተጻፈው ብቻ አይደለም ፤ ያልተጻፈ ብዙ ታሪክ አለ ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የክሽፈት ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እኮ የአክሱም ስልጣኔ ፤ የላልይበላ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡

  ሌሎቹ ፕሮፌሰሩ የጠቀሷቸው የታሪክ መጻሕፍት ናቸው፡፡ የታሪክ ጸሀፍቱ መጻህፍቱን ከጻፏቸው 41 ዓመታት ያህል ተቆጥረዋል፡፡ ፕሮፌሰር መርዕድ ሲሞቱ ፤ ፕሮፌሰር ታደሰ አልጋ ላይ ሲውሉ ጠብቆ የእነሱ ስራ ላይ ሂስ ማቅረብ ተገቢ ነው? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ለዓመታት አብረው የነበሩ ሰው ጊዜ ጠብቀው ይህን ማድረጋቸው በእኔ አስተያየት ትክክል አይደለም፡፡ ፕሮፌሰሩ መጽሀፍቱን በደርግ ዘመን ነው ያዘጋጀሁት በማለት በብሔራዊ ቴአትር መናገራቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡መጽሐፉን ለማሳተም ሳንሱር ቢያስቸግራቸው እንኳን የጥናት ወረቀቶቹን በተለያዩ መድረኮች በማቅረብ እነ ታደሰን መሞገት ይችሉ ነበር፡፡ ደርግ እኮ ከወደቀ 21 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ታዲያ ለምን ከደርግ ውድቀት በኋላ መጽሀፉን ሳያሳትሙት ቆዩ? መስፍን በቁጣ ስሜት ለኔ መልስ በማለት የጻፉት ጽሁፍ ምላሽ ያልሰጠሁት አንደኛ ለእሳቸው አክብሮት ስላለኝ ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም በዚች ሀገር ታሪክ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል፡፡ በዚህ ላይ በአደባባይ ከሚናገሩ ጥቂት ምሁራን አንዱ መሆናቸውን ከግምት በመክተት ነገሩን በዝምታ ማለፍ መርጫለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለፕሮፌሰሩ ምንም ምላሽ አትስጥ በማለት ምክራቸውን ለግሰውኛል፡፡

  ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ በዋናነት “ቤተ መንግሥቱን” አየሁት በማለት በሰጠህው ምስክርነት ተበሳጭተዋል፡፡ የማላውቀውን ዶክተር በመጥቀስ ነገሩን ሌላ ትርጉም እንዲይዝ አድርጓል ብለዋል፡፡

  ዲ/ን ዳንኤል፡- የጠቀስኩትን ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቁት ስድስት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከስድስቱ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት ፕሮፌሰሩና መንግስቱ ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡ የዶክተሩን ስም መጥቀስ ያልፈለኩት ዶክተሩ በህይወት ስለሌሉ ነው፡፡ ይህንን መናገር ድብትርና የሚል ትርጓሜ አያሰጥም፡፡ እኔ ለድብትርና አልበቃሁም፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የጻፈውን ካነበባችሁ ድብትርና ትልቅ ማዕረግ መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ሹመት የሚሰጡ በሆኑና በተቀበልኳቸው ደስታውን አልችለውም፡፡

  ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ “ታሪክ ከሽፏል” ካሉባቸው ነጥቦች አንዱ የአገሪቱ የስኬት ታሪክ መቀጠል ባለመቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ የአክሱም ሃውልትና የላበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት የሰራ ህዝብ እንዴት በደሳሳ ጎጆ ይኖራል ? ይላሉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝቤን አላወግዝም በማለት ራሳቸውን ለጥይት የሰጡላት አገር እንዴት ጠዋት የሚናገሩትን ለማታ መድገም የማይችሉ አባቶችን ታፈራለች ? በማለት ክሽፈቱ በሁሉም የታሪክ አውድ መኖሩን በመጥቀስ ይሟገታሉ፡፡

  ዲ/ን ዳንኤል፡- የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ በሚደረግ ጥናት የሚደረስበትና ከሽፏል የምንለው አይደለም፡፡ የአክሱም ሀውልት ወይም የአቡነ ጴጥሮስን አይነት የሞራል አርአያ ማጣታችን የታሪካችን ቁንጽል አካል ነው፡፡ ይህንን በማንሳት ብቻ ታሪካችንን ከሽፏል ማለት ተገቢ አይደለም፡፡

  ላይፍ፡- ፕሮፌሰር መስፍን እኮ አንድ ያልከሸፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ለማግኝት አልቻልኩም ነው ያሉት?

  ዲ/ን ዳንኤል፡- አልፈለጉም፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ እንደማትጨርሰው ተነጋግረናል፡፡ ምናልባት የምናውቀው የመካከለኛውንና የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ያልተዳሰሱ ጉዳዮች ደግሞ አሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በምልአት ዛሬ ልትናገር አትችልም፡፡ በነገራችን ላይ እንደ ባለሙያ ሁሌም መጠንቀቅ ያለብን ስለ አንድ ነገር በምልአት ልታውቅም ልትደርስበትም አትችልም፡፡ ስለዚህ ይመስለኛል ፤ ሊሆን ይችላል ፤ እገምታለሁ ትላለህ እንጂ እርግጠኛ ልትለው የምትችለው ነገር በጭራሽ የለም፡፡ ያውም እንደ ኢትዮጵያዊነት ውስብስብ በጣም ብዙ ባህሎች ያሉት ህዝብን በዛ ደረጃ ማስቀመጥ ትክክል አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረድቼዋለሁ የማትለው ልዩ ሕዝብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ በቃ ጨርሷል ስትል ብድግ የሚል ፤ ተኝቷል ስትለው የሚነሳ ፤ ከ1997 ዓ.ም በፊት የነበረውን 97 ላይ ለምንድነው ብድግ ያለው? ለሚለው እንኳን ተንትኖ የሚነግርህ የለም::

 2. abdu says:

  shameful!

 3. yohannes M says:

  ፕሮፌሰር የሚለውን የትምህርት ደረጃ ማዕረግ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ የማውቀው የእርስዎን ስም በየሚዲያው ስሰማ ነበር፡፡ በተለይ በ80ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ይታተሙ በነበሩ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይ ሃሳበዎን በድፍረት እና በትጋት ያካፍሉ ስለነበር ከእርስዎ ጋር የተደረጉ ቃለመጠይቆች እና የመሳሰሉትን ለማንበብ እድሉ ነበረኝ፡፡ የምስማማባቸውን ሃሳቦችዎንና አስተያየቶችዎን እንደማደንቅልዎት ሁሉ የማልስማማባቸውን አስተያየቶች እና ሃሳቦችዎንም ሳከብርልዎት ኖሬያለሁ፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ የአደባባይ ሙሁራኖቻችን (ዳንኤል እንዳለው) አንዱ መሆንዎን ሁልጊዜም ቢሆን በአክብሮት አስታውሳለሁ፡፡
  የዚህ አስተያየት ምክንያት የሆነውን መጽሐፍዎን በሚገባ አንብቤዋለሁ (አላነበብከውም ! ደንቆሮ፣ ውሸታም… ካላሉኝ) መጽሐፍዎን በተመለከተ ዳንኤል ክብረት (ዲያቆን ያላልኩት እንደእርስዎ በመገበዝ ማእረጉ አይገባውም በሚል ሳይሆን እርሱም ከስሜ በፊት ማዕረጌን ቀጽላችሁ ካልጠራችሁኝ ብሎ ስላማያውቅ ነው) የሰነዘረውን አጭር አስተያየትም በደንብ አንብቤዋለሁ ! በእውነት አንብቤዋለሁ ! እርስዎ የተከበሩት ፕሮፌሰር ለዳንኤል የጻፉት መልስ ግን በእውነት እጅግ ጨዋነት የጎደለው፣ በተለይ ከእርሰዎ የማልጠብቀው ስለነበር ከልብ አዝኜብዎታለሁ፡፡ ስድብ የተቀላቀለበት በሰከነ አእምሮ ያልተጻፈ ብቻ ሳይሆን የእርስዎን አዋቂነት በዳንኤል አላዋቂነት ለማስመስከር የሚሞከረ ነበር የሚመስለው፡፡ (ዳንኤል እርስዎ እንዳዋረዱት አላዋቂ ነው ብዬ ብቀልቀበልልዎት )
  የአሁኑ ይባስ ! አሁን ደግሞ የጭቃ ጅራፍዎ ከዳንኤል ወደ የዋሃን አስተያየት ሰጪዎች ዞሮ ‹‹ ጭፍራዎች ›› ከሚል ቅጽል ጋር በጅምላ መናጆ ሆነው ተዋርደዋል፡፡ ምነው የተከበሩ ኣባቴ ! እንደው ትንሽ አልከበደዎትም ወይንስ ከስምዎ የቀደመው ማዕረግዎ እና ዕድሜዎ ከበደዎት እና ሰው ሁሉ ትንኝ መሰለብዎ ! አንድ ሰው ማዋረድ ፣ ማንኳሰስ ተገቢ አይደለም ብለው አስተያየት የሰጥዎትን ሁሉ ይግረማችሁ ብለው ‹‹የምን አንድ ሰው! እናንተስ ብትሆኑ›› ብለው በአንድ ሙቀጫ አስገብተው ወቀጧቸው !
  ከተሳሳትኩ እታረማለሁ እድሜዎ 82 ዓመት አካባቢ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ እድሜ ሲደረስ ትልቁ ዳቦ ሊጥ ይሆናል እንዴ ! ‹‹ካረጁ አይበጁ›› የሚለው የቆየው የማኅበረሰባችን ተረት በእርስዎ በኣባቴ እንዳይደርስብዎት እመኛለሁ ! የእኔ አዲወሱ ትውልድ (ዕድሜዬ 35 ነው) ከእናንተ ከአባቶቻችን ዘለፋን፣ ማዋረድን .. ሳይሆን ሃሳብን በሃሳብ መሞገትን፣ ሰውን ሁሉ ከነልዩነቱ ማክበርን፣ በሰከነ ሁኔታመነጋገርን መማር እንፈልጋለን፡፡ የምታስተምሩን ነገር ከሌላችሁ ግን የእስልምናው ቅዱስ ቁራን እንደሚለው ‹‹ ደግ ነገር መናገር ካቻልክ ዝም በል››

 4. netsanet says:

  sad to see! its quite intriguing to me to see the owner unable to defend his “reason” for not letting you in. its also amazing to see that the people (guests) unable make their voices heard coherently. (seems everybody wanted to speak so they talked over each other) was there any way of convincing the owner/hotel to let you dine…? maybe maybe not. but it would have been worthed to give the guy an ultimatum. all in all, its sad to see the situation in Ethiopia worsening with out a way out. that way out being a sound opposition party. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ..?!?!?!”

Comments are closed.