አንድ ፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

በአለፉት ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ እንደኢሳት (የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ) ያለ ኃይል የትኛውንም የኢትዮጵያ አገዛዝ አጋጥሞት አያውቅም፤ በመሠረቱ የኢሳት መሣሪያነት ከባህል ውጭ ቢሆንም የባህል ይዘት አለበት፤ ይህንን ወደኋላ አመለክታለሁ፤ ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ታሪክ በመሠረቱ ሁሌም በኃይል ላይ ቆሞ በኃይል የሚሽከረከር ነው፤ በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ የመጡት አብዮተኞች ሁሉ ይህንን በመሠረታዊነት የመክሸፍ ምንጭ የሆነውን የጉልበት አምልኮት እንደዓላማም እንደመሣሪያም ይዘው የተነሡ ናቸው፤ ዛሬም ቢሆን ተሸናፊዎችም ሆኑ አሸናፊዎች አብዮተኞች የሚያወሩትና የሚጽፉት ከጉልበተኛነት ከረጢታቸው ሳይወጡ ጥፋታቸውን እንደልማት፣ አላዋቂነታቸውን እንደብልህነት በማድረግ ራሳቸውን አታልለው ሌላውን ለማታለል እየሞከሩ ነው፤ አንድም የከሸፈ አብዮታዊ መሪ ያለጠዋሪ ልጅ የቀሩትን እናቶችና አባቶች፣ የብልጣብልጦች መሣሪያ ሆነው እንደወጡ የቀሩትን ወጣቶች በኃላፊነትን ተቀብሎ በእውነት የሚዘክራቸው የለም፤ እነዚያ በየሜዳው በጥይት ነደው ጅብና አሞራ የበላቸው ወጣቶች እንደማንም ሰው ሕይወትን ለማጣጣም የሚያስችሉ ሌሎች ዓላማዎች ነበሩአቸው፤ ዛሬ ‹‹መስዋእት ሆኑ›› እየተባለ ይነገርላቸዋል፤ ዶሮን ሲያታልሏት ዓይነት ነው፤ ይህንን የሚሉት የራሳቸውን ሕይወት እየሳሱለት ጠብቀው በሌሎች ሕይወት ጉልበተኞች ለመሆን የተመኙት ናቸው፤ በወጣቶቹ አጥንት ላይ ጉልበተኛነታቸውን የተከሉት አጥንቱ እየቆረቆራቸው ይባንናሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፤ በወጣቶቹ አጥንት ላይ ከአሜሪካ የመጣ ድርብርብ ፍራሽ ስላነጠፉበት አጥንቱ መኖሩንም አያስታውሱትም፤ ዛሬም የሚሳሱለትን ሕይወታቸውን በሰፊ ግምብና በታጠቁ ወጣቶች አጥር ይጠብቃሉ፤ በአንጻሩ በምኞት የቀሩት ከንፈራቸውን እየነከሱ ከጠርሙስ ጋር ይታገላሉ፤ ከምኞት ባርነት ወጥተው ለንስሐና ለነጻነት ገና አልበቁም፤ ለንስሐ ሳይበቁ የሞቱም አሉ፤ የመክሸፍ ክፉነት እውነትን ፊት-ለፊት የመጋፈጥ ወኔ ሳያገኙና ንስሐ ሳይገቡ ከነኃጢአት በወጣቶች ደም ተጨማልቆ መሞት ነው፤ የከሸፈውን እንዳልከሸፈ፣የከሰረውን እንዳልከሰረ፣ተሸንፎ የተንኮታኮተውን እንዳልተሸነፈ እያደረጉ የሬሳ ቀረርቶ ማሰማት የማይሰለቻቸው ሞልተዋል፤ ወደፊት መግፋት የሚቻለው ሬሳ ሬሳን ተሸክሞ ሳይሆን፣ ስሕተትን አርሞ የሞተውን ቀብሮ ነው።

በሃይማኖታዊ ቋንቋ ንስሐ አለመግባት ማለት ጥፋትንና ስሕተትን አለማመንና በቅብብሎሽ ለሚቀጥሉት ትውልዶች ማስተላለፍ ነው፤ ጥፋቱንና ስሕተቱን የማይቀበል ከነጥፋቱና ከነስሕተቱ ዕድሜውን ይጨርሳል፤ ለልጆቹም የሚያወርሰው ያንኑ ጥፋቱንና ስሕተቱን ነው፤ ዓይን ያለው ያያል፤ ይህንን የጥፋት ውርስና ቅርስ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ወስነን ካየነው ጉዳቱ በጣም የሚያንስ ይመስላል፤ በማኅበረሰብና በአገር ደረጃ ካየነው ግን ጉዳቱ ከባድ ነው፤ ከኋላችን የሚመጡት ሁሉ የሚቀድሙን በሌላ ምክንያት አይደለም፤ ከሃምሳና ስድሳ ዓመታት በፊት ከናይጂርያ፣ ከጋና፣ ከማላዊ፣ ከታንዛንያ፣ ከኬንያና ከኡጋንዳ እየመጡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሩ ወጣቶች ሁሉ በከፍተኛ ደረጃ አገሮቻቸውን ሲያገለግሉ ነበሩ፤ በኬንያ እንደሮበርት ኡኮ ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበረ፤ በታንዛንያ እንደጆርጅ ማጎምቤ ለብዙ ዘመናት በተለያዩ አገሮች አምባሳደር ነበር፤ በዚያን ዘመን ለነዚህ የአፍሪካ አገሮች የተረፈችው ኢትዮጵያ ዛሬ ከእነሱ በታች መሆንዋ ቆሞ ከመቅረት የመጣ ነው፤ ቆሞ መቅረቱ ደግሞ ስሕተትንና ጥፋትን እያዘሉና እሹሩሩ እያሉ ከመንከባከብ የሚመጣ ነው፤ እውነተኛ መልካችንን የምናይበት መስታዋት ሳይኖረን ብዙ ምዕተ-ዓመታት አለፉ፤ አቧራ ሲጠራቀም ከጊዜ ብዛት ተራራ ይሆናል፤ ትንሽ ጉድጓድ ከጊዜ ብዛት ረጅም ገደል ይሆናል፤ ትንሹ ቁስል ከዋለ ካደረ የቆላ ቁስል ይሆንና እንቅልፍ ይነሳል፤ በአንድ ቦታ ላይ አንድ እንቅፋት ደጋግሞ የሚመታው ሰው ረዳት ያስፈልገዋል፤ አለዚያ አንድ ቀን ያው እንቅፋቱ ይገድለዋል።

ኢሳት ለኢትዮጵያ አዲስና ኢትዮጵያዊ አብዮትን የሚያውጅ ይመስላል፤ እስከዛሬ አብዮት የምንለው ሁሉ የተለያዩ አገሮችን የታሪክ ውራጅ በግድ ኢትዮጵያን ለማልበስ የሚሞክር ነው፤ በ1967 ሶሺያሊዝም አዲሱ ሃይማኖት መሆን ሲጀምር በጎንደር በማኅበረ ሥላሴ ኅብረተሰባዊነት (ሶሺያሊዝም) አለ ብዬ ብናገር ውራጅ ሶሺያሊዝምን የሚያመልኩ ብዙ ዘለፋ አወረዱብኝ፤ አሁንም ቢሆን ውራጅ ከመዋስ ገና አልወጣንም፤ የልመና ስልቻችንን ተሸክመን አንዴ በአሜሪካ በር፣ አንዴ በሩስያ በር፣ አንዴ በቻይና በር ላይ እንቅለሰለሳለን፤ ልመና ባህል ነው፤ ለጌታ ማደርም ባህል ነው፤ ሆኖም ሁለቱም ዘዴዎች እድገትንና መሻሻልን አያመጡም፤ መሻሻልን የሚያመጡ ቢሆኑም የሚያስከትሉት ጉዳት ከሚሰጡት ጥቅም የበዛ ነው፤የሚገኘው ግዑዝ ጥቅም የአእምሮና የመንፈስ ውድቀትን በማስከተል ዋጋን ያስከፍላል፤ ይህ ሁሉ ጉዳይ በነጻነትና በሙሉ ልብ ክርክርን የሚጋብዝ ነው፤ ኢሳት ለዚህ ጥሩ መድረክ ሊሆን ይችላል፤ ይሆናል ለማለት ብችል ደስ ይለኝ ነበር።

ይቀጥላል—————–

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት. Bookmark the permalink.

11 Responses to አንድ ፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 1. Dan says:

  “የዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነውን የዶ/ር ብርሃኑ ደቦጭን ትችት ማግኘት ባለመቻላቸው ቅሬታ ያሰሙና ጥያቄ ያቀረቡ ጥቂት አይደሉም። እናመሰግናለን። ይህን ጥያቄ ለማስተናገድ ሲባል ጽሑፉን ፈልጎ በማዘጋጅት የረዱንን ግለሰብ እያመሰገንን ለሚገኝበት ግድፈት (ከተገኘ) በቅድሚያ ይቅርታ እንጠይቃለን። ጽሑፉ እነሆ፦” Pro. Mesfin

  Thank you for sharing with us. I could not comment on the relevant post. It seems you disabled it. And I would like to add one more point. Dear Prof., as much as I enjoy reading your posts, I’m sometimes getting disappointed with some of your discourses. Of course, I don’t expect all your essays to please me. But there are some works that I would never expect from you, such as the discouses you had with Daniel et al. and Aboy Sibhat. While I appreciate your humbleness as to come out publicly and fight against ignorance openly, I, and many other young fellows, do not like seeing you “degrading” yourself to the levels of Aboy sibhat and “Ye Daniel chifroch”. I have the feeling that you became a bit biased (“zeregna”), in writting “Mekshif” due to the discourse you had with Aboy Sibhat. I might be wrong, but that’s my feeling. I have also the feeling that you are too defensive. Dear Pro., don’t you think that being too defensive is one of the reason for our “Mekshef”. As much as you are enlightening us with your deep knowledge, we would expect you also to show us few more exemplary manners. What would cost you if sometimes you deliberatly admit some critics openly? It does not mean you are submissive, but that deliberate practice would convey tones of message to your fellows. Do we have to expect some “kifu kens” to get the most out of you? I expect another “Agetuni” from my enlightened, albeit somehow emotional, professor.

  Best,

  (Pls, you don’t have to post this. But, of course, if you want you can do)

 2. yared lakew says:

  I can not wait to read the next part of the article. whether something positive or not. But i would like to say ESAT is a great source of information which shows the real image of the country.

 3. ESAT is the first independent media which is not hijacked by special groups or the government.This makes ESAT a pioneer, by any measure,in the histroy of Ethiopian media.Thank you Prof. for the insight. Looking forward to reading the next article.

 4. ለፕሮፌሰር መስፍን ጥልቅ ኣክብሮት ኣለኝ። ነገርግን ተሳስተዋል። ኢሳት ፋና ወጊ ሳይሆን ያንኑ በኢትዮጵያ የተለመደ ፖለቲካዊ ወገናዊነትን ወደ ውጭ ሃገር ይዞ የመጣ ለጋዜጥኝነት መሰረታዊ መርሆዎች ብዙም ደንታ የማይሰጠው ነው።

 5. Gerazmach Chilomader says:

  what a short precise and positively provoking idea! here we go i am sure the coming discussion would be so fruitful and ESAT will progress more.Go ahead Gashe Mesfin

 6. Senait says:

  Great, eagerly waiting part two.

 7. Amba Alem says:

  What you said will be true if only ESAT was impartial and balanced. As a self-claimed intellectual who stand for the truth, you also need to be balanced and impartial and ESAT, although is clearly upsetting the rulings party, unfortunately they are the opposite version of ETV.

  • Baye says:

   I agree with you Amba. As the say goes, it’s like an old wine in a new bottle. The same “old” ETV staff is dominating the game, with the same attitude. The only difference is they are now in a different/ “new” TV station with different tone. Upsetting the regime can’t be a measure of achivement. We need change, a fundamental change that stems from attitudinal change.

   • Yetafenu Dimtsochi says:

    Don’t take me wrong but I think you guys aren’t clear about partiality or impartiality. The only person who was willing to have interview with ESAT was Sibhat Nega (that was also unknowingly). Otherwise, I could say that all the regime officials are not willing or allowed to have any kind of contact with ESAT. Providing counter information for accusations and what’s happening in the ground is the responsibility of the regime. The regime’s failure from such actions is the sole reason for ESAT to air information only from a single side. So we cannot blame ESAT about that and we cannot spoil their good work. I am sure you are not saying that ESAT should hold NEWS until they are confirmed by the regime. Not only the the regime officials but the church leaders were trying to hide the late patriarch Paulos sickness even if his death was confirmed a day later.

 8. Mekonnen says:

  Prof. Good insight.

Comments are closed.