ሁለት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

  ልክ ወያኔ/ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን መገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ለአንድ የወያኔ ዓላማ ብቻ እንዲውል እንዳደረገው ኢሳትም የኢትዮጵያን ሕዝብ ለአንድ ቡድን ዓላማ ተገዢ ለማድረግ የታሰበ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፤ እስቲ ማስረጃ ቁጠሩ ሲባሉ ከስሜትና ከጥርጣሬ በቀር ምንም ተጨባጭ ነገር አይወጣቸውም፤ የተለያዩ ቡድኖች፣ በትጥቅ ትግል ውስጥ ነን ከሚሉ ጀምሮ በሰላማዊ የፖሊቲካ ትግል ተወስነናል የሚሉና በተገኘው በማናቸውም መንገድ ወያኔ/ኢሕአዴግን እንታገላለን የሚሉ ሁሉ በኢሳት መድረክ እንዳገኙ ይታያል፤ ኢሳት የራሱ የፖሊቲካ እምነት የለውም፤ ወይም ሁሉንም የፖሊቲካ እምነቶች ይደግፋል ማለት ይቻል እንደሆነ አላውቅም፤ ዝም ብሎ እምነት የሌለው መድረክ ነው እንዳይባል ወያኔን ተቃዋሚነቱ ጎልቶ የወጣ ነው፤ ኢሳት የጸዳ የዴሞክራሲ መድረክ ነው ከተባለ ጸረ-ዴሞክራሲ አቅዋም ያላቸውን፣ ወያኔንም ጨምሮ ማስተናገድ የሚኖርበት ይመስለኛል፤ ይህ ግን ጎልቶ እየታየ አይደለም።

ዋናው የዴሞክራሲ ችግር ዴሞክራሲ መሆኑ የታወቀ ነው፤ ዋናው የነጻነት ችግር ነጻነት ነው፤ ዴሞክራሲንና ነጻነትን አልፈልግም የሚል ሰው የለም፤ በቅርቡ ከወጣው የመርስዔ ኀዘን ትዝታዬ የሚል መጽሐፍ ውስጥ አንድ እንቊ የሆነ ነገር አገኘሁ፤ እንደተጻፈ ልጥቀሰው፡-

በአእላፍ ሰገድ ኢያሱ ዘመን፣ በ1672 ዓ.ም. ጥቅምት 10 ቀን የሃይማኖት ጉባኤ ቆሞ ነበርና የቅብዓቶች አፈ ጉባኤ አባ አካለ ክርስቶስና የተዋሕዶዎች አፈ ጉባኤ አባ ኒቆላዎስ በየበኩላቸው ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በንጉሡ ፊት በብዙ ተከራከሩ፡፡ በክርክሩም ላይ አባ አካለ ክርስቶስ ተረትቶ ጳጳሱና እጨጌው አወገዙት፡፡ ንጉሡ አእላፍ ሰገድ ዮሐንስም የተዋሕዶዎችን መርታት የቅብዓቶችን መረታት አይተው ‹‹ከበረ ሥጋ በተዋሕዶ›› ተብሎ ዐዋጅ እንዲነገር አደረጉ፡፡ እርሳቸው ራሳቸው ግን የግል እምነታቸውን ሲገልጡ ‹‹እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ›› ብለው ተናገሩ ይባላል፡፡

አእላፍ ሰገድ ኢያሱ ከሦስት መቶ ሠላሳ ዓመታት በፊት ሦስት ቁም-ነገሮችን ያስተማረናል፤ አንደኛ ፍትሕ-ርትዕ ከሥልጣን ነጻ መሆኑን የሁለት ወገኖችን ክርክር አዳምጦ፣ የጳጳሱንና የእጨጌውን በውግዘት የተገለጸ ውሳኔ ተቀበለ፤ ሁለተኛ የግል እምነት ከዳኝነት ነጻ መሆኑን ሲያሳይ አሸናፊው ተዋሕዶ መሆኑን አወጀ፤ ሦስተኛ ሃይማኖት የግል መሆኑን ለማሳየት ‹‹እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ፤›› በማለት የራሱን እምነት አሳወቀ፤ እነዚህ ሁሉ ቁም-ነገሮች ከሽፈው ዛሬ፣ በሚያዝያ 2005 ዓ.ም. ከሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመታት በኋላ ከባድ ችግሮቻችን ሆነው ለተዋሕዶውም ለእስላሙም ተደንቅረውብናል! ይህ ባለህበት ሂድ! አይደለም፤ ቀኝ-ኋላ ዙር! ነው።

ከላይ ዋናው የዴሞክራሲ ቸግር ዴሞክራሲ፣ ዋናው የነጻነት ችግር ነጻነት መሆኑን ገልጬ ነበር፤ ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት በአጼ አእላፍ ሰገድ ኢያሱ ዘመን የተወሰነም ቢሆን የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትና ነጻነት በመኖሩ በአደባባይ በሙሉ ነጻነት ክርክር ተደርጎ አሸናፊና ተሸናፊ በይፋ ተለዩ፤ ዛሬ ግን ያንን ያህል የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነትና ነጻነት ስለሌለ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተሰንጥቃለች፤ የኢትዮጵያ እስልምናም የመሰንጠቅ አደጋ እያንዣበበበት በመሆኑ እንዳይሰነጠቅ አጥብቆ እየታገለ ነው።

ከዴሞክራሲና ከነጻነት የሚወለደው ችግር በውይይትና በክርክር፣ በሕጋዊ ሥርዓትና በሕግ ልዕልና ይፈታል፤ በአምባ-ገነን አገዛዝ ያለው አፈና ነው፤ ነገር ግን ዴሞክራሲንና ነጻነትን የሚያፍኑ አምባ-ገነኖችና ሎሌዎቻቸው ሁሉ አፈናቸውን የሚያከናውኑት በዴሞክራሲና በነጻነት ስም ነው፤ በደቡብ አፍሪካ አፓርቴይድ መሠረት የነበረው ለነጮቹና ለጥቁሮቹ ለየብቻ ዴሞክራሲና ነጻነት ይበጃል በሚል ነበር፤ ማነው ይበጃል ብሎ የሚወስነው? ሲባል መልሱ ነጮቹ ናቸው ነው፤ ነጮቹ በዴሞክራሲና በነጻነት ለነጮች ብቻ ሳይሆን ለጥቁሮችም ይወስናሉ! ኢትዮጵያም ውስጥ እነአሜሪካ ባርከው የተቀበሉት ክልል-በዘር ከተመሠረተ ሃያ ዓመታት አለፉ፤ ውጤቱ እያቆጠቆጠ ነው፤ ዴሞክራሲንና ነጻነትን እየደፈጠጠ ነው፤ ኢትዮጵያም እየደበዘዘች ነው፤ ከዚህ የአንድ አገር ውርደት የሚጠቀሙት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው፤ እነዚህም ሰዎች ቢሆኑ ለሢሶ ዕድሜያቸው አንኳን አይጠቀሙም፤ ለልጆች የሚተላለፍ ጥቅምም አይኖራቸውም፤ ከኢትዮጵያ ውጭ እንደልብ ተንደላቅቀው የሚኖሩበት አገርም መኖሩ ያጠራጥራል፤ ዛሬ እየተጠቀሙ እንዳሉት ነገም እንጠቀማለን ብለው ማሰባቸው ቂልነት ነው፤ ነገ ራሱን የቻለ ጣጣ ይዞ ይመጣል።

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት. Bookmark the permalink.

8 Responses to ሁለት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 1. degankahaway says:

  ፕሮፍ

  እኔ እንደሚመስለኝ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ብዙውን ግዜ እንኳን ለኢሳት ይቅርና ለቪኦኢ መቼ ቀርበው መግለጫ ይሰጣሉና ነው ኢሳት የሚወቀሰው፡፡ በእርግጥ ኢሳትም “ከመንግስት ባለስልጣን ሁኔታውን ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም” ሲባል ነው የምንሰማው ልክ ቪኦኢ እንደሚለው እንደውም አንድ ግዜ በቪኦኢ የቀረቡት ባለስልጣን ተብዪ ፖሊስ አዲሱን ሲያስፈራሩት ሰምቼ ነበር ይህ ማለት ኢሳትም እነኚህ “የመንግስት ባለስልጣን” ተብዪዎችን ለማነጋገርና ሃሳባቸውን ለማሰማት የተቸገረ ይመስለኛል፡፡

 2. meyesaw kassa says:

  Are gash M
  esfen beahunu sate endihe ayenet asetyayet be Esat laye yalewn yeakome mennet lemaweq kemtar men ale menorya latute Ethiopiawiyanoch byeasebu yekrta sayasebu kertwale malete ayedlem .gen beahunu sate gera betegaba haizb ehein mallet mabetaten new yemimeselew mekiniyatum manen mamen endalebn betam techgrenale , seleziha abate betam yekirta akibariwet nege betam E/r edmiwetn yarzimlen….

 3. Negash says:

  እውነትም ይሄ ዝናር ገና ሙሉ ነው፡፡ ረጅም እድሜ እና ጤና ፕሮፌሰር፡፡

 4. በቅድሚያ አንዲህ በግላጭ አግኝቶ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር መወያየትና መማር ትልቅ ንገር ነው:: ይህ በአንዲህ አንዲቀጥል ታዲያ (የመማማሪያ መድረኮችን ሁሉ በዘጋው አካል አንዳይዘጋ በመስጋት) ፕሮፌሰር አንዳንድ ጥንቃቄዎችን ቢያደርጉ አመክራለሁ:: አንዚህ ጥንቃቄዎች ቀላልና አስተማማኝ ናቸው::
  በኢትዮጵያችን ስለዲሞክራሲ የሚያወሩ በነጻነት የሚምሉ ወደስልጣን መጥተው (የመንግስት ስልጣን ብቻ አይደለም) ነጻነታችንን የገፈፉ ስንት አይተናል:: ሕግን፣ ስርዓትን፣ ፍትህን ጨፍልቀው በግል ፍላጎታቸው የተኩ ስንት አናውቃለን:: አንደውም የሚቀለው ያላደረጉትን መቁጠሩ ነው:: የዚህ ምክንያቱ አኛ ራሳችን ነን:: አስካልተነካን ድረስ ለነዚህ መብት ነጣቂዎች ድጋፍ በመስጠት:: ነገሩ የቀን ጉዳይ አንጂ መነካታችን አይቀርም::
  እሳት ፍትሃዊ መድረክ አይደለም ተብሎ የሚወቀሰው የገዢውን ፓርቲ መድረክ ባለመስጠቱ ብቻ አይደለም:: (ለነገሩ ይህ ብቻውን ቆም ብለን አንድንጠይቅ ሊያደርገን ይገባል):: እሳት በመድረኩ ላይ ብቻ በሚያደርጋቸው ነገሮችም ብቻ አይደለም:: ከመድረክ ውጭ ደጋፊዎቹ የሚያደርጉት የአፈና ሙከራም ከስሌት መግባት አለበት::ከሁሉም በላይ እሳትን ተጠየቅ የሚሉ ሁሉም እሳትን ለማጥፋት የተነሱ አይደሉም::

 5. Dan says:

  በኔ ዕይታ የኢሳት ችግር የፖለቲካ እምነቱ ወይም አቋሙ አይደለም:: ፍጹም ገለልተኛ የሆነ የሚድያ ሚና ሊኖረው አለመቻሉ ነው:: አንዳንዴ ፍጹም ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩም ቢሆን: የወያኔን አፈና በማጋለጥ ረገድ የሚሰራውን ያክል፦ በማህበረሰባችን በተቃዋሚዎችና በሌሎች ተቋሞች (በራሱ በሚድያው ጭምር) የባህልና የአመለካከት አብዮት ለመፍጠር አለመሞከሩ ነው:: አንድ ወያኔ ላይ ጣት ስለተቀሰረ ብቻ ለውጥ አይመጣም:: ለውጥ ማምጣት ያልቻለውን የተቃዋሚውን: የማህበረሰቡንና የሌሎች ተቋማትን ችግር እኩል መፈተሽ ካልቻለ ሚድያነቱና ገለልተኛነቱ ምኑ ላይ ነው? እንዲያውም በቅርቡ እንደታዘብኩት የራሱን የኢሳት ችግር ባደባባይ መተቸት እንደወንጀል/ክህደት እንደሚያየው ነው:: ለራሱ ነጻ ያልሆነ ድርጅት እንዴት ስለነጻነት ሊታገል ይችላል?

 6. Merga says:

  እግዚአብሔር እጆትን ይባርከው ክቡር ፕሮፌሰር !!!

 7. እኔ የምለው ኢሳት አሁን ለስልጣን ውድ ድር ራሱን እያዘጋጀ መንግስት አይመስለኝም። በአሁኑ ሰአት ሚስኪኑ ህዝብ ጩከቱን የሚያሰማበት አማራጭ የመገናኛ ብዙሃን አለመኖሩ እየታወቀ ወሪያችን አራት እግሩን ተክሎ ባንሰራፋው የገዥ መንግስት ሚዲያ አንጻር መታየት ያለበት እንጅ የገዥ መንግስት ባለስልጣኖችን በኢሳት ማቅረቡና ተጋባዥ ማድረጉ ቢኦኤን ጨምሮ ለማፈንና ለማዘጋት ቆርጦ ከተነሳ መንግስት የሚጠበቅ አይመስለኝም።እርስዎም እንዴት እንዳዩት እንጃ።ለርስዎ ክብር አለኝ።

Comments are closed.