አራት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2005

 እንደሚመስለኝ ከነፍጠኛነት ይልቅ ነገረኛነት ጥሩ የዴሞክራሲ መሠረት ሊሆን ይችላል፤ በእርግጥ ነገረኛነት ለኢትዮጵያውያን የባህል መሠረት አለው ቢባልም በነፍጠኛነት ስር እየታሸ ነው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ከነፍጠኛነት ጫና ስር ሲያመልጡና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመደራጀት ሲሞክሩ ሁሌም ነገረኛነት ያይላል፤ በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያውያን ማኅበሮች መሀከል ሕግንና ሥርዓትን ተከትሎ የተዋጣለት ማኅበር ብርቅ ነው፤ አብዛኛዎቹ እየተነታረኩ ሲከፋፈሉና ሲዳከሙ የሚታዩ ናቸው፤ የችግሩ መነሻም ሁልጊዜም ሥልጣን፣ ገንዘብና ዝና ናቸው፤ ከነዚህ ሲያልፍም በኢትዮጵያዊነት መሠረት ላይ ብቻ የቆመውን ማኅበር የፖሊቲካ እምነት ወይም የጎሣ ቀለም ለመቀባት በመሞከር ነው፤ በኢትዮጵያውያን ማኅበሮች ላይ ሲታይ የቆየው ኋላ-ቀር አስተሳሰብ በውጭ በተቋቋሙ ቤተ ክርስቲያኖችም ላይ መታየት ጀመረ፤ ባህል ነዋ።

በዘመናችን የተከሰተው ነገረኛነት ከባህላዊው እሰጥ-አገባ ክርክር በጣም የራቀና የዘቀጠ ነው፤ ‹‹ማን ይናገር የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረከመጠምጠም መማር ይቅደምነገር ሳያውቁ ሙግት፣ ሳይጎለብቱ ትዕቢት…›› ወዘተ. በሚሉ የሕገ ኀልዮት መመሪያዎች የሚገዛ ሙግትም ሆነ ክርክር፣ ወይም ወግና ጨዋታ ከነገረኛነት የተለየ ነው ለማለት ይቻላል።

የዛሬው ነገረኛነት የአእምሮ ሥርዓተ-ቢስነት አለበት፤ እኩልነትን በትክክል ካለመረዳት የሚገኝ የአእምሮ ብልግና አለበት፤ ዱላ ከያዘ ጋር ነገረኛነት አይኖርም፤ ፍርሃት ያጠፋዋል፤ ሥርዓት የሚመጣው በዱላ ብቻ ነው ከተባለ ውርደት ነው፤ በአንድ በኩል በስደት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በስደተኛነት እኩል ናቸው ከሚል መነሻ፣ በሌላ በኩል በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ጭቁን አቅመ-ቢሶች በመሆናቸው እኩል ናቸው ከሚል መነሻ ይጀምርና ሌላው ልዩነት ሁሉ ድራሹ ይጠፋል፤ ስለዚህ ማንም በምንም ጉዳይ ቃላትን እየፈተለ እንደዘመኑ ዳንስ ብቻ ለብቻ መንቦጫረቅ የኢትዮጵያውያን የነገረኛነት ባህል ሆኖአል፤ በቅርቡ አንደሰማሁት በዚህ የቃላት መንቦጫረቅ (ፓልቶክ) አንደኛ ሶማሌያውያን፣ሁለተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ሦስተኛ ኤርትራውያን ሲሆኑ ሌሎች አፍሪካውያን የሉበትም አሉ፤እውነት ካልሆነ እንርሳው፤ እውነት ከሆነ ግን ብዙ የምንማርበትና ራሳችንን የምናስተካክልበት ምክንያት ሊሆነን ይችላል፤ በቃላት መንቦጫረቅ ለጊዜው በእኩልነት ጸዳል የሚያሞቅ ቢመስልም የኋላኋላ ራስንም፣ማኅበረሰቡንም ይጎዳል።

የሶማልያውያኑንና የኤርትራውያኑን ባላውቅም ስለኢትዮጵያውያኑ ባጭሩ ምስክርነት መስጠት እችላለሁ፤ አብዛኛዎቹ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን ፊደል ከቆጠሩ ራሳቸውን አዋቂዎችና ፈላስፋዎች አድርገው በአደባባይ ለማቅረብ አያፍሩም፤ ግን ያሳፍራሉ፤ ለአንባቢው ማስተላለፍ የሚፈልጉትን ራሳቸው ሳያውቁት ጀምረው ሳያውቁት ይጨርሱታል፤ በእንግሊዝኛ መጻፍ የማይችሉ ቢሆንም በአማርኛ ጽሑፋቸው እንግሊዝኛ የሚያውቁ ለማስመሰል የሚያደርጉት ጥረት ሀሳቡንም አጻጻፉንም ያወላግድባቸዋል፤ ለዚህ ብዙ ምሳሌዎችን ከየጋዜጣው ማሳየት ይቻላል፤ ግን አስፈላጊ አይደለም፤ ምክንያትም አለኝ፤ ካላበዙት አንድ ጥሩ ባሕርይን ያመለክታል፤ በድንቁርናም ቢሆን በጣም የሚያስደንቅ በራስ መተማመንን ያሳያል፤ እኔ አምስተኛ ክፍል ሆኜ (የዚያ ክፍል ጓደኛዬ የዓየር መንገዱ ግርማ መኮንን አሁንም አለ) አንድ የሳይንስ አስተማሪ የካቶሊክ መነኩሴ መሬት ትዞራለች ብለው ማስረጃዎቻቸውን ሲደረድሩ እኔ እጄን አውጥቼ ‹‹መሬት አትዞርም፤ ዳዊት ወአጽንአ ለምድር ዲበ ማይ ይላል፤ ብዬ ድርቅ አልሁ፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፤ እኔ ገና የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፤ አስተማሪዬ ያላቸው እውቀት ለእኔ እሳቸው ከመጡበት አገር ከካናዳም ይርቃል፤ በዚያ ላይ እሳቸው መነኩሴ ናቸው፤ ዳዊትን በየቀኑ ይደግማሉ፤ ስለሃይማኖትም ቢሆን እኔ ከሳቸው ጋር አልወዳደርም ነበር፤ አስተማሪዬ ዝም ብለው ይስቁብኝ ነበር፤ በፈተና ጊዜ ግን ዳዊትን ጠቅሼ አልመለስሁም! ባልለወጥ የትምህርት ነገር በአምስተኛ ክፍል አብቅቶልኝ ነበር፤ እንዲህ ያለውን አጉልና ባዶ በራስ መተማመን በቶሎ ካልቀጩት አእምሮን ያባልጋል፤ በጥሩ መልኩም ቢሆን ነገረኛነት አይወደድም፤ ዳኛቸው ወርቁ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የወጣው ክርክሩን ሊቀበሉት ያልፈለጉ ሰዎች ‹‹ነገረኛ›› (እንደአቶ ሐዲስ ዓለማየሁ ‹‹ጉዱ ካሣ››) ተብሎ ነበረ።

አፍ ዳገት አይፈራም ሲባል የአነጋገሩን ትክክለኛነት ለመለካት ሳይሆን የተናጋሪውን አለመፍራትና አለማፈር ለመግለጽ ነው፤ አሽከር በአንደበቱ ውሻ በጅራቱ ሲባልም መናገር ወደላይ እያዩ ለመቀባባት ወይም ለማረጋገጥ ነው እንጂ ይዘቱ ከእውነት ጋር የማይገናኝ ይሆናል፤ ነገረኛ ማለት ደረቅ፣ እውነቱን ለቅቆ ለስለስ የማይል፣ ችኮ-መንቻካ ማለትም ይሆናል፤ ባለሥልጣኖቹ ለመስማት የሚፈልጉትን ብቻ እየመረጠና እያዋዛ ሳይሆን ለሱ የሚታየውን ደረቁን እውነት ይዞ የሚናገር ማለት ነው፤ በግልምጫ፣ በቁጣ፣ በጥቅም፣ ሳይሸነፍ የሚኖረው ነገረኛ ይባላል፤ ባህላችን ነገረኛነትን የሚያጥላላው ለኔ እንደሚመስለኝ ጠመንጃ-ያዥነትን ለማስከበር ነው፤ ሎሌ የሚኖረው መሣሪያ ወይ አንደበት ወይ ጠመንጃ ነው፤ ሎሌ በአንደበቱ ሲናገርም ሆነ በጠመንጃው ሲተኩስ ለጌታው ሲል ለመግደል ወይም ለማቁሰል ነው፤ የራሱ ዓላማም ሆነ ኢላማ የለውም።

ጠመንጃ-ያዥና ጠመንጃ-ያዥ ሲጫረሱ የሚያደርሱት ከባድ ጥፋት ለሰላማዊው ሕዝብም፣ ለአገርም  ይተርፋል፤ ነገረኛነት የዚያን ያህል አይጎዳም፤ በተጨማሪም ወደሠለጠነና ሥርዓት ወዳለው እሰጥ-አገባ ክርክር ለመድረስ ከጉልበተኛነት ከመነሣት ይልቅ ከነገረኛነት መነሣቱ መንገዱን ቀና የሚያደርገው ይመስለኛል፤ ነገረኛነት በአጉል እኩልነት ላይ የቆመ ቢሆንም የዱላ ፍርሃት የለበትምና ይሻላል፤ ደግሞም ትምህርት እየተስፋፋ ሲሄድ አጉል ነገረኛነት ለዝናብ እንደተጋለጠ ጨው እየቀለለ ይሄዳል፤ ስለዚህም አጉል ነገረኛነት የሚያስጠላ ቢሆንም ብንታገሠውና ብናርመው ከመደባደብ የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ይጠቅመናል፤ እየተራረምን በዚህ መንገድ ብንሄድና ብንለምደው፣ የእውቀትን ጎዳና አገኘነው ማለት ነው፤ ለብዙ ችግሮቻችን መፍትሔዎችን ማግኘት እንችላለን ማለት ነው።

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች, አፈናና ከአፈና መውጣት. Bookmark the permalink.

12 Responses to አራት፦ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 1. አንድ የመጨረሻ ነጥብ ላክልና አስተያየቴን ልቋጭ። ሌላው ትዝብቴ በአደባባይ የሕዝብ በሆኑ እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሻንን ለመናገር፣ ለመተንተን፣ አቋማችንን ለመግለጽ፣ ሌሎችንም ለመወንጀልና ለመተቸት ያለንን ድፍረት ያህል አስተያየቶችን ለመቀበል፣ ባደባባይ ለመተቸትና ለመወቀስ ድፍረት የማጣታችን ጉዳይ ነው። በርካታ ግለሰሶች፣ ቡድኖች እና የፖለቲካ ድርጅቶች የሕዝብ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያገባኛል በሚል የባለቤትነት ስሜት በማንኛውም መልኩ ይሁን ደረጃ የሃሳብ ወይም የተግባር ተሳትፎ ማድረጋቸው የሚደገፍ ተግባር ነው። ይሁንና አደባባይ እራስን ካወጡ በኋላ እኔን በተመለከተ ሃሳብ አትስጡ፣ አትተቹኝ፣ አትውቀሱኝ የሚባል ፈሊጥ ጥሩ መከላከያ አይሆንም። “ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ” ነው የሚሆነው። ከግል ሕይወታችን አልፈን አደባባይ ስንወጣና በተለይም በሕዝብ ጉዳይ ውስጥ ገብተን ተሳታፊ መሆን ስንጀምር ሃሳባችን ብቻ ሳይሆን እኛነታችንም የሕዝብ ይሆናል። ሕዝብ ደግሞ የራሱ በሆነ ጉዳይ ላይ ያሻውን የመምከር፣ የማንሳትና የመጣል ሙሉ መብት አለው። ይህን ሃሳብ ያካተትኩት ከኔ ቀደም ብሎ “አንድነት” በሚል መጠሪያ በፕ/ር መስፍን ላይ ለምን ኢሳትን እና ተቃዋሚዎችን ተቹ በሚል ለሰነዘሩት አመክንዮ የጎደለው ወቀሳ ምላሽ ቢሆን በሚል ነው።

 2. Andinet says:

  እንደ humanrightsinethiopia ( ያሬድ ኃይለማርያም ) ለኢሳት በቀናነት በቀጥተኛ እና ግልጽ በሆነ መንገድ የሚሰጥ አስተያየት ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ከእኔ በላይ አዋቂ ላሳር በሚል በተረትና በቅኔ የታጨቀ የተንኮል አስተያየት ለኢሳት አይጠቅመውም ፡፡
  ለውጥ በማያመጣ ፖለቲካ ሲንተጋተጉ ከርመው ድጋፍ ሲያጡ ከእነሱ በተቃራኒው ድጋፍ እያገኙ ካሉት ጋር ተባብረው መስራት እንኳን ባይችሉ ምናለ በስኬታቸው ጊዜ ደርሰው እንቅፋት ባይሆኑ?
  ወይ አይሰሩ ወይ አያሰሩ አለ ያገሬ ሰው!

 3. ሓየት! says:

  ኢሳት በተቆረቆረ በጥቂት ወራት ውስጥ የዛሬ ሶስት አመት ገደማ (ነሓሴ 2010) የሚከተለውን ስጋት-አዘል ምክር በአንድ የፖለቲካ ፎረም ጻፍኩኝ … በኔ የደረሰ በአይተ ፕ/ር መስፍን አይድረስ::
  ——————————————————————————
  ኢሳት በኔ እይታ ሚድያ ነው :: ኖ ሞር ኖ ለስ :: እንደሚድያ ደግሞ ከማንም መወገን የለበትም :: ለህዝብም ወግኖ ሊቆም አይገባም :: ሊቆምለት የሚገባው ዋና ነጥብ ቢኖር “ለእውነት ” ነው :: …

  እኔ በተደጋጋሚ ስጋቴን አስቀምጫለሁ :: ለኢትዮጵያ የሚበጅ ስራ መስራት ከፈለገ ያ ሚድያ …ዓላማውም ራዕይውም ምኑም እውነትና እውነት ብቻ መሆን ይኖርበታል :: ያ ሚድያ ከወያኔ ሚድያዎች የተሻለ ነገር ሊሰራ ይጠበቅበታል :: የወያኔ ሚድያ የራሱን ዓላማ ብቻ ለማስተጋባትና ህዝቡን ለመጫን 24 ሰዓት ሙሉ ፕሮፖጋንዳውን ሲነፋበት ውሎ የሚያድር : የሱን አመለካከት የማይጋሩ እንደ ጠላት የሚያስነግርበት ሚድያ ነው :: በዛው ልክ ደግሞ ተሳክቶለታል ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የዘራው የዘር እሾህ የእያንዳንድችንን ልብ እየወጋ እርስ በርስ እንደተፈራራን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ እንድንኖር አስችሎታል :: ኢሳትም ማንም ያቆቁመው ማንም የራሱን ዓላማ ለማስረጽ ብቻ የሚያውል ከሆነ ወይም ከአንድ የተመረጠ ተቃዋሚው ጎራ ብቻ ወግኖ ሲለፍፍ ውሎ ቢያድር የሚፈይደው አንዳች ቁም ነገር አይኖርም :: ጥፋትን እንጂ :: ትርፍ ፈልጎ ይክፈተው ወይም ለኢትዮጵያ ህልውና ብሎ እውነትን እስካላስተጋባ ድረስ ወይ በራሱ ጊዜ ይዘጋል ወይ የማያባራ ሰደድ እሳት ለቆብን ይቀራል :: ለእውነት እቆማለሁ እስካለ ድረስ ከጣፋጭ ፍሬውም ከጎምዛዛውም የምንቋደሰው ሁላችንም መሆን አለብን :: …

  ለእወነት ከመቆም በተጎዳኝ ኢሳት ሊኖረው የሚገባ ኳሊቲ ሁሉንም ማዳረስ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ላይ መድረስም ጭምር ነው :: እውነት በአንድ ወገን ብቻ መሽጋ የምትገኝ ንብረት አይደለችም :: ለአገር ቤዛ ነኝ ; ከኔ በላይ ተቃዋሚ ላሳር ነው ; ከኛ በላይ አዋቂ ለእብደት ነው … ወዘተ የሚሉትንም መዳሰስ ይኖርበታል :: ያንዱን ፍላጎት በሌላው ላይ ለመጫን ሲባል ብቻ የራስን ጉድፍ ሸፋፍኖ ወያኔ -መድረክ : ኢዴፓ -ዓረና ወዘተ ማለት ብቻ ተገቢ አይሆንም :: .የኢሳት ዓይን ሁሉንም በእኩልነት የሚያይ መሆን አለበት :: ሁሉንም ፓርቲና አመራር እኩል ፈትሾ … ለህዝብ ማቅረብ አለበት :: ህዝቡንም ፈትሾ መልሶ ሊያስተጋባለት ይገባል :: በእያንዳንዳችን ማጀት ውስጥ ስር የሰደደ በሽታ ሳይኖር አይቀርምና ኢትዮጵያን ማዳን ከዛ ይጀምራል ::

 4. የወያኔን ስሕተትና ወንጀል ሌላው ኃይል ሲፈጽመው ትክክልና ሕጋዊ ሊሆን አይችልም!
  በተደጋጋሚ ጊዜያት በተለያዩ የመወያያ መድረኮች ላይ ሲነገር የምሰማውና በውስጤም ትልቅ ጥያቄ የጫረብኝ ጉዳይ አለ። ይህውም ወያኔን ብቸኛ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊያን ጠላት አርጎ በማስቀመጥ ሌሎች ኃይሎች ወይም ግለሰቦች ያሻቸውን ቢያደርጉ፣ ሕግ ቢተላለፉ፣ በጎጥና በዘር ፖለቲካ ውስጥ ተዘፍቀው ሕዝባቸውን ቢያዋርዱ፣ መብት ቢጥሱ፣ የሰዎችን ክብር እና ስብዕና የሚያዋርዱ ተግባራትን ቢፈጽሙ፣ ከዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና መርሆዎች እርቀው ፈላጭ ቆራጭ ቢሆኑ፣ ወያኔ የተጓዘበትን ሕዝብን፣ አገርን እና ኢትዮጵያዊነትን የመካድ መሰሪ ተግባር ሲደግሙትና ተያይዘውም ቁልቁል ሲወርዱ ብናይ እንኳን ወያኔን አሽቀንጥሮ ለመጣል በሚደረገው ትግል ወስጥ እነዚህ ኃይሎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እስከሆኑ ድረስ ወይም ሥርዓቱን እስከተቃወሙና እስካወገዙ ድረስ ሊተቹ፣ ሊወገዙ ወይም ሊሚያደርሷቸውም ጥፋቶች ተጥያቂ ሊደረጉ አይገባም ከሚል እምነት የመነጨ ውይም “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ” አይነት አስተሳሰብ በብዙ ሥፍራዎች ላይ ለነፃነት እንታገላለን ከሚሉ ኃይሎች ሲነገር አስተውያለሁ።
  ይህ አይነተ የተወላገደና መርህ የለሽ አስተሳሰብ እየጠነከረ ከመምጣቱም የተነሳ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ካድሬዎቻቸው አልፎ ለሰብአዊ መብቶች መከበር እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንታገላለን በሚሉ ግለሰቦች፣ የመገናኛ ሚዲያዎች (የቴሌቪዥን እና እሬዲዮ ጣቢያዎችን የተለያዩ የዜና ማሰራጫ ድህረ-ገጾች)፣ የሲቪክ ማኅበራትና የተለያዩ ቡድኖች ዘንድም እንደ ወረርሽኝ እየተንሰራፋ መጥቷል። በአገር ጉዳይ የምናበረክተው አስተዋጸኦ የኢትዮጵያን ሕዝብ የራሱ ሥልጣን ባለቤት እንዲሆን፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተገነባባት፣ የሕግ ልዕልና እና የሕግ የበላያነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ እንድትኖረን ከሆነ በምን መስፈርት ነው አንዱን ጎሠኛ እያወገዝን ሌላኛውን ጎሠኛ የምናጠበድለው? አንዱን አገር ገንጣይ አይንህን ላፈር እያልን ሌላኛውን አገር በማስገንጠል የፖለቲካ ስካርና ምኞት የሚናውዘውን እሹሩሩ የምንለው? አንዱን በወንጀለኛነት እና በሰብአዊ መብቶች እረጋጭነት እየኮነንን ያንኑ ድርጊት የሚፈጽሙ ሌሎች ኃይሎችን የዴሞክራሲ ለውጥ አጋር የምናደርገው?
  ይህን አስተያየት እንድሰጥ ምክንያት ወደሆነኝ ፍሬ ጉዳይ ልመለስና ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ክፍል አንድ ብለው የጀመሩት ዳሰሳ እራሳችንን ለመፈተሽ እና ከስህተታችንም ለመታረም ድፍረቱ ካለን ብዙ ልንማርበት የሚገባ ብርካታ ቁምነገሮችን የያዘ ነው። ምንም እንኳን ፕ/ር መስፍን የኢሳትን ገለልተኝነትና ነጻ ሚዲያነት በተመለከተ በመጀመሪያዎቹ ክፍሎች ውስጥ በጻፉዋቸው ሃሳቦች እና ባንጸባረቁት አቋም ባልስማማም ይህን ጉዳይ በማንሳት ለውይይት በር መክፈታቸው ላመሰግን እወዳለሁ። በመጀመሪያ ኢሳት እያበረከተ ያለውን አስተዋጸኦ ለማኮሰስም ሆነ አሳንሼ ለማቅረብ አልወድም። ኢሳት መረጃቾችን በማሰራጨት እረገድ ቀላል የማይባል ሚና እየተጫወተ መሆኑ ግልጽ ነው። ይሁንና ሚዲያውም ሆነ ሁሉም ሳይሆኑ የተወሰኑት በዙሪያው የተሰበሰቡ ግለሰቦች ከላይ ከጠቀስኩት ወያኔን ብቻ ኢላማ ያደረገና ሌላው “እንዳሻው” የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ሰለባዎች መሆናቸውን የሚያመላክቱ ተግባራትን በሚዲያው ላይ ሲያከናውኑ ማየት የተለመደ ሆኗል። ይህ ያለመወቀስ፣ ያለመተቸትና ያለመገምገም ከለላይ የተሰጣቸው የፖለቲካ ኃይሎች ባልተመጣተነ መልኩም ቢሆን በኢሳት የአየር ጊዜ ማግኘታቸውና ኢሳትም ወያኔን ከጠዋት እስከማታ ሲያወግዝ ውሎ ማምሸቱ ቀንደኛ የወያኔ ተቃዋሚ መሆኑን እና ለተቃዋሚዎችም የመተንፈሻ መድረክ መሆኑን ያሳያል እንጂ ለገለልተኛና ነጻ ሚዲያነቱ መገለጫ ሊሆነው አይችልም።
  ፕ/ር መስፍን እንዳሉት በኢሳት ላይ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያነገቡ ኃይሎች በተናጠል እንጂ እርስ በርስ ሲሟገቱ እና ክርክር ሲያደርጉ አለመስተዋሉ አንድ ድክመት ቢሆንም ምንጩ ግን ከላይ የጠቀስኩት የአስተሳሰብ ችግር ይመስለኛል። ኢሳት ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ሲገመግም፣ ስህተቶቻቸውን ሲነቅፍ ወይም ላጠፉቻቸው ጥፋቶች ተጠያቂዎች ሲያደርግ ያየሁበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ለሕዝብ አደባባይ የወጡና መወያያ በሆኑ የተቃዋሚ ኃይሎች ገበና ላይ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አልፎ አልፎ በሚያደርጋቸው ውይይቶች ከሚያነሳቸ ጥያቄዎች ውጪ ኢሳት ‘አይኔን ግንባር ያድርገው’ በሚል አንዳልሰማ ነገሮችን ሲያልፍ ወይም ሲሸፋፍን ማየት የተለመደ ነው። በተለየ ሁኔታም በግንቦት 7 እና ከኤርትራ መንግስት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ጉዳዮችን፣ አስተያየቶችን ሆነ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ ኢሳት ገና ድፍረቱን አላገኘም ወይም ነጻነቱ የለውም።
  ቅድም ያነሳውት የመርህ ጉዳይ ለኢሳት የሚኖረው ትርጉም ግልጽ አይደለም። አንድ ኢትዮጵያዊ በወያኔ መንግስት በደል ሲፈጸምበት ኢሳት በማጋለጡም ሆነ ተጠያቂ በማድረግ የሚያሳየው ትጋት ይበል የሚያሰኘውን ያህል ያንንኑ ድርጊት በአንድ ኢትዮጵያዊ ላይ ሻቢያ ሲፈጽመው ኢሳትን የማይነዝረው ከሆን ነገር አለ ማለት ነው! ለዚህ ወደፊት በምጽፋቸ ጽሑፎች ላይ ማስረጃ እያጣቀስኩኝ እመጣበታለሁ። ለማንሳት የምፈልገው ቁምነገር ግን አንድ ለሰብአዊ መብቶች መከበር እቆረቆራለሁ የሚል ግለሰብ ወይም ቡድን ወይም እንደ ኢሳት ያለ ሚዲያ ጥሰቱ በማንም ላይ ይፈጸም፣ በየትም ሥፍራ ይፈጸም፣ በማንም ይፈጸም ተቆርቋሪነቱን እና ድምጹን እኩል ሊያስተጋባ ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ገለልተንነት፣ መርህ፣ ነጻነት፣ እና ለሕዝብ ተቆርቋሪነት ጥያቄ ውስጥ ይወድቃሉ።

  እድሜና የተሟላ ጤንነትን ለማከብርዎ ፕ/ር መስፍን እመኛለሁ።
  ከቀደሙት የምንማርበት ልቦና ይስጠን!
  ያሬድ ኃይለማርያም
  ከቤልጅየም

 5. Mike says:

  Professor Mesfin pointed out a number of issues lingering in my head. I watch ESAT frequently and noticed several weaknesses. Most of the time the journalists don’t have sufficient knowledge of the area they interview. For example when they plan to interview an economist about the state of Ethiopian economy, they have to do a proper preparations. The interviewee should be an economist who has active research interest on Ethiopian economy. The interviewer should also have deep knowledge and proper preparation. Picking someone who is teaching in one of American universities who don’t have knowledge of Ethiopian economy beyond listing and reading news is utter stupidity. Trying to get an economist whose opinion is not tainted by his political view is paramount importance. Othewise, cherry picking would be common place. A biased economist selects facts to fit into his political view. Once I was listening an interview of a professional regarding Illicit financial flows, I was shocked to find out how he distorted the facts because he hated the regime in Addis. If the interviewer were well versed with the issue, he would have challenged him and we would have the chance to get a proper understanding of the issue. Unfortunately, ESAT is giving them a free ride to say whatever they want. I do somehow understand if politicians chery pick facts. Still they have to be challenged. I don’t take the views of Dr Berhanu as independent economist view as he is fighting the regime tooth and nail. At certain instances, the journalists of ESAT become very soft on some interviewees. When Sisay interviewed Dr Dima Nego he was very soft particulary about those people supposedly killed by OLF cadres. Dr Dima threw the blame on TPLF cadres. Instead of challenging Dr Dima with a number of evidences and serious questions Sisay let Dr Dima off the hook. It seemed that Sisay did worry about that challenging opposition politicians no matter what their horrible track record would damage the struggle against the regime in Addis. . These people got serious questions to answer. The other striking fact in other webstites is that they don’t publish serious issues of public interest when they believe that it would tarnish the name of the opposition. Once UN published a report blaming OLF and Shabia planning to bomb a number of places. A number of webstites didn’t publish that.Why? That is why we are witnessing day after day pseudo-democrats, dictators and criminals are hidding in opposition camp. Some of the journalists have very biased (sometimes lying) websites and these journalists bring their bais to ESAT. Clearning our house is as important as fighting the dictatorial regime in Addis. ESAT can do a lot. It should stop its bias, have journalists well versed with the subject matter they interview, get the right people, introduce regorous interviews, invit people with different views etc.

 6. ነፃነት አሸናፊ says:

  ጋሼ መሽፍን እናመሰግናለን ዛሬም ለማረም ለማስተማር ለመምከር ስላልደከሙ ጌታዬን አመሰግነዋለሁ፡፡ በዚህ ርዕስ ስር/ ከ ክፍል አንድ ጀምሮ/ ብዙ ጉዳዮች ተዳስሰዋል፡፡ እርሶ አሁን በግልጥ አወጡት እንጂ የኢሳት ጉዳይን የማያውቅ ተመልካች/አድማጭ አይኖርም፡፡ /ሚዛናዊነትን በተመለከተ ማለቴ ነው/ ኢሳት ሚዛናዊ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እንደ እኔ ኢሳትን የሚደግፈው ስደተኛ ብዙ ብሶት ያለበት ስለሆነ እኛ እና እነሱ /ወያኔ/ ወደሚል ፅንፍ ተገፍቶአል፡፡ ይህንንም አመለካከት የሚደግፈው ሚዲያ እንዲያንፀባርቅ ይፈልጋል ለዚህም ጫና ያሳድራል፡፡ በአንድ ወቅት በስደት የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እንዳለው… በውጭ ያለው ዳያስፖራ የድጋፉን ያህን ዘገባውንም መቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ኢሳት የቆመው በዳያስፖራው ገንዘብ እንደመሆኑ ከፍቃዳቸው ውጪ መሆን ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላል፡፡ ለዚህም ይሆናል ኢሳት በግልጥ ተቃዋሚ የሆነው፡፡ ይህ ነገር ካልታረመ ዛሬ ባይሆንም ነገ ዋጋ ያስከፍላል፤ አሁን ያልደከሙበትን ያላጎለበቱትን ሚዛናዊነት ነገ ከየት ያመጡታል?!?…. ዛሬ ያልተዘራ ነገ አይታጨድም፡፡ ይህ እንዳለ ግን ኢሳት መረጃ በማቀበልና እውነቱን በማጋለጥ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ያለ ወደፊትም ትልቅ መሆን የሚችል ተቁዋም መሆኑ አይካድም፡፡ በክፍል ሶስት እኔም የምስማማበትን የምመኘውን ሀሳብ አንስተዋል፡፡ ከእኛ ለእኛ የሆነ የአስተዳደር ዘይቤ/አይነት/፡፡ እስተዛሬ የማውቀው ብለው የነገሩን/ በአቶ ሀዲስ አለማየሁ፤ ሁለተኛው በኤንጂኒር-የሕግ ባለሙያ ደመቀ መታፈሪያ፣ ሦስተኛው የኔ ናቸው/ ያሉአቸውን በደንብ ቢያብራሩልንና ብንወያይበት እንዴት መልካም ነበር፡፡ ምክንያቱም ሀገሬ ኢትዮጵያ ሁሉንም በሚያስብል ሁኔታ ሞክራ አልሆነላትም፡፡ አዲሱ ትውልድ ተነጋግሮ ተመራምሮ ለ ሀገር የሚበጀውን መተግበር አለበት፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ ከሌላው መዋስ/መኮረጅ/ ስናቆም ነው፡፡ ክፍል አራት ላይ አንዲት አንጀቴ የገባች ሀረግ አለች… “…..አብዛኛዎቹ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን ፊደል ከቆጠሩ ራሳቸውን አዋቂዎችና ፈላስፋዎች አድርገው በአደባባይ ለማቅረብ አያፍሩም፤ ግን ያሳፍራሉ፤ ለአንባቢው ማስተላለፍ የሚፈልጉትን ራሳቸው ሳያውቁት ጀምረው ሳያውቁት ይጨርሱታል፤ በእንግሊዝኛ መጻፍ የማይችሉ ቢሆንም በአማርኛ ጽሑፋቸው እንግሊዝኛ የሚያውቁ ለማስመሰል የሚያደርጉት ጥረት ሀሳቡንም አጻጻፉንም ያወላግድባቸዋል፤”
  ልክ ነው!!!! የእኔ ትውልድ ምንም ሳያውቅ ያወቀ መስሎ መታየት ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የወያኔ አጥፊ የትምህርት ስርዐት ብቻ ሳይሆን የእኛም የንባብ ባህል አለመዳበር/ንባብን አለመውደድ/ አስተዋፅኦ አድርጎአል፡፡ ሀቁ ይህ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደሚያንቆለጳጵሰንም አይደለን፡፡ ለዚህ ትውልድ ኢትዮጵያዊነት በአረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ማሸብረቅ ነው፡፡ ሀገር ሲባል እማማ ኢትዮጵያ ብሎ ከንቱ ፉከራ ማሰማት ነው፡፡ የራሱ አስተሳሰብ የሌለው ዝም ብሎ የቲፎዞ ስብስብ ነው፡፡ የተወደደውን መደገፍ እንጂ ለምን ማለት የለም፡፡ ድሮ አዋቂዎች በስንዴ መሀል እንክርዳድ አይጠፋም ብለው ነበር ለዚህ ትውልድ የተገላቢጦሽ በእንክርዳድ መሀል ስንዴ የሚለው ይስማማል፡፡ ጥቂቶች ብርቱ የሆኑ አሉና፡፡ ደግነቱ ለማሰብ ፣ለመጠየቅ እንዲሁም ሀገርን ለመለወጥ ጥቂት በቂ መሆኑ ነው፡፡ ጥቂትን የሚያበዛው እግዚአብሄር ይርዳን፡፡ አሜን፡፡
  ጋሼ መሽፍን እድሜና ጤና ይስጥልኝ፡፡
  (ልደትዎ መከበሩን ሰምቻለሁና ቢዘገይም እንኩዋን አደረስዎ)
  አክባሪዎ
  ነፃነት አሸናፊ

  • Dan says:

   ከፕ/ር መስፍን አንድ የማልቀበለው አመለካከት ቢኖር ነጻነት የጠቀስከውን ነው:: ራስን ባለመዘንጋት (ማንነትህን ባለመርሳት) እና በጉራማይሌይኛ/በኢንግሊዝኛ በመተየብ/በመናገር መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያክል ነው :: አንድ ወጣት ጉራማይሌይኛ ሲያወራ ሃሳቡን በቅጡ መግለጽ ካልቻለ ያ ሰው ኢንግሊዝኛ እየተለማመደ መሆኑን ብቻ ነው የሚያሳየው እንጂ ክብርን ከማዋረድ ወይም ራስን ከመካድ ጋር የሚያገናኘው ነገር ምን እንደሆነ ለኔ አይታየኝም:: አንዳንዱ ምናልባት ጉራውን ለመንዛት ብሎ ሊያደርገው ይችላል:: አዋቂ መስሎ ለመታዬትም አንድ ሁለት ቃላት ጣል ሊያደርግ ይችላል:: በዚህ ድርጊቱ ግን ግለሰቡን የምኮንንበት ምክንያት አይታየኝም:: የግለሰቡ ችግር ሳይሆን ማህበረሰቡ ያቆየው/ያወረሰው የከሸፈ ባህል ነውና:: በኢንግሊዝኛ ማውራት/መጻፍ የአዋቂነት መለኪያ አድርጎ የሚመለከተውን ያክል እንደ ነውር የሚቆጥረው ጽንፈኛም አለ ማህበረሰባችን ውስጥ (በተለይ ቤተ ክህነት አካባቢ ያሉ ሰዎች) :: የፕ/ር አይነት አንዳንድ ኮንዘርቫቲቭ ምሁራን ደግሞ በጅምላ መመጻደቅ ይሉታል 🙂 :: በኢንግሊዝኛ መጻፍ በመጻፉቸው (በአማርኛ ባለመጻፋቸው) ብቻ ለሆዳቸው ያደሩ ተብለው ተወርፈዋል በፕ/ር:: በጣም ደካማ አመለካከት ነው ይሄ::
   በተለይ ወጣቱ በዚህ መንገደ ነው ቋንቋውን የሚያዳብረው:: ራሱን የቻለ “ኢንፎርማል” ትምህርት ቤት ነው ይሄ:: በዚህ መልኩ አወላግዶ ካልተማረው ባንዴ ጸዴ ኢንግሊዝኛ ከየት ያመጣዋል:: በዚህ አይነቱ ኋላቀር ትችት ስንቱ ተሳቆ አንደበቱ ተሳስሮ እንደሚቸገር ባያችሁ ይህንን ባላላችሁ ነበር::

 7. Dan says:

  አንድነት አልገባህ ያለ የፕ/ር ምክር እኮ ትችትንና ተቃራኒ ሃሳብን ካሁኑ ማስተናገድ አለብህ ነው:: ይህን ሳትለማመድ አገርን ያክል ነገር ለመረከብ ማኮብኮብ ምን የሚሉት የዋህነት ነው:: ትችትንና ተቃራኒ ሃሳብን ማስተናገድ አቅቷቸው ከተበታተኑ ሺ ጊዜ ዛሬ ይበተኑ: ነገ አገር ሳይበትኑ በፊት!! ይህንን ቢመርህም ቢጎመዝዝህም መላመድ ብቻ ነው ያለብህ:: ተሸፋፍኖ ጉዞ እስከዛሬ የትም አላደረሰንም: እዛው ባለንብት ስንረግጥና ስንራገጥ ነው ያለነው:: ትችት ማድመጥን: ማስተናገድን: መቀበልን ልመድና ዛሬ አገርን ከ”ሚመሩት” የተሻልክ መሆንህን አሳይ:: ካልሆን ወያኔን ስለጠላን ተብሎ ሌላ ወያኔ ኮትኩተን ማሳደግ ያለብን አይመስለኝም:: ሚድያው መርህ ይኑረው:: በግለሰቦች ስሜትና ኩርፊያ ሳይሆን በመርሁ መሰረት የሚጠበቅበትን ይስራ:: ሌላው ደግሞ እውቀት እንኳን ቢያንሰው ኢትዮጵያዊ ስነምግባርን ይጠብቅ:: ትርጉም በሌለው “ቦጭራቃ” ትግል ስም… የመቻቻል ባህላችንን ባልተገራ አንደበቱ አይበክለው:: ይኸው ነው የፕ/ሩ ምክር::

 8. Yared says:

  Thank you professor once again for your excellent analysis and insight. Your argument is logical and correct.
  It is a constructive critic to ESAT and not like Andinet commented as “ kesedeb yemayetenanese techete”. Sometimes a strong word will be more powerful to share ideas and to touch our inside. I think professor always uses strong words to effectively share ideas and initiate discussions.
  However, despite this logical analysis and good insights I want ask z professor some questions:
  Prfessor, Do you think “Negeregnanete” is our major problem especially at now? Is this problem greater than our major political problem that most of our people face right now? Don’t you think that it will be better if we could tolerate such kind of problems (“Negeregnanete” ) for the time being and focus on our major political problem?
  Professor, I asking these questions because I am afraid not to focus on our major political problem while sticking in these issues (“Negeregnanete” ) which I think we could improve it through time in our culture.
  I even believe that we could use these pal talks discussions ( in your word “yekalate meneboracheke”) with ‘negeregnoche” as a good opportunity. For me I prefer those “ negeregna “ people than most of our guys who have nothing to discuss other than European footballs or other unnecessary issues of us………… cause I have at least sth to discuss in common about our country with these “negeregna” people.
  As you said “…… አጉል ነገረኛነት የሚያስጠላ ቢሆንም ብንታገሠውና ብናርመው ከመደባደብ የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ይጠቅመናል፤ እየተራረምን በዚህ መንገድ ብንሄድና ብንለምደው፣ የእውቀትን ጎዳና አገኘነው ማለት ነው፤ ለብዙ ችግሮቻችን መፍትሔዎችን ማግኘት እንችላለን ማለት ነው።”.
  Lastly, I want to say that I have a great respect to your firm stand on your moral values. But sometimes we need political solutions keeping in mind these good moral values.

 9. Andinet says:

  የፕሮፌሰር መስፍን የትችት ኣላማ ስህተትን ለማረም እንጂ ሌላ ዓላማ እንደሌለው የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የፕሮፌሰር መስፍን የትችት አካሄድ አንዳንድ ጊዜ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ እና ፓለቲካዊ ጠቀሜታ የሌለው በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ አንድ ጥሩ ጅማሮ በሀገሪቱ ቢኖር እና የተወሰነ ሰህተት ካለበት ይህን ስህተት ለማስተካከል እሳቸው የሚመርጡት መንገድ ጠንካራ ጎኑን አበረታትቶ ከማጎልበት ይልቅ ስህተቱን በማጉላት ከስድብ በማይተናነስ ትችታቸው ማደባየት ነው፡፡
  ይህን ለማሳየት ሁለት ምሳሌዎችን ላቅርብ፡ –
  1. በ 97 ምርጫ ወቅት የፕሮፌሰር መስፍን ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንደ ቅንጅት ፓርቲ አመራር አባል ያመጡትን ውጤት ያህል በርካታ ስህተቶች ሲሰሩ ተስተውሎአል፡፡ ለምሳሌ በድርጅቱ ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮች ውስጥ ተነጋግሮ እንደመፍታት በየሚዲያዉ እየወጡ በአደባባይ የቅንጅት አመራሮችን ሲተቹ ይታዩ ነበር፡፡ እሳቸው የተከተሉት አካሄድ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሰፈነበት ሀገር ገነቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በዛ ወቅት ማንን እንደተጠቀመ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የእሳቸው የትችት አካሄድ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንዲሁም ፓለቲካዊ ጠቀሜታ የሌለው ነበር፡፡

  2. በ 97 ምርጫ ወቅት በቅንጅት ክፍፍል ወቅት እንኳን ክፍፍሉ እንዲረግብ ከማድረግ ይልቅ እንዲባባስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ማለት ቻላል፡፡ እስቲ ማን ይሙት ቢያንስ የ 97 ቱን ምርጫ እንዲሳካ ከማንም በላይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የነበሩ የቅንጅት አመራሮችን ለእነሱ በማይገባ ከስድብ በማይተናነስ ዘለፋ ከፓለቲካ እንዲርቁና እንዲበታተኑ ከማድረግ ይልቅ የማቀራረብ ስራ ቢሰሩ ምን ነበረበት ? በዚህም ወቅት ማን እንደተጠቀመ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ስለዚህ እዚህም ላይ እሳቸው የተከተሉት አካሄድ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንዲሁም ፓለቲካዊ ጠቀሜታ የሌለው ነበር፡፡
  አሁን አሁን ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን በሚያቀርቧቸው መጻህፍት እና ጽሁፎች ይህ የተለመደውን ከስድብ የማይተናነስ ትችታቸውን አጠንክረው ቀጥለውበታል፡፡ የሚያቀርቧቸው መጻህፍት እና ጽሁፎች እንደ ከዚህ ቀደሙ አስተማሪ እና አወያይ ከመሆን ይልቅ ልክ በፖለቲካ ተሳትፎአቸው እንደሚያሳዩት ባህሪ የሰዎችን ሞራል የሚነካ እና ለውይይት የማይጋብዝ እየሆነ ነው፡፡ የቅርብ ጊዜ መጽሀፋቸው መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሀፊዎች ይብዛም ይነስም በኢትዮጵያ ታሪክ ምርምር የራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል፡፡ በመሆኑም የእነሱን ስራ ገንቢ በሆነ ሁኔታ ጉድለቱን ከማሳየት ይልቅ ምንም አስተዋጽኦ እንዳላደረጉ አልባሌ ሰዎች ከስድብ በማይተናነስ ትችታቸው መዘለፍ አለባቸው? ለዚህም ይሆናል እነዚህ የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሀፊያን በጉዳዩ ላይ ውይይት ከማድረግ ይልቅ ዝምታን የመረጡት፡፡
  እሳቸው ስለ ኢሳት ያቀረቡት የሰሞኑ ጽሁፎችም ያስታወሰኝ ነገር ቢኖር ያው እንደተለመደው አሁን አትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፤ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ የሌለው እና እንዲሁም ኢሳት እዚህ እንዲደርስ ለደከሙት ሰዎች ከማበረታታት ይልቅ ሞራል የሚነካ ትችታቸውን ነው፡፡ የአቅሙን የሰራ ሰው ቀርቶ ምንም ያልሰራ ሰውን እንኳን ከስድብ የማይተናነስ ትችት አይገባውም፡፡

 10. Senait says:

  A constructive comment from the good professor to the voice of the voiceless.GREAT JOB thank you Professor!!!

 11. Kidus says:

  Dear ESATs I love U. you are our/my voice but Prof is telling you the truth, especially when you discuss within and while you interview your gusts. It should not be always to oppose media is about the truth. Sisay is the best (i mean in his interviews).

  I am so exited to read Prof’s writings. Keep it sir you are getting us.

Comments are closed.