ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2005

እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ ይህ እምነት ራስን ማጽዳትንም ይጠይቃል።

ማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል ነው፤ ከከሸፈ በኋላ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በጣም ከባድ ሥራን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ከወዲሁ ኢሳት ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲተከል የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ዘለቄታ እንዲኖረው ማረጋገጫ ይሆናል።

የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ አንፈራጥጠው ከላይ ቤት እታች ቤት እየቀላወጡ አካላቸውን፣ አእምሮአቸውንና መንፈሳቸውን የሚያባልጉ ሰዎችን ያበራክታል፤ የድብቅብቆሽ ዓለምን እየፈጠሩ የጠራውን ከደፈረሰው፣ የጸዳውን ከአደፈው፣ ሳይለዩ ለሚያወሩት ደካሞች ሜዳውን ያሰፋላቸዋል፤ የወያኔ/ኢሕአዴግን ፍርሃት ወደመርበድበድ ይለውጠዋል፤ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ  የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርን አያስገኝም።

ንስሐ ለመግባት ወኔ ለሌላቸው፣ በሠሩት ጥፋት አገርን ወይም ወገንን በመበደላቸው ዛሬም ለመኩራራት ለሚፈልጉት፣ አርበኛውንና ባንዳውን ባንድ ሚዛን አስቀምጠው ለሚተቹት፣ የኢትዮጵያውያንን ሰውነት አራክሰው ጊዜያዊ ጥቅማቸውን ለሚያከማቹ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በተንኮል እየመነዘሩ የሥልጣን መሰላል ለሚያበጁ ሁሉ ፊት-ለፊት ቆሞ ለሚጋፈጣቸው ኢሳት መድረክ ይሆናል፤ የኢሳት ዋና ጥቅሙ እዚህ ላይ ነው፤ ይህንን ተግባር ለመፈጸም ኢሳት የኢትዮጵያ፤ ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲሆን መንገዱን እንጥረግ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በባለቤትነት የሚመራውና የሚያካሂደው እናድርገው፤ ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሳት ላይ ያለው መብት ነው ከተባለ፣ ግዴታውንም አብሮ መቀበል ሳይታለም የተፈታ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ ግዴታውን በቃል ኪዳን መቋጨት ከቻለ ኢሳት ከቀፈፋና ለመክሸፍ ይድናል።

የእኔ ምኞት ኢሳት በኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን ተገንብቶ በሕገ ኀልዮት እየተመራ አዲስ ዓላማ፣ አዲስ የአሠራር ዘዴ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ጉድለቶችን ሁሉ አውቆ በጥንቃቄ እየነቀሰ አዲስ የመተማመንና የመተባበር ባህል ይፈጥራል የሚል ነው፤ (እኔ ቃል ኪዳን የምለው ሁለት ቁም-ነገሮችን የያዘ ነው፤ በአንድ በኩል እውነትን አለመፍራት (ወይም በጥሩ መልኩ ለእውነት መቆም፣) በሌላ በኩል ለአንድ የጋራ ዓላማ የራስን ግዴታ ሳያስተጓጕሉ ለመወጣት በቆራጥነት መቆም፤ ስንት ልጆች አሉህ ተብሎ ሲጠየቅ ሁለት ወይም ሦስት እያለ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ የሚመልስ ለቃል ኪዳን አይበቃም፤) ከሩቅ እንደማየው ጥቂት ሰዎች ኢሳትን በቃል ኪዳን ተይዘው ሲጥሩ አብዛኛው ደግሞ በአጋጣሚ እንደተመቸውና እንደፈለገ የተቻለውን የሚያደርግ ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን የሌለው ነው፤ ከተሳሳትሁ ደስ ይለኛል፤ አስተያየቴ ትክክል ከሆነ ኢሳት አይዘልቅም፤ መክሸፍ ዕጣ-ፋንታው ይሆናል።

ዓላማውን ሳይመታ እንዳይከሽፍ ኢሳት በቃል ኪዳን መታሰር አለበት፤ እንዴት? ቢባል፣ አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በአማካይ በወር አሥር ዶላር ለመስጠት ቃል ኪዳን ቢገቡና የየዓመቱን ግዴታቸውን በአንዴ ቢወጡ፣ በወር አሥር ሚልዮን ዶላር (በዓመት አንድ መቶ ሃያ ሚልዮን ዶላር) ኢሳትን  ኢትዮጵያዊነትን የሚያስከብር የሰላምና የፍቅር፣ የብልጽግናና የተስፋ መድረክ ሊያደርገው ይችል ነበር፤ አብዛኛዎቹ ችሎታው ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለኢሳት የሚገቡት ቃል ኪዳን ለጥሬ ሥጋና ለመጠጥ የገቡትን ቃል ኪዳን ካላሸነፈ ታማኝ በየነን በያገሩ እየላከ በሚያደርገው ዓመታዊ ቀፈፋ ኢሳት ይገነባል ብዬ ለማመን ያሰቸግረኛል፤ በኢሰመጉ አይቼዋለሁ።

ቀፈፋ ወይም ልመና አንዱና ዋናው የባህል ሕመም ነው፤ እያንዳንዳችን ከዚህ ሕመም ለመዳን በራሳችን ላይ መዝመት የሚያስፈልገን ይመስለኛል፤ በተለይ በአገር ጉዳይ፣ በወገን ጉዳይ ማን ነው ለማኝ? ተለማኙስ ማን ነው? ስለአገሩና ስለወገኑ ችግር የማያውቅ አለ? ለማወቅ የማይፈልግ ይኖራል እንጂ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ችግር ገሀድ ነው፤ በአስከፊ መልኩ ለመረዳት የሚፈልግ በመረረ ቋንቋ የተጻፈውን የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ሀገሬ ገበናሽ (ክፍል አንድ፣  ክፍል ሁለትና ክፍል ሦስትን)  ያንብብ።  አንብቦ ካላለቀሰ፣ አልቅሶ ‹‹ምን ላድርግ!›› የሚል ቁርጠኛነት ያላደረበት በዓመት አንድ ጊዜ በታማኝ ቀፈፋ አገሩንና ወገኑን መርዳት አይችልም፤ እምነቱ ካለ፣ ስሜቱ ካለ በገንዘብ የሚደረግ ማናቸውም እርዳታ የመጨረሻው፣ መናኛው ነው፤ መናኛ የሚያደርገው የገንዘቡ መብዛት ወይም ማነስ አይደለም፤ ለአገርና ለወገን ከዚያ በጣም የበለጠ የሚከፈል ዋጋ በመኖሩ ነው፤ አያቶቻችንና ቅምአያቶቻችን የከፈሉት ዋጋ በገንዘብ አይመነዘርም፤ እነሱ በሕይወታቸው ያስገኙልንንና እኛ በገንዘብ የሸጥነውን ኩራትና ክብር በገንዘብ ብቻ አናስመልሰውም፤ ቃል ኪዳን እንግባ!

https://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2013/05/19/453/ ‎

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

19 Responses to ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ

 1. Fiseha Gebremariam says:

  I have found the discussion which is going on is very important.Thanks to all of you who have participated in this discussion ,as you have thought me a lot. Thank you PROF. & long live to you. May God show you success of your effort.

 2. Andinet says:

  ውድ ደረሰ – ፕሮፌሰር ለአትዮጵያ ችግር መፍትሔው ሰላማዊ ትግል ብቻ ነው ብለው ስለሚምኑ ከሰላማዊ ትግል ውጭ ሌላ መፍትሄ አለ ብለው ለሚስቡ ክፍሎች ኢሳት መድረክ መስጠቱ የኢሳትን መክሽፍ መገለጫ እንደሆነ እንዲህ ገልጸውታል፡፡
  “ የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ ………………………………የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርን አያስገኝም።”
  እኔም ‹ለሃገራችን ችግር መፍትሄው አንድ መንገድ (የእርሶ መንገድ) ብቻ አይደለም› ያልኩት ኢሳት ነጻ ሚዲያ እንዲሆን የምንሻ ከሆነ ከመርህ አኳያ ሁሉንም በእኩል መድረክ መስጠት እንዳለበት ለመግለጽ ፈልጌ ነው፡፡ ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡
  ውድ ሰናይት – በተወሰነ መልኩ ግንዛቤዬን እንዳስተካክል (ታማኝን በተመለከተ) ስለጠቆምሽኝ እና ስለ ቀና አስተያየትሽ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
  ውድ ቴዲ – የኔ አስተያየቶች ፕሮፌሰሩን ከኢሳትም ሆነ ከአድናቂዎቻቸው ጋር ለማላተም-ቤንዝን፤ አይነት ሆነው አገኘሃቸው ? በመጀመሪያ ነገር አንተ ለአድናቂዎች የምትሰጠውን ትልቅ ቦታ አሳቸው አንተ እንደምትመኘው አይነት ሰው ስላልሆኑ ቦታ አይሰጡትም፡፡ ፕሮፌሰሩ የሚጽፉት ነገር ለእሳቸው ዕውነት ወይም ምክንያታዊ ይሁን እንጂ ማንንም ያስከፋ ወይም ከአድናቂዎቻቸው ያላትማቸው እሳቸው ግድ አይሰጣቸውም፡፡ ባይሆን ሃሳባቸውን በስህተት ተረድቼው ሊሆን ግን ይችላል፡፡
  አብርሃም ደስታ በፌስቡክ ገጹ ሰዎች በትክክል ሃሳቡን ሳይረዱ ሲቀሩ ምን እንደተሰማው ሲገልጽ “ የህይወት መጥፎ አጋጣሚ ሰው ሲከዳህ ወይ ሲበድልህ … አይደለም፤ መጥፎው አጋጣሚ ሰዎች በስሕተት እንደተረዱህ ስትረዳ የሚኖርህ የውስጥ ስሜት መሆኑ ዛሬ ስለ መንግስቱ ኃይለማርያም በለጠፍኩት ፅሑፍ መረዳት ችያለሁ።” ብሎ ነበር፡፡ ስለዚህ የእሳቸው ልፋት መና እንዳይይቀር እና ለሀገራችን ችግር በሚያቀርቧቸው መፍትሄዎች በተቻለ መጠን ሰዎች በስህተት እንዳይረዷቸው ሲሉ እሳቸው በጽሁፎቻቸው ጥንቃቄ ቢያደርጉ የተሻለ ነው የሚል ሃሳብ አለኝ፡፡ በመጨረሻም ለፕሮፌሰር መስፍን ረጅም እድሜ እንዲሁም አሳቸው በዕድሜያቸው የሚመኟትን ኢትዮጵያ ፈጣሪ እንዲያሳያቸው ምኞቴ ከፍ ያለ ነው፡፡

 3. Teddy says:

  የአቶ “አንድነት“ አስተያየቶችን መልሶ ላነበባቸው፤ እንዲሁ አሳቢ መስለው፤ የፕሮፌሰሩን ጽሑፎች ጥላሸት ለመቀባት-ሰበብ ፈላጊ፤ ሰዉየውን ከኢሳትም ሆነ ከአድናቂዎቻቸው ጋር ለማላተም-ቤንዝን፤ አይነት ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ለዚህም፤ አስተያየታቸውን ማየት በቂ ነው። መቸ ይሆን ከእንዲህ አይነት የጭቃ እሾሆች የምነገላገለው?

 4. Deresse says:

  Deresse

  ፐሮፌሰር መስፍን

  ስለ ፅሁፍዎ አስተያየትዎ ትችትዎና ምክርዎ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ይህ ከአንድ አገር ወዳድ ምሁር የሚጠበቅ ተግባርዎ ሁልጊዜ ያስደስተኛል፡፡

  በተረፈ

  አንደኛ ዳን የተባሉ አስተያየት ሰጪ በ19/05/13 ባሰፈሩት አስተያየት አርበኛና ባንዳ ብለው የሚከፋፍሉት ጎራ መኖሩን ነቅፈዋል፡፡ ሁለተኛ አንድነት የተባሉት ግለሰብ ደግሞ በ20/05/13 ባሰፈሩት ፅሁፍ ፐሮፌሰር መስፍን ኢሳትን ለማሻሻል በሚል የሰጡት አስተያየት ከጠቃሚነቱ ይልቅ ጎጂነቱ የበለጠ ጎልቶ የታያቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

  ሁለቱም አስተያየት ሰጪዎች ፕሮፌሰር የሰጡትን የአስተያየት ጥልቀት በሚገባ የተረዱት አይመስለኝም፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሳቀርበው እኛ ኢትዮጵያውያን የሃገራችንን ችግር ለመፍታት እንችል ዘንድ ከጊዜያዊ ስሜት ተላቀን ፅናትና ቁርጠኝነት ሊኖረን ይገባል የሚል ፅሁፍ ነው ያነበብኩት፡፡

  ይህንን ከላይ የተመለከተውን ሃይል ያለውን ሃሳብ ትተን ወይንም አቅጣጫ ቀይረን አርበኛ ማነው? ባንዳስ ማነው? ወዘተ… በሚሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ የፅሁፉም አላማ ይሄ አይመስለኝም፡፡

  በመጨረሻም አንድነት ‹ለሃገራችን ችግር መፍትሄው አንድ መንገድ (የእርሶ መንገድ) ብቻ አይደለም› በማለት ፕሮፌሰርን ተችተዋል፡፡ የእርስዎን የመፍትሄ ሃሳብ ቢያስቀምጡ ኖሮ ሚዛናዊ በሆኑ ነበር፡፡

  • Dan says:

   ውድ ደረሰ _ ፕ/ር መስፍን በጣም የሚያዘወትሯት ግድፈት ስለሆነች (በኔ ዕይታ ማለቴ ነው) አጋጣሚውን በመጠቀም እንዲያስተካክሉ ጠቆምኩ እንጂ በዚህ ክፍል ማስተላለፍ የፈለጉትን መልዕክት ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም:: የውይይቱን አቅጣጫ ለማስቀየስም አልነበረም ፍላጎቴ::

 5. Andinet says:

  በየሀገሩ እየዞረ ለኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ የሚደክመውን የታማኝ በየነን ጥሩ ተግባር ዓመታዊ ቀፈፋ አሉት ፡፡ይህም ኢሳትን እነደማይገነባ ገለጹ፡፡ ኢሳትን በቅንነት ለማጠናከር ከተፈለገ አሁን እየተደረገ ያለውን ጥረት አድንቆ የተሻለ ነገር መጠቆም አንድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን እርሶ የማይወዱትን ነገር ጥላሸት እየቀቡ “ ኢሳትን ለማሻሻል” በሚል ዓላማ መምከር የበለጠ ጎጂ ነው የሚሆነው፡፡
  ደግሞስ በሰላማዊ መንገድ ይህን ስርዓት መቀየር አይቻልም ብለው የራሳቸውን የትግል ስልት ቀይሰው ለዚህም ኢሳትን እንደመድረክ የሚጠቀሙትን ደግሞ ኢሳት “ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል” በማለት ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እነደማይጠቅም ገለጹ፡፡
  ለሀገራችን ችግር መፍትሄው አንድ መንገድ (የእርሶ መንገድ) ብቻ አይደለም፡፡ኢሳትን ለማሻሻል ቃል ኪዳን ስንገባ ከላይ ዳን እንዳለው የሚከፋፍሉትን ጎራ መጀመሪያ ያቁሙ፡፡ የእርሶን ምክር ለኢሳት የሚጠቅመው ያኔ ነው፡፡

  • degankahaway says:

   አንድነት እና ዳና
   ክፍፍሉ ታዲያ በዘር ቢሆን ይሻላል ነው የምትሉት? ለዚች አገር የሰራና ያልሰራ ብሎ እንደመከፋፈል አድርገህ ለምን አታየውም! አሁን እንደው እውነቱን እንናገር ብንል ኢትዮጵያ ውስጥ አርበኛ እና ባንዳ የለም ለማለት ነው፡፡ እኔ ከፕሮፍ እንደተረዳሁት አርበኛ ማለት ለኢትዮጵያ ብልፅግና የሚሰራ ማለት ሲሆን ባንዳ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትጠፋ (አትጠፋም እንጂ) የሚለፋ እንደማለት ነው፡፡ ይህ ታዲያ አንተንና ዳንን የሚያስከፋችሁ ለምንድነው?

   በተጨማሪ “ለሀገራችን ችግር መፍትሄው አንድ መንገድ (የእርሶ መንገድ) ብቻ አይደለም” አንድነት ብለሃል ይህንን ለፕሮፍ የሚነገራቸው አይመስለኝም ሆኖም ግን አሁንም ለውጥ ለማምጣት እየተጨራረስን መሆን እንደሊለበት ግን መታየት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል ፕሮፍም ይህንን የሚያምኑበት ይመስለኛል፡፡

   ፕሮፍ በተለያዩ ወቅቶች ለአስተማሪና ለምክር አዘል ጹሁፎችዎ ምስጋናዬን አቀርባለሁ
   እግዚአብሂርም ዕድሜ ይስጥልን
   እናመሰግናለን

   • Dan says:

    “አሁን እንደው እውነቱን እንናገር ብንል ኢትዮጵያ ውስጥ አርበኛ እና ባንዳ የለም ለማለት ነው፡፡ እኔ ከፕሮፍ እንደተረዳሁት አርበኛ ማለት ለኢትዮጵያ ብልፅግና የሚሰራ ማለት ሲሆን ባንዳ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትጠፋ (አትጠፋም እንጂ) የሚለፋ እንደማለት ነው፡፡ ”

    First of all, I don’t think Pr. Mesfin would define it this way. As I have read most of his books and articles, his concept of አርበኛ እና ባንዳ is different from your view; and lacks scholarly substance, just as yours. Mesfin calls some as ባንዳ , because he thinks they stand against “the interest” of the country. But whose interest represents the interest of the country? Why do people stand against their own country/people in the first place? Why do the Ginbot-7 members stand against the “The Grand Ethiopian Renaissance Dam “? Why do some stand against “The grand investment on land”? Is it because they are ባንዳs? Was it their very nature of ባንዳ that made some, in the past, to stand against the then Governments? to standby foreign enemies? You see, that is how people react when they are oppressed; yet, the oppressors regard them as traitors (ባንዳs). It’s simply awkward to hear such a term frequently from one of the most respected academician, politician, author and senior citizen.

    I would like to read a better definition, if you have any, than this shallow one. Yours is even the worst definition I ever encountered. I don’t believe that there is an Ethiopian who wishes the worst to his own country; who don’t want to see a prosperous, peaceful, and powerful Ethiopia. ባንዳ ማለት ኢትዮጵያ እንድትጠፋ የሚለፋ ኢትዮጵያዊ ማለት ከሆነ … it simply means that there is no ባንዳ at all.

   • Andinet says:

    ውድ degankahaway,
    በመጀመሪያ ነገር ክፍፍሉ ለምን ያስፈልጋል ? ኢሳት ነጻ ሚዲያ እንዲሆን ከፈለግን ሁሉም በኢሳት መድረክ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በተለይም ለሀገራችን የራሳቸው መፍትሄ ይዘው ለሚመጡት ነገር ግን በተለያየ ዘዴ ድምጻቸውን እንዳያሰሙ ለታፈኑ ዜጎች ፡፡ ያመጡት መፍትሄ ባይጥመንም ድምጻቸውን እንዲያሰሙ መድረክ ኢሳት መፍጠር አለበት፡፡ ህዝቡ ደግሞ የሚጠቅመውን ስለሚያውቅ የሚበጀውን ይመርጣል፡ ይደግፋል………

  • Senait says:

   Dear andinet, why you don’t think positive!!

   • Andinet says:

    እኔ ለማለት የፈለኩት ምንም ሳይሰራ ዝም ብሎ ከሚቀመጠው ከአብዛኛው ሰው ይልቅ በማንኛውም መንገድ የሀገራችንን ችግር ለመፍታት ጥረት የሚያደርገውን ሰው መንገዱን ባንደግፈው እንኳን ቢያንስ የጋራ ዓላማ ስላለን ለምን በመጀመሪያ ጥረቱን “Appreciate” አድርገን አካሄዱ እንዲያስተካክል ለምንድን ነው በጨዋነት የማንተቸው ? ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለምን እዚህ ላይ አናሳይም? እርስበርሳችን ገንቢ በሆነ መልኩ ካልተራረምን እነዴት ነው ከሌላኛው ወገን ጥሩ ነገር የምንጠብቀው?
    ምናልባት ከፕሮፌሰር ብዙ ስለምጠብቅ ወይም የፕሮፌሰር የእስካሁን የልፋት ውጤት ፍሬ አለማፍራቱ ስሜታዊ አርጎኝ ይሆን ይሆናል፡፡ “Pessimist “ ሆኜ ከሆነ በጣም ይቅርታ እህቴ ፡፡

   • Senait says:

    Dear Andinet, thank you so much for your kind words. I can feel your concern and worries. When i come to Prof’s point, I don’t think he is criticizing Tamagn Beyene (If you read the previous articles, prof already appreciate Tamagn for his great job): However, as an institution ESAT should not relay on generating income this way and the society should be the owner and as well responsible to sustain its continuity, here is the core idea of the article.
    Finally God bless Ethiopia and long live for the Prof.

 6. sb23 says:

  GOD BLESS U MESFIN(PROFF)!!LONG LIVE FOR ETHIOPIAN AND U!!!!!!!!!!!!!1

 7. Yihonal Ayikerm says:

  Dink new. it is true. How we can make sure that we can convience the people. ESAT itself has to work on this idea.
  May God Bless Ethiopia

 8. Dan says:

  እንደተለመደው ድንቅ ምክር ነው, ፕሮ! ሆኖም ከእርሶ ሁሌም ስሰማት የምትቀፈኝ አነጋገር አለች በዚችኛው ጦማሮ:: ይኸውም፦ “አርበኛውና ባንዳ” ብለው ዛሬም ድረስ የሚከፋፍሉት ጎራ መኖሩ ነው:: በዚህ ላይ ትንሽ ሚዛናዊ ይሆኑ ዘንድ የዘሪሁን ተሾመን “ኩርኮራ” (መጽሃፍ) መግቢያዋን ብቻ እንዲያነቡ (አንብበውት ከነበረም ድጋሚ እንዲያነቡ) ብጋብዞት ከድፍረት እንደማይቆጥሩብኝ ተስፋ አደርጋለሁ::

 9. Lambadyna says:

  Gashi Mesfini Hulachine zime beline gini Antene yeminageri Yemiyanagiri yemoralei ena yeewiketi Abati selesetenei E/rinei enameseginaleni. Ena gidatayeni ewetaleiweii “KAlei egebalewi”

 10. Teddy says:

  ክቡር ፕሮፌሰር፤ ውሳጣዊ ስሜትን ኮርኳሪ፣የምናደርገውን ቆም ብለን እንድናስብ መሪ ለሆነው ጽሑፍዎ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር እንዲህ አይነቱን ችግር ነቃሽ፣ አቅጣጫ መሪ እና መፍትሄ ፈላጊ የሆኑትን አባት ይጠብቅልን።
  አንባቢዎች ሆይ፤ የክቡር ፕሮፌሰርን መነሻ ሃሳብ (አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በአማካይ በወር አሥር ዶላር ለመስጠት ቃል ኪዳን ቢገቡና የየዓመቱን ግዴታቸውን በአንዴ ቢወጡ) ለመደገፍ እንወስን፤ ወስነንም ወደ ተግባር እንቀይረው። ውሳኔአችንንም ለኢሳት ቀጥታ በውስጥ ስልካቸው፤ ወይም በጽሑፍ እንግለጽ፤ ገንዘቡንም እናስገባላቸው።
  የኢሳት ሃላፊዎችና ባልደርቦችም፤ የሬድዮና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ቢያዘጋጁ። የፕሮግራሙንም መሪ ቃል፤ ዘመቻ መስፍን ወልደማሪያም-ኢሳትን እንደ ብረት ለማጠንከርና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለስልጣን ለማብቃት እልህ አስጨራሽ ትግል ከ …እስከ… ቀን (የሚል አይነት ነገር ቢሆን)፤ ለዚህ ምላሽ የሰጡትን የኢትዮጵያውያን ወገኖች ለደህንነታቸው ሲባል ቁጥራቸውን ብቻ እንዲሁም የገባውን የገንዘብ መጠን በየጊዜው ኢትሳት ይፋ ቢያደርግ ፤ ፕሮፌሰሩ የጠቆሙት መፍትሄ እውን ይሆናል የሚል እምት አለኝ። እባካችሁ እንሞክረው። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ።

 11. DASSENNECH says:

  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፡
  እግዚአብሄር ይባርኮት፡ ከ90ሚሊየን ህዝብ መሃል አንድ ሚሊየን ከእሳት ጋር ቃል የሚገባ ያውም ለመናኛ 10 ዶላር ወይም ዩሮ ካልተገኘ እንደ ሃገር፤ እንደ ህዝብ ወድቀናል ማለት ነው፡
  እኔ ከእሳት ጋር ቃለ ገብቻልሁ፡ አንባቢ ሆይ አነቺስ? አንተስ?

Comments are closed.