ዛሬ ደግሞ—

https://www.facebook.com/mesfin.woldemariam.5?hc_location=timeline

ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ —

1. የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤
2. በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤
3. የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤

ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

19 Responses to ዛሬ ደግሞ—

 1. gedeyon says:

  betam yemigerm newu ..ahun professor mesfen banda sibalu !!! yasekalem ,yanadedalem, yasgeremalem.. mahemed amin ye Ethiopia tekorkuari sibalem edezawu yasekal ….weye alemawok..(ante tadelehal aygebahem) endetebalewu sewuye newu filimon mallet..demo eko sele talian worera mukera tarikem liawera yemokeral . talianen yenneman abatoch enna ayatoch endetewagu, yeneman demo menged simeru endeneber filimon becha sayhon talianochum yawukalu..aye filimon tadelehal aygebahem lebeleh bedegami.. hode becha ,bigebahma noro…

 2. Pingback: Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር | Danielberhane's Blog

 3. ፀዋር says:

  ለየትኛው አባይ ?

  ኢትዮጵያዊው ወታደርና ታጋይ ለአስራሰባት አመታት እርስበእርስ ሲፋጅ የኖረው ለማን ነው ?

  ተፋጅቶ ሲያበቃ ብትንትኑ የወጣውና ዲዞልቭ የተደረገው ለማን ነው ?

  ተበታትኖ ሲያበቃ ድጋሚ ለአገራዊ ጥሪ ኢትዮጵያዊ ግዴታውን በመወጣት በጋራ ተሰባስቦ በባድሜ የሞተው ለማንና ለምንድን ነው ?

  በባድሜ ሞቱ የውሻ ሞት ሆኖ የቀረው : ደሙ ደመከልብ ሆኖ የቀረው ለምን ሲባል ነው ? ተሳስተናል ይቅር በለን ተባለ ? ወይስ ሞቱንና አካለ ጎደሎነቱን ተሳለቁበት ?

  የሶማሊያ ጦርነት የማን ጦርነት ነበር ? ለኢትዮጵያ ጥቅም ወይስ ለወያኔ የውጪ ምንዛሪ ምንጭ ማስገኛ “ outsourced” ጦርነት ?

  ለዚህ ዶላር የሞተው ዜጋ ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል ? እንደ አገርም እንደ ህዝብም ስለሞተው ወታደር አትጠይቁን : እኛም በኮንትራት አገሪቱን ማስተዳደር (በኮንትራት የጦርነት ውል መፈራረም ) እንጂ የሞተውን ቁጥር ለማንም የማሳወቅ ግዴታ የለብንም አልተባልንም ?

  አባይ ግድብ ለማን ነው ? የኢትዮጵያ ገበሬ መስኖ ሊያለማበት ? አልምቶ ልጆቹን ሊያስተምርበት ? አስተምሮ ህይወቱን ሊቀይርበት ? ወይስ የውጪ ምንዛሪ ማስገኛ መንገድ ? የተገኘውን ማስኮብለያና ባለስልጣኖችን መባለጊያ ? በአስር አመት ውስጥ ከአስር ቢልዮን ዶላር በላይ ወደ ውጪ አላስኮበለሉም ? በ 6ሺ ወርሃዊ ደሞዝ የአለማችን ሃብታም ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚንስተር አላሰኙንም ? አብረው ዘርፈው ሲጋጩ መሳቂያችን ሆነው አልሰነበቱም ? እኮ ለማንና ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊው የሚሞተው ?

  መጥፎ አስተዳደራቸው አንገሽግሾት ሰልፍ ቢወጣ ጆሮ ዳባ ልበስ ብቻ ብለው አበቁ ? ወይስ የግብጽና የሻዕብያ ሴራ እንጂ አስተዳደራችን እንከን የለበትም ሲሉ ብህዝብ ግፍ ተሳለቁብን ? ለምንድን ነው የተገፋው : የተሳለቁበት : የረገጡት እንዳሻቸው የተጨማለቁበት ህዝብ ለአባይ የሚሞተው ? ለየትኛው አባይ ?

  ከኖረበት ከቀዬው እትብቱ ከተቀበረበት ህጻን : ልጅ : አዋቂ : እርጉዝ : እና አረጋዊ በዘሩ ምክንያት አልተፈናቀለም ? መድረሻ አሳጥተውት ወፍ ዘራሽ ሆኖ አልቀረም ? አባይ ቢገደብ ባይገደብ በቀዬው የመኖር ዋስትና ለሌለው ኢትዮጵያዊ ምኑ ነው ? አባይ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም አይገነባም :: ግብጽም ኢትዮጵያን ሊወር አልመጣም :: ታድያ ለአባይ የምንሞትበት ምክንያት ምንድነው ?

  አባይ መገደብ ካለበትም በህዝብ ስምምነትና ይሁንታ ነው :: ደሞዙን አስገድደው ሊነጥቁት ይችላሉ : ነፍሱን በአጋዚ ስናይፐር ከስጋው ሊነጥሏት ይችላሉ : በግድ ማዘመትና ማዋጋት ግን አይችሉም :: በግድ የዘመተ ወጣት ውጤቱ ምን ሊመስል እንደሚችል በባድሜ አይተውታልና ይማራሉ ባይባልም የሚያዛልቃቸው እንዳልሆነ አያጡትም :: አባይ መገደብ ካለበትም : በባዶ ሜዳ በቀረርቶ አይደለም :: በቅድምያ የህዝብን ጥያቄ መመለስ የግድ ይላል :: ቀጥሎም በጥጋብና እብሪት ሳይሆን በበቂ ዲፕሎማሲ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ይሆናል :: አለበለዚያ እስከዛሬ ድረስ መስሎት ራሱን መስዋእት ያደረገው ሁሉ : የጥቂት ባለጊዜዎች ካልሆነ በስተቀር ለማንም ፋይዳ ያለው ነገር አላስከተለምና ትርፉ ደመከልብነት ብቻ ይሆናል :: እና አንሞኝ :: መሞትም ካለብን ከአባይ በፊት ለኢትዮጵያ እንሙት!

 4. Walelgne says:

  It is quite saddening to read some of the comments — instead of focusing on the critical issues raised, they prefer to frivolously bash the personality of the Professor with complete lack of basic set of moral and ethical values. I don’t think any rational Ethiopian will question the records of Professor Mesfin on issues related to famine, human rights and poverty at large. If it were not Ethiopia, he would have won several accolades for his effort.
  Any sensible person would agree that war should always be a last resort — particularly in countries where authoritarian and suppressive regimes are at the helm. What is wrong to point out that it is imperative to know our enemies as much as we can!!

 5. haq says:

  መምሪ በተባለው የግብጽ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት የተደረገ ውይይት)

  የነጻነትና ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር እንዲህ አሉ፤

  «ድምጼን አሰምቼ በግልጽ መናገር የምፈልገው ነገር ሁሉም አማራጮች ለእኛ አስፈላጊዎች መሆናቸውን ነው። እናም ሁሉንም አማራጮች እንደግፋለን፤ ነገር ግን ሂደቱ በየደረጃው መሆን ይገባዋል። የንግግር ግንኙነታችን ሂደቱን መቀየር ካልቻለ ወደዓለም ዐቀፉ የግልግል አካል እናቀርበዋለን። ይህም ካልተሳካ ማንም ሊገምተው እንደሚችለው የውሃ ደኅንነታችንን ለመከላከል ወደሌላ አማራጭ እንገባለን። ምክንያቱም የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ለእኛ የሞት ወይም የሕይወት ጉዳይ ነውና።

  የአልኑር ፓርቲ ፓርቲ ሊቀመንበር በተራቸው እንዲህ አሉ፤

  አሁን እየተካሄደ ባለው የዐባይ ማዕቀፍ ላይ ግብጽ ከተስማማች አደገኛ ስትራቴጂካዊ ስህተት መፈጸሟ ነው። ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ አሜሪካ፤ እስራኤልና ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ኋላ አሉና። ምክንያቱም በዚህ ስምምነት ግብጽን በመጉዳት ርካሽ የፖለቲካ ጫና ለማሳረፍ ሲሉ ነው። እኛም እንደእነሱ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ 35% ኦሮሞ ስለሆነና ኦሮሞም ለመገንጠል የሚዋጋለት ኦነግ የሚባል ድርጅት ስላለው ለእሱ ሁለመናዊ ድጋፍ ማቅረብ አለብን። በሀገር ቤት ያለው ፖለቲካዊ የተቃውሞ መድረክ ደካማና ልፍስፍስ ስለሆነ ለመገንጠል በሚዋጉት እንደኦጋዴን ነጻነት ግንባር ያሉትንም መደገፍ ይገባናል። ይህም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የተቀናጀ ጫና እንድናሳርፍ ያስችለናል። ይህ ሁሉ ተደርጎ ውጤት ካላስገኘልን ሌላው አማራጭ ለግብጽ ኅልውና አደገኛ የሆነ ማንኛውንም ግድብ ለማውደም የምንችልበት ሁኔታ መፍጠር ነው። ለዚህም አስተማማኝ የደኅንነት መረጃ መኖር አለበት። ምክንያቱም አንዳንድ ጠበብቶች ግድቡን መጀመር በራሱ አደገኛና ጦርነት የማወጅ ያህል እንድንቆጥር በቂ ማስረጃ ነው እያሉን ነውና።

  የአል አዝሃር ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖት መምህር የሆኑት ደግሞ በተራቸው፤

  አስታውሳለሁ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግብጽ በመጣበት ወቅት በግብጽ ሕዝብ ላይ አላግጦ ነው የሄደው። ዐባይ ክንፍ የለውም፤ ወደእስራኤልም አይበርም አለ፤ ነገር ግን ማንኛውም ህዝብ እንደሚያውቀው የግብጽ ሕዝብም ያውቃል። የዓባይ ወንዝ በቀይባህር ስር የሚሄድበት የራሱ የቧንቧ መስመር ስውር ክንፍ አለው። ማንም ሀገር በቧንቧ መስመር ውሃ ወደሀገሩ እንደሚያስገባ ይታወቃል፤ ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን በመቃወም ዐባይ ክንፍ አለው ብለዋል።

  የገድ አልተውራ ፓርቲ ሊቀመንበር ደግሞ ተራቸውን ጠብቀው እንዲህ አሉ፤

  እንደዚህ ይባል ወይም አይባል እንደሆነ አላውቅም፤ ነገር ግን አንዱ ጓደኛዬ ቅድም እንዳለው ኢትዮጵያ ብዙ ተቃዋሚዎች እንዳሏት ይታወቃል፤ እዚያም የተለየ እንቅስቃሴ እያየን ነው። የግብጽ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩ ምን ያደርግልናል? አስፈላጊ ነገር አሁን የፖለቲካና የመረጃ ክፍሎቻችን ብቻ ናቸው። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመርኩዘን ሚና መጫወት አለብን። ይህንን ማስኬድ መቻል በትንሽ ወጪ ብዙ መስራት የሚያስችለን ሲሆን አጸፋዊ አደጋውም የቀነሰ ነው። በደንብ አድርገን በውስጥ ጉዳያቸው ብዙ መስራት ከቻልን የመንግስታቸውን ዐቅም ማዳከም ይቻለናል። አንድ የኢትዮጵያ ጋዜጣ እንዳለው ግብጽ የጦርነት ሃሳብ የላትም። ይህንን የማድረግ ብቃት የላትም፤ ሚሳይል የላትም፤ አውሮፕላን የላትም፤ ቢኖራትም ሱዳን በክልሏ ላይ ይህ እንዲደረግ አትፈቅድም ብሏል። በእርግጥም የሱዳኖች ሁኔታ በጣም የሚያሳምም ነው። ሁኔታዋ ማድረግ ከሚገባት አንጻር በጣም ደካማ ነው። ይሁን በእኛም በኩል መረጃ የማፍሰስ ችግር አለ። ግብጽ የጦር አውሮፕላን ልትገዛ ነው፤ በአየር ላይ ነዳጅ መሙላት የሚችል አውሮፕላን አላት ወዘተ የሚሉት መረጃዎች መውጣት አለባቸው፤ በእርግጥ ባይሆንም መረጃው በዲፕሎማሲያዊ ጥረታችን ላይ ራሱ ተጽዕኖ ሊያመጣ ይችላል።

  የሪፎርምና ደቨሎፕመንት ፓርቲ ሊቀመንበር ደግሞ ተራውን ተረክበው እንዲህ ዶለቱ፤

  እኛ ባለን ግንዛቤ የብሔራዊ ቡድናችን ኢትዮጵያ ሄዶ ባደረገው ጫወታ ተጽእኖ በመፍጠር ማሸነፍ መቻሉን ነው። ብሔራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኑና እጅግ በአመርቂ ውጤት ጫና መፍጠር መቻሉ በራሱ የሚያሳየው እውነትም ግብጻውያን ጫና የመፍጠር ጥበብ እንዳለን ነው። ትልቅም ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም አለን። የግብጽን ቤተክርስቲያንና የአልሃዛር ስኮላሮችን መጠቀም እንችላለን። አንዳንዶች የጦርነት አማራጮች ሊኖር እንደሚችል ያወራሉ። የሚወራው ነገር በተግባር አስቸጋሪ ነው። እንደዚህ ዓይነቱን እሳቤ መነቀፍ ይገባዋል። ከዚህ ይልቅ የግንኙነት ምህዋራችንን ከኤርትራ፤ ከሶማሊያና ከጅቡቲ ጋር ብናደርግ ለደኅንነታችን ክፍሎች ትልቅ መስክ ነው። ዙሪያቸውን መስራት አለብን። ይህንን ማድረግ ጥሩ ከመሆኑም ባሻገር ግንኙነት የማድረግ መብታችንም ስለሆነ ተገቢ ነው። ተስፋችን ሲጨልም ደግሞ ሃሳባችንን መፈጸም የምንችልባቸው በተዘዋዋሪ አንድ መቶ መንገዶች አሉን። ሁሉንም እንሞክር።

  የኢስላሚክ ሌበር ፓርቲ ሊቀመንበር ደግሞ ምኞታቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፤

  እኔ ከጠላቶቻችን ጋር ጦርነት የምናደርግበት ቀን ናፍቆኛል፤ በእርግጥም ከእስራኤልና ከአሜሪካ ጋር። ጦርነቱ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎ ተገቢውን ፍትህና እርጋታ የሚያመጣ መሆን አለበት። ምንም እንኳን ይህ ውይይት ምስጢራዊ ውይይት እንደመሆኑ ሁሉንም ነገር በምስጢር መያዝ ይገባናል። ውይይታችን ወደሚዲያ ሾልኮ መውጣት የለበትም። በእህታችን በባኪናም በኩል በግልጽ ከሚወጣው በስተቀር። ሕዝባዊ የሀገራዊ ደኅንነት እቅድ በግልጽ እንዲኖር እንፈልጋለን። እኛ እንዲህ ቢሆንም እንኳን………. እሺ…..መልካም………እኔ የማነሳቸው ነጥቦች አግባብ ከመሆናቸው ጀርባ በእርግጥም ምንም ምስጢርነት የላቸውም። ውጊያችን ከአሜሪካና ከእስራኤል ጋር እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር አይደለም። ስለዚህ ውጊያችንን ለማስኬድ ፤ ይህ የኔ ሃሳብ ነው……….( ፕሬዚዳንት ሙርሲ ጣልቃ ገቡና፤ ይህ ውይይት እኮ በቀጥታ ስርጭት ላይ ነው ያለው! አሉ) የኢስላሚክ ፓርቲው ሊቀመንበርም፤ እኔም የምስጢር እቅድ ወይም ፕላን ማብራሪያ እየሰጠሁ አይደለም! ሲሉ በጉባዔው ሳቅ ሆነ። ቀጥለውም «እኔ ያልኩትን እኮ ማንም ሀገር የሚያደርገው ነው፤ በሌሎችም ሲባል የቆየ ነው» አሉ። (የጉባዔው ረጅም ሳቅ!!)
  ማንም ሀገር ለከባቢያዊ ጥቅሙ የሚያደርገው ነው። እኔ ለግብጽ ሕዝብ የምለው ማንም ተነስቶ የውሃ አቅርቦትህን ሊዘጋ አይችልም ነው። የግብጽን ሕዝብ የዓለም አደገኛው የጽንፈኝነት መንገድ እንዲገባ ካልፈለጉ በስተቀር ይህን አያደርጉም። እስኪ አስቡት 80 ሚሊዮን ግብጻዊ ውሃ ሲዘጋበት በአሜሪካና በእስራኤል ላይ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል?

  ፕሬዚዳንት ሙርሲ፤ የልባቸውን በልባቸው ይዘው፤ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ደስ የተሰኙበትን ገታራ ውይይት አለዝበው እንዲህ ሲሉ ደመደሙ።

  «እኛ ለሰሜንና ደቡብ ሱዳናውያን የከበረና የተትረፈረፈ አክብሮት አለን» አሉና የሱዳንን ዳተኝነት ሸነገሉ። «ውሳኔዎቻቸውን ሁሉ እናከብራለን» ሲሉ በማሞካሸት ጠላት ማፍራት እንደማይገባ በውሰጠ ታዋቂ ጠቆሙ። እንደዚሁም ሁሉ «ለኢትዮጵያ ሕዝብም ያለን አክብሮት ተመሳሳይ ነው!» አሉና ዙሪያ ገባህን እሳት እንለኩሳለን ሲል ለቆየው ጉባዔ ማለስለሻ ቫዝሊን ቀቡት። እኛ የትኛውንም ጀብደንነት ጀማሪዎችና በማንም ላይ አሳቢዎችም አይደለንም አሉ። ነገር ግን አሉ ፕሬዚዳንት ሞርሲ፤ ነገር ግን መታወቅ ያለበት እያንዳንዷን የዐባይ ውሃ ጠብታ ለመከላከል እጅግ የጠነከረ እርምጃ የምንወስድ መሆናችን ነው። ለእያንዳንዷ ጠብታ ውሃ! source http://dejebirhan.blogspot.com/2013/06/blog-post_6.html

 6. Filmon says:

  በአፍራሽ አስተሳሰባቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዛሬም የግብጽን ጦር ገና ከሩቁ እንድንገብርለት ጉትጎታ ይዘዋል :: ፕሮፌሰሩ እያረጁ ሲሄዱ የሃገራቸውን ታሪክ ዘነጉት መሰለኝ:: ለነገሩ ዘመን ተሻጋሪ አኩሪ ታሪካችንን ተቀምጠው ሲያከሽፉት ለሚውሉ ሰው የሃገራቸውን ታሪክ ዋጋ ቢያሳጡትና በተንጋደደ እይታ ቢያዩት ምን ይገርማል? ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ይባል የለ::

  ሰውየው እኮ ሃገራችን በደም አላባ ስትታጠብ በርሃብ አለንጋ ስትገረፍና ህዝቦቿ በአለም አደባባይ ስንዋረድ የኬንያዊውን የመሃመድ አሚንን ያክል ለሃገራችን ያላበረከቱ ግለሰብ ናቸው:: ዜጎች ያለፍርድ ሲረሸኑ ሲዋረዱ ሃገራችን የጨለማ ዘመን አገዛዘን እያማከሩ ሲሰሩ የነበሩ ሰው ስለሃገር ክብርና ስለሃገር እድገት ብዙም ይገዳችዋል ብሎ መጠበቅ ከሰማይ ደመናን እንደመዝገን ይሆናል::ተማሪወቻቸው እና ከሳቸው በእጅጉ በትምህርት እና በእድሜ የሚያንሱ ወጣቶች ለሃገራቸው እና ለህዝባቸው ነጻነት ሲዋደቁ ክቡርነታቸው ግን ለንደን እና ዋሽንግተን እየተንሸራሸሩ በነበረበት ወቅት በርሃብ እና በጦርነት እየነደደ ስለነበረው ህዝባቸው አንዲትም ቃል እንደተነፈሱ ታሪክ የላቸውም ::

  ጀግኖቹ ወጣቶች እና የተገፉ ኢትዮጵያዊያን ደርግን ድል አድርገው ሃገሪቱን ሲቆጣጠሩ ህዝቡ እንዳይቀበላቸው እና የነበረው ስርአት እንዲቀጥል ሢተጉ እንደነበር የሚታወስ ነው:: እናም ፕሮፌሰሩ ለሃገራችው ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ከመስራት ይልቅ የመንገድ ላይ እሾህ በመሆን ሂወታቸውን ሙሉ ሲያወሩ ጊዜ ያለፈባቸው ታሪክ የሚሰራን ተቀምጠው በውሃ ቀጠነ ሲነዘንዙ የከረሙ፣ በተንኮል የተመረዘው አእምሯቸው ዛሬም የእድሜ ብዛት ያላስተማራቸው ግለሰብ ናቸው:: እስኪ ይሄንን ሁሉ ያስባለኝን የፕሮፌሰሩ ሃሳብ ባጭሩ ላስቀምጥ፥

  የግብጽ ጦር በአለም አስረኛ ነው የጦር ብዛቱ አንድ ሚሊየን ተኩል ያክላል:: በአየር ሃይሉም ቢሆን በአለም አስራ አራተኛ ነው:: የታንክ ብዛቱ በአለም አራተኛ ነው፣ ቅብጥርሴ እያሉ ነገራቸውን ይቀጥላሉ ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩም የቀድሞ ታሪክን እያስታከኩ ለጦርነት የሚገፋፉ የስርአቱ ደጋፊወች ጠግበው ነው ሊሉ ይዳዳቸዋል:: እኔ እስከማውቀው ድረስ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከእርሳቸው በበለጠ የጦርነትን ምንነት ጠንቅቆ የሚረዳ እና የጦርነትን አስከፊነት እንደክቡርነታቸው በቴሌቪዥን ሳይሆን በተግባር የሚረዳ ይመስለኛል:: እናም የሃገራችን ጥቅም ለማስከበር በሚደረገው ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ስራ ከጎን ከመቆም ይልቅ በተንኮላቸው የማይወዱትን አካል ጠልፎ ለመጣል እስከጠቀመ ድረስ የሃገርን ጥቅም ለመሸጥ ጉጉነታቸውን አይቸበታለሁ::

  በጣም የሚገርመው ሰውየው የሃገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በጥርጣሬ እንዲተያዩ እና የዲሞክራሲ እድገታችን ሳንካ ሆነው እንደቆዩ ልብ ያለው ልብ የሚለው ይመስለኛል:: እናም ግብጽን በተመለከተ የጸፉት የሃገራቸው ታሪክ ጠፍቶባቸዋል ወይም ሰውየው እርጂናው ጽንቶባቸዋል እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ጣልያን ሆነ ሃገራችንን ለመውረር የመጣ ወራሪ መቸም ቢሆን በወታደራዊ አቅም በልጠን ሳይሆን በአላማ ጽናት እና እውነተኛነት እንዲሁም በጀግንነት እንደመከትነው እንጂ በመሳሪያ እና በሰለጠነ ጦር ልቀን ስለተገኘን ያገኘነው ድል እንደሆነ ታሪክ አይነግረንም:: ለነገሩ እርሳቸው የህዳሴው ግድብ በዘመነ ኢህአዴግ እንዲሰራ እንደማይፈልጉ እርግጥ ነው:: ግን ሳይሞቱ ኢህአዴግ የጀመራቸውን ግዙፍ ፕሮጀችቶችን ተጠናቀው እንዲያዮ እመኛለሁ:: ቋቅ ይበላቸው እንጂ ግድቡ በወርቅ ከሚጻፉ የወጣቶቹ ድሎች ውስጥ ዋነኛው ነው:: እናም ይመኑኝ ክቡር ፕሮፌሰሩ እንደሚሰጉት ግብጾቹ አያሸንፉንም ከንግዲህም ደግሞ ወደኋላ አይመልሱንም ::

  በመጨረሻም የፕሮፌሰሩ ድርጊት በጣልያን ወረራ ጊዜ የነበሩ ባንዳ ምሁርን የጣልያንን ሃያልነት እና ስልጣኔ እንደምክንያት በመውሰድ የኢትዮጵያ ህዝብ የጣሊያንን ወረራ እንዲቀበል ሲወተውቱ የነበሩትን አፈወርቅ ገብረየሱስን አስታወሰኝ:: ስለዚህ ፕሮፌሰሩን የዘመኑ አፈወርቅ እንበላቸው??????????ቸር ይግጠመን>>

  • jhon says:

   • አፍራሽ ብለሃል የቱ ጋር አፍራሽ እንደሆነ ብትገልፅ ጥሩ ነበር ፡፡ ያለውን እውነታ ስለነገሩህ ነው እንዴ አትደንግጥ!!
   • አኩሪ ታሪክ ማለት እኮ ጠብ ፈልገን አይደለም ጦርነት ወይም ግጭት ውስጥ ስንገባ የነበረው፡፡
   • “ተማሪወቻቸው እና ከሳቸው በእጅጉ በትምህርት እና በእድሜ የሚያንሱ ወጣቶች ለሃገራቸው እና ለህዝባቸው ነጻነት ሲዋደቁ ክቡርነታቸው ግን ለንደን እና ዋሽንግተን እየተንሸራሸሩ በነበረበት ወቅት በርሃብ እና በጦርነት እየነደደ ስለነበረው ህዝባቸው አንዲትም ቃል እንደተነፈሱ ታሪክ የላቸውም ::” ብለሃል ስነ ፕሮፌሰር ምንም እንደማተውቅ በደንብ ያስታውቃል፡፡ ዘለፋና ዝንብሎ ጩኸት እንዲሁም ብስጭት ግን ታውቃለህ እሱንም በደንብ አትችልበትም፡፡
   • ፕሮፈሰር መስፍን ከአፈወርቅ ገብረየሱስን ማመሳሰል አዲሱ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ባንዳ ማለትስ? ለነገሩ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው፡፡
   • ባንዳ ማን እንደነበረ እና እንደሆነ እራሱ ያውቃል፡፡

 7. Filmon says:

  you are an evil man just like afework g/yesus banda.

 8. Selam says:

  I agree Professor, I am a bit surprised when a number of Ethiopians on various Egyptian and other news websites leave comments like ‘revise you history books about the battle of Gura, Gundet and Adwa’, ‘We were never colonized’, ‘bring it on’ and so on. Lets all tame the testosterone

  • Selam says:

   And Prof. I recall what you said during when we were beating more war drums during the Ethio-Eritrean war. You said ‘The Ethiopian people are tired of war, are tired of hunger…’

 9. Kolotemari says:

  Dear, professor
  I understand you. Love needs acceptance. Acceptance comes after knowledge.Defending mother Ethiopia is experiencing love.To stop enemy, we need to have knowledge on it.
  Thank you

 10. Bante says:

  Ena men yhun pro….ahunes egna ternachew..metuben enje alkesekesenachewn .mefthewen bdeb ykerbulen yalebleza gen mawerat becha new

 11. geezonline says:

  እንዴት ያለ ዓይን ነው ያለዎት ባክዎት? የንስር ዓይን!!!

 12. haq says:

  Yosief’s Circular Journey In Search Of Ethiopia,,, http://awate.com/yosiefs-circular-journey-in-search-of-ethiopia/ …But according to Yosief, there is only one way out of Eritrea’s predicament: call for “demobilization”! This is an attractive proposition. As Yosief is quick to remind us this reunites families. What more could we ask for? What he doesn’t tell us is that demobilization will also render them sitting ducks making them as “helpless” as the family they will reunite with. Shouldn’t we instead call for the guns to be pointed squarely at the slave master, the oppressor, and tyrant?

  Besides, who is going to demand demobilization? The Diaspora? No, because according to him, they are in the “wrong stage”. Those in Eritrea? Impossible! Didn’t he tell us that there are only helpless women, illiterate peasants, children, and the old? How about the soldiers? Again, no. They are too atomized and too indoctrinated according to him to stage any collective action or demand. Thus, in Yosief’s “disjointed” Eritrea, no one is fit to demand the “demobilization” he is proposing. Perhaps he wants Ethiopia to make the demand? His own words say it all: “the demobilization demand cannot be entertained without the intention of making peace with Ethiopia” (note the emphasis – his not mine). Is “demobilization” a path to ensure Ethiopia a final victory over a disarmed Eritrea and to reverse the achievements of a dearly won war of independence that he openly derides – to somehow wind back Eritrea’s history to square one? if the opposition (both those in and those out of Eritrea) will never be able to bring change, who is to rescue Eritrea from the jaws of Shaebia? Ethiopia, silly! In other words, Yosief wants Eritrea – which according to his thesis is a rebellious teenager that run away from home against her best interests and suffered for decades as a result – to come back home fully repentant to reunite with “mama” Ethiopia.

 13. haq says:

  – ይህ ማለት ግን እነርሱ ይፈልጉናል ማለት አይደለም እንዲያውም እጅግ ይጠሉናል- ይህንን እስኪ ተመልከቱ–- የሚገርመው ዌብሲቱ የshabeia ተቃዋሚዎች ነው ተቃዋሚዎቹም አዲስ አበባ ናቼው-http://awate.com/the-political-chess-game-to-tame-the-woyanes/ ….Well, well, well… Why I’m I not surprised? Deki-Ere – it’s happening again. History is in the making. It is a brand new day in Eritrea; and it is a dawn of a new era in Ethiopian politics. In Addis deep from its inner core, the ground is shifting along its geological fault lines. And as a result of this massive underground tremor, a brand new landscape is emerging in the Ethiopian political terrain. While the wind-vane on top of the newly formed landscape is decisively pointing south, Mekele is mute; and for a good reason. The Woyane revolution as a Tigrean ethnic revolution is buried with Meles Zenawi. Yes – the dream of Greater Tigray, the dream of Tigrean dynasty, the dream of independent Tigray nation state…. are all gone. Meles the revolutionary, Meles the face of Woyane, Meles the pride of Tigray is buried in Addis wrapped-in Ethiopian flag. Yep, you heard me right, not in Tigrean flag but wrapped-in Ethiopian flag; not in Dedebit, not in Adwa, not in Mekele, not even in Tigray but in Shoa. The Tigrean safety net: Article Thirty Nine is null and void. The Tigreans have crossed the Rubicon. Now, it is safe to say, the Tigreans are Ethiopians!The people of Tigray are shocked by Meles’s untimely death. The people of Tigray are confused. The people of Tigray are kept in the dark. The people of Tigray are duped. The people of Tigray are so overwhelmed by the whole thing they didn’t even know how to react.

  Heralding dawn of a new era – “There is no change in policy….” said Hailemariam Desalegn the new Ethiopian prime minster, referring to his country’s ‘no war no peace’ policy towards Eritrea. But he was roaring from way, way…. way distant South. Eritreans could barely hear his Tuta, Zeraf, Geday roar from way up North. Of course Mr. Hailemariam is not the real man. How could he be the real man if he doesn’t have the organizational infrastructure, a strong power base and a dominant personality to be one? He is just a placeholder. But for sure, he was roaring on behalf of the new powerful. Yes, on behalf of the soon to be advertised and marketed as “democratic” and “visionary leader/s” for the next ten to twenty years by their handlers. If you read between the lines, Mr. Hailemariam was not roaring to warn the PFDJ regime when he said “there won’t be any change in policy towards Eritrea”. Caught between a rock and hard place, he was just trying his best to juggle three giant iron-balls without having a bad throw that would end-up in mid-air-collision and eventually the unfortunate dropping of a ball on his foot. He is trying delicately, to lure the Woyane bosses to accept reality and live life as a second best, to assure the Tigrean people from panicking; and all these and more without stepping on the toes of the new-powerful. Quite a task, isn’t it?

  Through Hailemariam Desalegn and through every media outlet in Ethiopia, the deceptive new powerful and the cunning Woyane hardliners are busy spinning Ethiopian politics like never before. They are busy selling the Woyane revolution as an Ethiopian revolution. They are selling Meles the Woyanay, as an Ethiopian hero who fought to liberate all Ethiopians from tyranny, poverty and backwardness. They are professing their love, respect, and admiration for Meles the “great visionary leader”. They are promising their fellow Ethiopians that they will follow his programs, his vision and his policies. They are showing sound-bites from Meles’s speech 24/7 to assure his base. They are selling Meles as an Ethiopian hero ! For starters, the wind-direction has changed. The dark clouds that were looming on the horizon are moving farther south leaving the Eritrean-blue-skies clear-off the “no war no peace” Meles policy. It is time for us Eritreans to realize the change in moment, and shift gears to lower the political temperature at the ground level. Today, there is no Woyane-dream of Greater Tigray. Today there are no vindictive-Woyane leaders at the helm who are hell-bent to, humiliate Eritrea and achieve ‘regime change’ to have it their way. Today there are only Tigrean-Ethiopians !

 14. haq says:

  በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራ- አታስፈልገንም ተብሎ እስከ ባህር በራችን ማስረከባችን እውነት ነው– ይህ ማለት ግን እነርሱ ይፈልጉናል ማለት አይደለም እንዲያውም እጅግ ይጠሉናል- ይህንን እስኪ ተመልከቱ–http://awate.com/seyoum-haregots-new-book-a-critique/ comment by auther of article….For Eritreans, there is a cautionary tale of how Ethiopia had dealt with its border problems with Somalia and the Sudan. In short, “adhering to principles” and “doing the right thing” meant nothing to Ethiopia; the only game it was interested in was winning, through either chicanery that masqueraded as diplomacy or brute force.If you read my article, that is exactly what I said about the need for caution with Tigrayans and Ethiopians. Their commimtment to doing the right thing is historicallly very dismal. I gave the examples of Somalia and the Sudan for that purpose. The Ethiopianization of TPLF has not been good to us; they are following the same policies of the Amhara dominated previous regimes and we have every reason to be extra cautious. But this should never make us deny our blood ties with them and if we could wise up, it could be a bridge to fostering a great future!…I’m intrigued why Tigrinya speaking Eritreans in Ehtiopia didnt identify themselves with their Tigrinya-speaking Ethiopians–the Tigaru. Is this the case of “Asha sebeyti’s wedHamuta zeyweda ymesla? The restoration of Tigryan pride is one of the few changes that makes me happy. Thanks to Alemseged Abbay, I now know the politics of “Y” where Tigriyans were forbidden to use their proper name. My only concern is that the EPRDF ‘Ethiopianess” is undermining TPLF’s Tigrayness. EPRDF’s policies, unlike the TPLF’s is a continuation of the Amhara dominated Ethiopian policies…. I’m even puzzled why many Eritreans (let me qualify it by saying of the ones I know and on the discussions I’ve had with other Eritreans)prefer Amharas than Tigaru. You see I don’t see any difference between Tigrinya speaking Eritreans and Tigaru–we’re the same. I honestly don’t care about the prevailing politics that is unnecessarily creating divisions among us, but I cannt deny the fact that a Tigrinya speaking person from Seraye, Akeleguzay, Hamasein, Adwa, Agame, Tembien…are the same people, ethnically, culturally, religiously and historically. I’ve not had the honor of visiting Tigray but I can imagine that is one place outside Eritrea where I will completely feel at home. I’ve never met a Tigrayan I didn’t like or one I didn’t feel a sense of kinship with it. As I said before, when a Tigrinya speaking Eritrean sees him/herself in the mirror, s/he sees a Tigrayan and the opposite is true. The sooner we realize, appreciate and honor this truth, the better chance we will have for a better future…My reading of history tells me we need to reflect on our past and prepare a better future for our kids. Towards that goal, I’m ready to do my part.

Comments are closed.