ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል

መስፍን ወልደ ማርያም

ሰኔ 2005

ከጥቂት ቀናት በፊት አንዳንድ ሰዎች በዓባይ ጉዳይ ቀረርቶና ሽለላ ማሰማት ሲጀምሩ ከባድ የሆነ የመረጃ እጥረት መኖሩን ስለተገነዘብሁ ስለግብጽ የኃይል ሚዛን ደረቅ መረጃ የጦርነትን መጥፎ መልክ ከሚገልጽ አስተያየት ጋር አቀረብሁ፤ የወያኔ ሎሌዎች ወዲያው በእኔ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፈቱ፤  ድንቁርናው ከዚህ ይጀምራል፤ ማሪዮ ፊልሞና ብሩኖ ‹‹በአፍራሽ አስተሳሰባቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዛሬም የግብጽን ጦር ገና ከሩቁ እንድንገብርለት ጉትጎታ ይዘዋል፡፡›› በማለት ውርጅብኙን ይጀምራል፤ አንድም ቦታ እኔ ያቀረብሁትን መረጃም ሆነ አስተያየት አንሥቶ ጉድለትን አላሳየም፤ ዓላማው መረጃው ወይም አስተያየቱ አይደለም፤ ለረጅም ጽሑፉ ዓላማው እኔ ነኝ፤ የአሉላ ሰሎሞን ጆቫኒ የግጥም ዓይነት መልክ ከመያዙ በቀር ያው ነው፡፡

ለእነዚህ ሰዎች መልስ የሚያስፈልጋቸው በእኔ ላይ የሰነዘሩትን ለማረም አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች መልስ አይገባቸውም ይሉኛል፤ እውነት ነው፤ እኔ በሥራዬ እቆማለሁ፤ ወይም በሥራዬ እወድቃለሁ፤ ነገር ግን ንጹሐን ወጣቶችን አዋቂዎች መስለው እንዳይበክሉ መከላከል ግዴታ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ድንቁርና እንደተላላፊ በሽታ ነው፤ ይጋባል፡፡

ድንቁርና መጥፎነቱና አደገኛነቱ ከኋላውም ሆነ ከፊቱ የሚያይበት ዘዴ አለመኖሩ ነው፤ ለዛሬ፣ ለሆድ ብቻ መኖርን ዕለታዊ ዓላማው የሚያደርግ ነው፤ አንጎሉ በድንቁርና የተሞላ ለምንም ሌላ ነገር ቦታ የለውም፤ ይህ ድፍን ወይም ፍጹም ድንቁርና ነው፤ ተስፋ-ቢስ ነው፤ አንጎሉ ውስጥ ድንቁርና ያልደረሰበት ትንሽ ቦታም ቢሆን ከአለ የእውቀትን ዘር ለመዝራትና ብርሃን ለመፈንጠቅ ዕድል ይኖራል፤ አለዚያ ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡

ፊልሞን በሚል ስም ራሱን የሚጠራው ከሽፍንፍን መውጣት ያልቻለው ፈሪ ፊደልን ብቻ የተማረ መሀይም ነው፤ ይህንን አንብበህ መልስ ስጥበት ብሎ ያዘዘው ሰው የእኔን ጽሑፍ ካልሰጠው በቀር የእኔ ስም ባለበት ሰሌዳ ደርሶ ከሆነ ሰውዬው የማየት ችግርም አለበት ማለት ነው፤ በሰሌዳው  መጀመሪያ ገጽ ላይ የእኔ መጽሐፎች ሽፋኖች ይታያሉ የሎሌነቱን ተግባር ለመፈጸም የቀባጠረውን በዝምታ ማለፍ እሱን ራሱንም ሆነ በተለይም የአነበቡትን ሰዎች መጉዳት ሰለመሰለኝ ከእውነቱ ጋር እንዲጋፈጥ ማስገደድ ይገባኛል፤ ባንዳውን ምሁር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስን ማወቁን ሳደንቅለት ኃይለ ሥላሴ ጉግሳንና ጭፍሮቹን እንዳልረሳቸው ተስፋ አለኝ፡፡

 እኔ እስከማውቀው ድረስ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከእርሳቸው በበለጠ የጦርነትን ምንነት ጠንቅቆ የሚረዳ እና የጦርነትን አስከፊነት እንደክቡርነታቸው በቴሌቪዥን ሳይሆን በተግባር የሚረዳ ይመስለኛል:: እናም የሃገራችን ጥቅም ለማስከበር በሚደረገው ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ስራ ከጎን ከመቆም ይልቅ በተንኮላቸው የማይወዱትን አካል ጠልፎ ለመጣል እስከጠቀመ ድረስ የሃገርን ጥቅም ለመሸጥ ጉጉነታቸውን አይቸበታለሁ፡፡

 

ይህንን ለመጻፍ የሚያስችል ድንቁርና ፍጹም ነው፤ ይህንን ፍጹምነት ሲያጠናክረው፤ —

ሰውየው እኮ ሃገራችን በደም አንባ ስትታጠብ በርሃብ አለንጋ ስትገረፍና ህዝቦቿ በአለም አደባባይ ስንዋረድ የኬንያዊውን የመሃመድ አሚንን ያክል ለሃገራችን ያላበረከቱ ግለሰብ ናቸው:: ዜጎች ያለፍርድ ሲረሸኑ ሲዋረዱ ሃገራችን የጨለማ ዘመን አገዛዘን እያማከሩ ሲሰሩ የነበሩ ሰው ስለሃገር ክብርና ስለሃገር እድገት ብዙም ይገዳችዋል ብሎ መጠበቅ ከሰማይ ደመናን እንደመዝገን ይሆናል::ተማሪወቻቸው እና ከሳቸው በእጅጉ በትምህርት እና በእድሜ የሚያንሱ ወጣቶች ለሃገራቸው እና ለህዝባቸው ነጻነት ሲዋደቁ ክቡርነታቸው ግን ለንደን እና ዋሽንግተን እየተንሸራሸሩ በነበረበት ወቅት በርሃብ እና በጦርነት እየነደደ ስለነበረው ህዝባቸው አንዲትም ቃል እንደተነፈሱ ታሪክ የላቸውም ::

የተማሪ ቤት ግቢን የረገጠ ይህንን አይጽፍም፤ አንደአለቆቹ መሸጦ አስተማሪ ቤቱ ድረስ እየሄደ ፊደል ያስቆጠረው ሳይሆን አይቀርም፤ ፊደሉን ማወቁን እንደመጨረሻ ትምህርት ወስዶታል፤ በአንድ በኩል የሚያሳዝን ሰው ነው፤ በሌላ በኩል ግን ድፍረቱ ድንቁርናን የሚያበረታና ለጥቃት የሚዳርግ ነው፤ ለኮሎኔል መንግሥቱ ጂቡቲ ጦርነት ብትከፍት ኢትዮጵያ እንደማታሸንፍ ነግሬው ነበር፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የክምችት ክፍል ሄዶ በጓደኞቹ እርዳታ ትንሽ ቢቆፍር በደርግ ዘመን ‹‹ሕዝብና መንግሥት ሆድና ጀርባ ሆነዋል፤›› በማለት የተናገርሁትን ያገኘውና ዓይኑን ይከፍትለት ነበር፤ ምስክሮቹ ሁሉ በሕይወት ባሉበት ጊዜ እንዲህ ያለ ውንጀላ አያዋጣም፤ ወይም እኔን በባንዳነት ከራሱ ጋር ሊያዛምደኝ ፈልጎ ከሆነ ያማ መንገድ አያስሄድም፤ እግዚአብሔር ይመስገንና በዚህም በዚያም ከባንዳ ጋር ንክኪ የለኝም፡፡

እኔ ስለጦርነት የጻፍሁት ለሚያውቁና ማሰብ ለሚችሉ ሰዎች ነበር፤ የሚያውቁ ሰዎች የምላቸው የአሥራ ዘጠነኛውን የመጀመሪያ አጋማሽና የሃያ አንደኛውን ምዕተ-ዓመታት ሁኔታዎች ተገንዝቦ ማመዛዘን የሚችለውን፣ በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ በአድዋ ላይ የተቀዳጀችውን ድል በኩራት እያስታወሰ በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ደግሞ በማይጨው ላይ በኢጣልያ ጦር የተሸነፈችበትን ውርደት የሚያውቅና የሚሰማው፣ በዚያው ላይ ኢጣልያ በአድዋ መሸነፍ የተማረች ስትሆን ኢትዮጵያ በአድዋ ድልም ሆነ በማይጨው መሸነፍ ሳትማር መቆየቷን የሚያውቅና የሚቆረቆር፣ ካላወቀም ለማወቅ የሚጓጓ ሰው ነው፤ ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ጦር ከወያኔ ጀሌ ጋር፣ ከሻቢያ ጀሌ ጋር፣ ከሶማልያ ጋር፣ በቅርቡም ከኤርትራ ጋር፣ በኋላም ከሶማልያ አክራሪዎች ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ሁሉ የሚያኮራ ነገር አልታየም፤ ይህንን ሁሉ እውነት አውቆና አመዛዝኖ ለማየት የማሰብ ችሎታን ይጠይቃል፤  ማሪዮ ፊልሞና ለዚህ አልታደለም፤ በቅዠት ዓለም ውስጥ ሆኖ ራሱን አሉላ የሚለው ብሩኖም እንዲሁ ያልታደለ ሎሌ ነው፤ ለሁለቱም ከጉራዕና ከጉንደት በኋላ ታሪክ የለም፤ እዚያ ላይ ቆሟል፤ የደበዘዙ ዓይኖችና የደነዘዙ አንጎሎች በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የሆነውን ይዘው 2005ን ለመደልደል የሚፈልጉ እንደፊልሞንና እንደአሉላ ሶሎሞን ያሉ ምስኪኖች እንዳይታዘንላቸው ትዕቢታቸው አያስቀርብም፤ እንዳይተዋቸው መርዛቸው ብዙ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል፤ ያለው አማራጭ ድንቁርናቸውን ማጋለጥ ብቻ ነው፡፡

የታሪክ ዋናው ዓላማ ጥቅም ዓይኖችን በአለፈው ነገር ላይ ተክሎ ወደኋላ ለማየት ሳይሆን ከፊታችን የተደቀነውን የዛሬውን ችግር ለመወጣት ከአለፈው ስሕተት መማር ነው፤ አንድ ጥያቄ፡– የኢትዮጵያ ድንበር ከዓባይ ጀምሮ ወደሰሜን እየሰለለ የሄደው ለምንድን ነው? እነፊልሞንና እነአሉላ ሶሎሞን ይህንን የማስተዋል ብቃት የላቸውም፤ ቢያስተውሉትም ስለማያስቡ አያሳስባቸውም፤ ማሰብ ቢችሉ የሚደነፉበትንና ግጥም የሚጽፉበትን ወደእፍረት ይለውጥባቸው ነበር፤ በቅርቡም በባድመ ጦርነት ፉከራውና ሽለላው ወደእፍረት ሲለወጥ አይተናል፤ ድንቁርና የሚደነድነው እውነትን፣ ከእውነት ጋርም እውቀትን እያፈነ ነው፡፡

በ1864 ዓ.ም. አካባቢ በጦርና በጋሻ አሸንፈናል፤ ዛሬም በ2005 ዓ.ም. በዚያው ዘዴ እናሸንፋለን ማለት የድንቁርና ዘውድ ነው፤ እኛ እንዳልተለወጥን ሌሎችም አልተለወጡምና በ1988 ዓ.ም. በአድዋ ኢጣልያን ድባቅ መተናል፤ እያልን ስንፎክር በ1928 ተመልሶ ሲመጣ በማይጨው ድባቅ መታን፤ ያን ጊዜ የሆነውን ማን ነው ከታሪክ የተማረው? ዛሬ ኢጣልያ ቢመጣ ፊልሞንና አሉላ ከነጓደኞቻቸው መንገድ መሪዎች መሆናቸው እጅግም አያጠራጥርም፤ ምክንያቱም እኔ የግብጽን ኃይል ለማሳወቅ የፈለግሁት እንዳንዘናጋ ሲሆን የእነማሪ ፊልሞንና አሉላ ጆቫኒ ፍላጎት ደግሞ ለማዘናጋት መሆኑ ነው፤ ዋናው ጥያቄ ግን ለምን እንድንዘናጋ ይፈልጋሉ? የኢትዮጵያ መዘናጋትና ለአደጋ መጋለጥ ምን ይጠቅማቸዋል? የሚለው ነው፤ መልሱ ውስጥ አልገባም፤ ፡፡

ዘመኑ እውቀት የረከሰበት ነው፤ ዛሬ አንድ ሰው የፈለገውን እውቀት ለማግኘት ከስንፍናና ከእኩይ ትዕቢት በቀር የሚያግደው የለም፤ በድንቁርና ከመኩራራት ፈርጠም ብሎ በእውቀት መስተካከልና ለወደፊቱ ማሰብ ቀና ይሆናል፤ ድንቁርናን የሚድን ሕመም እናድርገው፡፡

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

46 Responses to ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል

 1. realistic says:

  lehod ader beshitegnoch medhanit professor mesfin

 2. Siltan says:

  Few Points on the “Banda”
  Some of you, including the professor seem to be obsessed with the word “banda”, which you are applying to anyone with views different from yours; in worst cases you are even using it to label a certain political or ethnic group. Bandas are not strangers in Ethiopian history. They exist today as they had in the past; and their motives were also different. They sprung up from every region, every ethnic group and every walk of life; but one has to first clearly understand the circumstances in which they became bandas. Some of the noted bandas during the time of Italian Occupation such as: Negadras Afework Gebreyesus, Dejazmach HaileSilassie Gugsa, Ras Hailu Teklehaimanot, Dejazmach Ayalew Biru, Bilata Deressa Amentie, Ato Kebede Michael, etc…,do not belong to single ethnic group or region and they collaborated with Italians for different reasons. Professor Mesfin also had early foundations of life as “Ragazzi il Duce[Mussolini]”, which makes him to be qualified as a banda of a different type. This means we have to see our application of the term in light of specific issues before we judge them.
  Regarding the type of bandas with proven propensity to dismantle Ethiopia by negotiating with invaders, of course, Emperor Menelik comes at the top. Be it in cowardice or in selling out sovereign territories, Menelik has no parallels in Ethiopian history (and Ras Mekonen comes second to him). As a note for his cowardice, for example, Emperor Tewodros nicknamed him “Zereto” and many of his close aides, including his wife Taytu and Ras Gobena, were scolding him again and again (calling him “Ye-Bafena muhacha”)for displaying timidity and fear in times of war.
  The worst of Menelik’s crimes is, however, giving Ethiopian lands to foreign powers. Article III of Wuchale Treaty bears witness how Menelik gave Eritrea to the Italians. To this effect Ras Mekonnen too signed the Naples Convention permitting Italians to get hold of lands in northern Ethiopia as vast as they can before the signing of Wuchale treaty by King Umberto of Italy. Again Menelik not only gave Obok( what we now call Djibouti) to the French, but also sold to the Italians an area covering about 50,000 sq.kms (of Ethiopian lands adjoining Italian Somaliland) just for 3 million Lira. These shameless acts of Menelik, (like Hailesilassie’s and Mengistu’s) are conveniently omitted by Shoan Historians and pseudo-scholars like Mesfin Woldemariam. But history is unforgiving and un-forgetting.
  I hope, the blind funs of Professor Mesfin would give us clarifications as to where we should place not only Menelik but also that “Ragazzo di Mussolini”, whom they worship, and they could check historical realities before uttering the word “Banda” or “yebanda lij” !
  Written By Woldebirhan Sihul

  • zee says:

   “Banda” may feet to you. No wonder you scared of this word.

   • Siltan says:

    Ato Zee, challenge these arguments instead of retreating to your usual jargon. In your brief comment you proved to me how you still love to bury your head in the sand, like the proverbial ostrich. Anyone with healthy mind can not have difficulty in understanding how Woldebirhan is striving to clarify the vulgar and categorical application of the word “banda” ( such as in the case of the professor and sycophants like yourself). But you just vented this term to ward off ideas (facts, explanations and arguments) that scare you most. I know, you love stick into your outdated worldview, but i advise you to see things in a new light_though ignorance could be your choice!

 3. Shegawe says:

  After reading and trying to analyze what has been written and said on the good professor, I think I finally found what the problem is for all: him , them and me! My problem is silence. pure and simple. As to him and them, the professor having the interest of his country at heart writes and deliberates. Others, them, claiming that they have their interest in that same country says neigh all the time! I presume having interest is not a problem ; be it on the country or at anything else. But if they think that the professor has acted against his country say for instance by assisting the murder of the sixty imperial officials and bla blas of other charges, why somebody does bring the evidence and take him to a court. Why is all the talk for about 21 years and who is counting anyway? The court is theirs! The prosecutor is theirs! But it seems that it is not easy to fabricate evidence even for them!!

  • ARAYA says:

   eyewerede yale dro-fessor. is it how 2 teach us? why ignorance of GURA and GUNDET? BEKA AYNOT DEKEME AYDEL. ke’DEBRE BIRHAN ASHAGRO MAYET AKATOT. why always stick on ‘bandas’? does z betrayal of H/Sellasie Gugsa overshadow z African-wide bravity of Alula? can repeated treason of Afewerk G/Eyesus diminish z honour of Belay Zeleke? i believe, no justification for betrayal of mother country. unfortunately historically in all areas we have bandas. so what? should i be ashamed 4 z past tme presence of banda in my birth place? who cares? every person punished 4 his own misdeed. PROF,do u believe zat z narrowness of Ethiopia’s map towards z north is due to z coward nature of northern Ethiopia compared to other regions?(red sea is laughing!!hahahahahaha………).yigbawot!!sometimes opposing u isn’t a matter of being slave of woyane or not being Amhara. don’t resort to this backward hasty generalization!!

   • Shegawe says:

    As I said I am not going to be silent anymore. The professor said and I agreed too that We have bandas and heros as well. He did not say why the boarders of northern Ethiopia has got narrower and narrower,. You indicated that if it means you having a lot of banadas in your surroundings. May be you are right ,may be you are wrong. But in one of his books the professor suggested that it is for the reason of colonial powers. For your information in my birthplace no italian has touched my land. Noting is the reason except the heroic deeds of my forefathers. But that does not exonerate me for the shame I suffered that my country was under occupation for five years.

   • Teddy says:

    Araya, do not only list out the names of your ‘banda’, include there deeds as well. Then we can learn how they dismantled our mama Ethiopia by negotiating with the invaders. ‘’The mistakes of the fool are known to the world, but not to himself. A smart man makes a mistake, learns from it, and never makes that mistake again. But a wise man finds a smart man and learns from him how to avoid the mistake altogether.’’ So check yourself in which line you are!

 4. dereje says:

  Posts by Daniel Berhane:
  ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ባለፈው እሮብ ከአባይ ጉዳይ በተያያዘ የጦርነት ቅስቀሳን ለመገሰጽና የግብጽን የጦር ሀያልነት ‹ለማሳወቅ› አንድ ጽሑፍ አስነብበውናል፡፡

  ጽሑፉ በጥድፊያ እና/ወይም እንደተለመደው የኢሕአዴግን ባለስልጣኖች ለማብሸቅ ተብሎ የቀረበ ስለመሰለኝ አላተኮርኩበትም ነበር፡፡mesfin woldemariam

  ነገር ግን እሳቸው የጽሑፋቸውን ግልብነት (shallowness) አስተውለው – ጠለቅ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል ይሞክራሉ ብዬ ስጠብቅ፣ ትችት የሰነዘሩባቸውን ሰዎች በመሀይምነት መፈረጅ ነው የመረጡት፡፡

  ሰለሆነም እንደው ምናልባት እሳቸውም ሆነ ብለው የሚያምኑ የሚመስሉት ደጋፊዎቻቸው ልብ አላሉት እንደሆን ለማስገንዘብ፤ ስለፕ/ር መስፍን ጽሑፍ አንድ ሁለት ልበል፡፡

  የ ጽሁፉ ዋነኛ ጭብጥ በሚከተለው ጥቅስ ይወከላል፡፡

  ‹‹ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤……ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ››

  የትኛው ‹የጠገበ› ባለስልጣን ነው ለጦርነት የቀሰቀስው?

  የመንግስት ባለስልጣኖች አንድ ሁለት ጊዜ – ከ2 ዓመታት በፊት – ‹‹ግብጽ ብትወረንስ›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ታሪክ ጠቅሰው እንደማይፈሩ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ፡፡ (ግን ሌላ ምን መልስ ሊሰጡስ ይቻላቸዋል?) ከዚያ ባለፈ ግን ግብጽን አስመልክቶ አዎንታዊ እንጂ አሉታዊ ዘገባ እና ቅስቀሳ በመንግስት ሚዲያ ሰምቼ አላውቅም፡፡

  እንዲያውም ከካይሮ ግድም አሉታዊ ወሬ በመጣ ቁጥር የመንግስት ባለስልጣኖች ጦርነትና ግጭት የመከሰት ዕድሉን ስለሚያጣጥሉ፣ አንዳንድ ታዛቢዎች ‹‹እነዚህ ሰዎች አስጠንቁለዋል እንዴ›› ያሉበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ – ከአንድ ወር በፊት የጠ/ሚኒስተሩን ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳን ሳናግረው ‹‹ግድቡን እንደማናቆም ሲያውቁ ራሳቸውን ከእውነታው ያስታርቃሉ›› ነበር ያለኝ፡፡

  እርግጥ መንግስት በይፋ የሚያሳየው መተማመን ስልታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ግብጾችንም ‹‹ማነው ከግድቡ ጀርባ ያለው?›› የሚያሰኛቸውም እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡

  ሌላው የጽሑፉ አንኳር ሀሳብ እንዲህ ይነበባል፡-

  ‹‹አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ — የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤››

  የመረጃ ምንጩን ባይጠቅሱም ከመጠነኛ አሰሳ በኋላ እንደተገነዘብኩት መረጃውን ያገኙት ከGlobalFirePower.com ነው፡፡ የዌብሳይቱን የደረጃ አሰጣጥ ስልት ከተረዳሁ በኋላ ግን መስፍን ጽሑፋቸውን በችኮላ እንደጻፉት ደመደምኩ፡፡

  ከGlobalFirePower.com ደረጃዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት ላቅርብ፡-

  * የእያንዳንዱን ሀገር ጠቅላላ የጦር አይሮፕላን (ጀት፣ ሔሊኮፕተር፣ ወዘተ) ብዛት በመቁጠር፡- በአየር ሀይል ለኢራን 5ኛ፣ ለሳውዲ አረቢያ 11ኛ፣ ለግብጽ 14ኛ፤ ለእስራኤል 20ኛ ደረጃ ይሰጣል፡፡

  * በባሕር ኃይል (ሁሉንም የባህር ላይ የጦር ተሸከርካሪዎች በመቁጠር) በሰጠው ደረጃ ግብጽ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ከቱርክ ከፈረንሳይ ከጣልያን ከሕንድና ከእንግሊዝ ትበልጣለች፡፡

  * በታንክ ብዛትም የግብጽ ደረጃ ከህንድ ከሩሲያና ከፈረንሳይ በላይ ነው፡፡

  * የግብጽ ወታደር ብዛትም (ግማሽ ሚሊዮን ቋሚና 1 ሚሊዮን ተጠባባቂ ወታደር በመያዝ) ከፈረንሳይ ከእንግሊዝና ከእስራኤል ይበልጣል፡፡

  ይህን የደረጃ አሰጣጥ መሠረት አድርጎ የወታደራዊ ሀያልነትን መመዘን አሳሳች መሆኑ ለማንም ግልጽ ስለሆነ ብዙ አልልም፡፡

  ያም ሆነ ይህ ግን የኢትዮጲያ ጦር ሀይል የወታደር ቁጥር እና የበጀት መጠን ውስን እንዲሆን የተደረገበት ሳይንሳዊ መነሻ ሲኖረው፤ ግብጽ ደግሞ የጦር ሀይል ብዛትና ወጪ ማብዛት የፈለገችበት የፖለቲካ ምክንያት ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ከቆየው ከፊል-ወታደራዊ ስርአቷ ባህርይ ጋር ይያያዛል፡፡

  ይልቁንስ ፕሮፌሰሩ ሊያነሱ ይገባ የነበረው ጥያቄዎች፡-

  * በዚህ ዘመን የጦርነት መነሳት ሆነ ውጤት በጥይት ብዛት ነው እንዴ የሚመሠረተው? (የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ፣ የinternational public opinion ወዘተ ወሳኝ ሚናስ)

  * እኛ እና ግብጽ የጋራ ድንበር ስለሌለን፤ ግብጽ ሺህ ኪሎሜትሮች ተጉዞ ለሚደረግ ጦርነት በቂ ክህሎት፣ ልምድ፣ ድርጅት እና ሎጂስቲክ አላት ወይ?

  * ሱዳን ወይም ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠር የግብጽን ሠራዊት ለማስፈርና ለማሳለፍ ይፈቅዳሉ ወይ?

  አንዳንድ ሰዎች፣- ውስን የዓየር ወይም የኮማንዶ ጥቃት(surgical attack) ሀሳብ በማንሳት የመስፍንን ጽሑፍ ለማሻሻል ይሞክራሉ፡፡ እዚህ ላይም የቴክኖሎጂ ጥያቄ አለ፡፡ ከካይሮ ተነስቶ ኢትዮጲያ ደርሶ የሚመለስ አይሮፕላን ግብጽ አላት? (ስለሌላትም) የሱዳንን ዓየር ክልል ጥሶ መብረር ብቻ ሳይሆን ማረፊያም ማግኘት ትሻለች፡፡ እናስ ሱዳን ትፈቅዳለች?

  አንድ ነገር ልብ በሉ፡- ግድቡ ሲያልቅ ለማፍረስ ጥቂት ከባድ ቦንቦች ወይም ፈንጂዎች ሊበቁ ይችላሉ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ማጥቃት የሚያስፈልገው እንዳለ የፕሮጀክት ሳይቱን ይሆናል፡፡ (ገና በጅምር ላይ ያለን ቤት ማጥቃት እና ተሠርቶ ያለቀን ቤት ማጥቃት አድርጋችሁ እዩት)

  እነዚህንና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች ሳይመልሱ ታንክ መቁጠር ግልብ ትንተና ይሆናል፡፡

  ለማንኛውም ከሀይማኖት ወይም ፈሪሀ-እግዚያብሔር በመነሳት በድፍኑ ‹ጥጋብ ውርደት ያስከትላል› ብሎ መናገር ቢቻልም፤ የፕ/ር መስፍን ጽሑፍ ግን የመንግስት ሀላፊዎች ‹ጠግበው› ለጦርነት መቀስቀሳቸውን ሆነ ‹ጥጋባቸው› ‹ውርደት› እንደሚያስከትል በበቂ አላስረዳም፡፡

  እርግጥ የግብጹ Al-Jamaa al Islamiya መሪ ኢትዮጲያ በአባይ ላይ የምትሠራው ሥራ የጦርነት አዋጅ ነው በማለት አፀፋውን ለመመለስ ዛቻ ብጤ አሰምቷል፡፡

  ፕ/ር መስፍን የ‹ጠገቡ መሪዎች ለአጉል ጀብደኛነት ዝና› እየነዱን እንዳሉ አድርገው የቆጠሩት የሕዳሴ ግድብ ሥራን ይሆን እንዴ?

  **************

  Related:
  * Ethiopia-Egypt | A War on Nile Improbable, for now
  * Military expenditure at a historic low | Ethiopia
  * Africa: Top 25 Military Spending Countries

 5. Tesfakiros says:

  ፕሮፌሰር ይቅርታ የኔታ መስፍን ከውጭ ወራሪ ጋር ያደረግነው ጦርነት ሲጠቅሱ ለምንድነው ዓደዋና ማይጨው ብቻ መጥቀስ የፈለጉት? ጉዱዩ ከግብፅ ጋር የተያያዘ መሆኑ እየታወቀ ከግብፅ ጋር ኢትዮጵያ ያደረገቻቸው ጦርነቶች ለምን ማውሳት አልፈለጉም? በጦርነቱ ክብደት/በተሰለፈው የሰው ሃይል ብዛት፤ ከከፈልነው መስዋእትነትና ከተቀዳጀነው ድል አንፃር ከዓድዋ የሚበልጥ ሆኖ ሳለ(እርግጥ ከimpact አንፃር ዓድዋ ሊበልጥ ይችላል) ለምን ለመዝለል ፈለጉ፡፡ ከመንደርተኝነት፤ከተዛባና ከተወላገደ አስተሳሰብና ከደብተራ ሴራ መቼ ነው የሚላቀቁት፡፡

  የሃይለስላሴን ስም መጥቅስ ለምን አስፈለገ? ሃይለስላሴ ጉግሳ አፄ ሃይለስላሴ ላይ የነበረው ተቃውሞ/ተቃርኖ ነው ከጣሊያን ጋር እንዲወግን ያደረገው ወይስ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን የመንፈስ አባት አፈ ቄሳር አፈወርቅ በነፃ ህሊና አገሩን በባእድ ስር እንድትተዳደር የሰበከ? የሃይለስላሴ ተግባር በዘመናችን ተቃዋሚዎች ከጎረቤትና አገሮችና ከግብፅ ጋር አብረው በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመዋጋት የሚያደርጉት ጥረት ከሃይለስላሴ ጉግሳ በምን ይለያቸዋል? ደፍረቱና ህሊናው ካለዎት በአፄ ሃለስላሴና በሃይለስላሴ ጉግሳ ጋር የነበረቀውን ቅራኔ ተንትነው ያሳዪን፡ከዛ ሃይለስላሴ ወደዛ ውስኔ ለምን እንደደረሰ ግንዛቤ እናገኛለን፡፡ ፕሮፌሰር ከባንዳነት ጋር ንክኪ የለኝም ብለዋል፤ በጣሊያን አስተዳደር ውስጥ ለመስራት በጣሊያን አዳሪ ትምህር ሲማሩ የነበሩበት ከምን ይቆጠር ነው የሚሉት?

 6. Dan says:

  ፕ/ር መስፍን በዕድሜ (ነፍሱን ይማረውና) የአባቴ ታላቅ ናቸው:: አባቴ በዕድሜ ከኔ የሚበልጡ በርካታ የልጅ ልጆችን አይቷል:: ይህም ማለት በዕድሜ አያቴ ሊሆኑ ከሚችሉ የዕድሜ ባለጸጋና አዋቂ ሰው ጋር ነው ኧፌን የማሾለው:: ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም ከስራዎቻቸው እንደተረዳሁት “ልጅ ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም:: ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም:: ወዘተ” የመሳሰሉ ተረቶች ለክሽፈታችን ምክንያት ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ስለተረዳሁና ለነጻ ውይይት በራቸው ክፍት ነው ከሚል እምነት ተነስቼ ነው::
  ባለፈው አስተያየቴን ስሰጥ ፕ/ርን እንዲህ ብያቸው ነበር፦ “ለምሳሌ የአባይ ግድብ እውን እንዳይሆን ጠንክረው ይሰራሉ: በሚል ፍርጃ የባንዳነት ቅጥያ ከገዢው መደብ የተሰጣቸው በርካታ የተቃዋሚ ጎራ አሉ:: በዚህ ረገድ እርሶም ከዚሁ ሳይመደቡ አይቀሩም::” ይቺን አባባሌን ግን በቅንነት የተረዱልኝ አይመስልም:: ከመንግስት ተብዬው በተቃራኒ አቋም የያዘ ዜጋ ባንዳ እየተባለ መኖሩን ለመረዳት የሮኬት ሳይንቲስ መሆን አይጠበቅብንም::

  ፕ/ር አሁን በወያኔ ጀሌዎች ባንዳ ስለተባሉ በጣም የተሰማቸው ይመስላል:: ዛሬ በህይወት የሌሉትን ስለራሳቸው ምንም ነገር መናገር የማይችሉትን ሙታንን ግን ባገኙት አጋጣሚ ባንዳ ሲሏቸው ይኖራሉ:: ይህን የሚሉትም ልጆቻቸውን ለማሸማቀቅ መሆኑ ነው:: ጽሁፋቸው በንዴት የተሞነጫጨረ ለመሆኑ ብዙ ምልክቶችን መጥቀስ ይቻላል:: ንዴት ጊዝያዊ እርካታን ያጎናጽፍ እንደሆን እንጂ ዘላቂ መፍትሔን አያስገኝም:: ፕ/ ርን እንዲህ የሚያናድደው ቃል ሌሎችንም በዛው ልክ ሊያስቆጣ እንደሚችል ተረድተው ጊዜያዊ ስሜታቸውን የሚያበርድላቸው ቃላት ከመጠቀም ይልቅ ሊያቀራርበን የሚችል ነገር ቢጽፉ እንዴት ድንቅ ነበር:: ይህን ስል ታድያ ባንዳ ተብለው ከተፈረጁ ሰዎች መካከል ንኪኪ ኖሮኝ አይደለም:: ቢኖረኝም እነሱ በፈጸሙት ግድፈት ልሸማቀቅ የምችል አይነት ሰው አይደለሁም:: የተሳሳተው ግንዛቤያችን ሰዎችን የሚያበሳጭና የሚያራርቅ መሆኑን ስለተገነዘብሁ ነው:: እንደ ግለሰብ የዚህ ማህበረሰብ ውጤት ነን:: የክፉውም የደጉም ቅይጥ ውጤት:: እኛነታችንን ለማደስ የተሳሳተን ማረም ተገቢ ነው:: ለማዋረድ መሞከር: መዝለፍ: ማራቅ ወዘተ ግን የከሸፍንበት ያረጀ መንገድ ነው:: ያረጀውን መንገድ የከሸፍንበትን ባህል የሚተች ሰው: አዲስ አቅጣጫና መንገድ ሊያሳየን ባይሞክር እንኳን፤ ያንኑ የተቸውን መንገድ መከተል የለበትም::

  ፕ/ር ያልተገነዘቡት አንድ ትልቅ ግድፈት ደግሞ አለ:: የነ አሉላንና ፊልሞንን አስተያየት ያነበበ ሰው በጣም ጥቂት ሰው ነበር:: ለምሳሌ አሉላ ጆቫኒ ሰሎሞን የተባለ አስተያየት ሰጪ እዚህ ብሎግ ላይ አላየሁም:: ሌላ ቦታ ላይ ሰጥቶ ከሆነም አላነበብኩትም:: ሌላውም እንደኔ ያላነበባቸውና ጭራሽ የማያውቃቸው ብዙ ታዳሚ እንደሚኖር አስባለሁ:: ለነሱ አስተያየት የተሰጠው የፕ/ር መልስ ግን በየድረገጹ ተሰራጭቷል: በርካታ አንባቢያን ጋር ደርሷል፤ ከነ አስጸያፊና ሃላፊነት የጎደለው ቃላቱ ጋር:: አንዳንዴ ፕ/ር ምን ሊያስተምሩን እንደሚፈለጉ ሳስበው ግራ ይገባኛል:: እንዳለመታደል ሆኖ እኛ ዘንድ የተማረ የሚባለው ተመጻዳቂና ጥራዝ ነጠቅ ሆነብን እንጂ: አለማወቁንና ድንቁርናው በቅድምያ መቀበል ያለበት ተማርኩ ባዩ ነበር:: ብዙ ባወቅን ቁጥር ይበልጥ የምናውቀው አለማወቃችንን ነውና እንደዚህ አይነት ሃላፊነት የጎደለው አስጸያፊ አባባል ከፕ/ር መስፍን አይጠበቅም ነበር:: ከኛ በባሰ ሁኔታ የማያውቅን ሰው: እውቀትን መቅሰም እንዲችል ፕ/ር ከመረጡት መንገድ የተሻለ ሌላ ውጤታማ መንገድ ነበር::

  ፕሮ ስሜቶትን ገታ አድርገው ይጻፉ:: ስሜቶን ተቆጣጥረው የሚጽፉት ነገር ዘመን ተሻጋሪ እንደሆነ እኔ እመስክራለሁ:: በስሜት የተነዱ ግዜ ግን የነ ፊልሞንና ዳንኤል ብርሃነ መደበሪያ ሆነው ነው የሚቀሩት:: ለድፍረቴ ይቅር ይበሉኝ: ያወራሁት ግን ሃቅ ነው::

  • Andinet says:

   ውድ ዳን
   ለማለት የምፈልገውን በተሻለ እና በሚማርክ ሁኔታ ስለገለጽከው በጣም አመሰግናለሁ፡፡
   ፕሮፌሰር በቀናነት ይህንን ምክር ቢቀበሉት እና በቀጣይ ጽሁፎቻቸው ምንኛ ደስ ባለኝ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ዕውቀቱም፡ተሞክሮውም፡ ችሎታውም እንዲሁም የአገር ወዳድነትና ተቆርቋሪነት ስሜት በሚገባ አላቸው፡፡ ትንሽ ትህትና ብቻ ጣል ያርጉበት ፡፡

 7. haq says:

  ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ባለፈው እሮብ ከአባይ ጉዳይ በተያያዘ የጦርነት ቅስቀሳን ለመገሰጽና የግብጽን የጦር ሀያልነት ‹ለማሳወቅ› አንድ ጽሑፍ አስነብበውናል፡፡
  ጽሑፉ በጥድፊያ እና/ወይም እንደተለመደው የኢሕአዴግን ባለስልጣኖች ለማብሸቅ ተብሎ የቀረበ ስለመሰለኝ አላተኮርኩበትም ነበር፡፡
  ነገር ግን እሳቸው የጽሑፋቸውን ግልብነት (shallowness) አስተውለው – ጠለቅ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል ይሞክራሉ ብዬ ስጠብቅ፣ ትችት የሰነዘሩባቸውን ሰዎች በመሀይምነት መፈረጅ ነው የመረጡት፡፡
  ሰለሆነም እንደው ምናልባት እሳቸውም ሆነ ብለው የሚያምኑ የሚመስሉት ደጋፊዎቻቸው ልብ አላሉት እንደሆን ለማስገንዘብ፤ ስለፕ/ር መስፍን ጽሑፍ አንድ ሁለት ልበል፡፡
  የ ጽሁፉ ዋነኛ ጭብጥ በሚከተለው ጥቅስ ይወከላል፡፡
  ‹‹ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤……ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ››
  የትኛው ‹የጠገበ› ባለስልጣን ነው ለጦርነት የቀሰቀስው?
  የመንግስት ባለስልጣኖች አንድ ሁለት ጊዜ – ከ2 ዓመታት በፊት – ‹‹ግብጽ ብትወረንስ›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ታሪክ ጠቅሰው እንደማይፈሩ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ፡፡ (ግን ሌላ ምን መልስ ሊሰጡስ ይቻላቸዋል?) ከዚያ ባለፈ ግን ግብጽን አስመልክቶ አዎንታዊ እንጂ አሉታዊ ዘገባ እና ቅስቀሳ በመንግስት ሚዲያ ሰምቼ አላውቅም፡፡
  እንዲያውም ከካይሮ ግድም አሉታዊ ወሬ በመጣ ቁጥር የመንግስት ባለስልጣኖች ጦርነትና ግጭት የመከሰት ዕድሉን ስለሚያጣጥሉ፣ አንዳንድ ታዛቢዎች ‹‹እነዚህ ሰዎች አስጠንቁለዋል እንዴ›› ያሉበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ – ከአንድ ወር በፊት የጠ/ሚኒስተሩን ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳን ሳናግረው ‹‹ግድቡን እንደማናቆም ሲያውቁ ራሳቸውን ከእውነታው ያስታርቃሉ›› ነበር ያለኝ፡፡
  እርግጥ መንግስት በይፋ የሚያሳየው መተማመን ስልታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ግብጾችንም ‹‹ማነው ከግድቡ ጀርባ ያለው?›› የሚያሰኛቸውም እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡
  ሌላው የጽሑፉ አንኳር ሀሳብ እንዲህ ይነበባል፡-
  ‹‹አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ — የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤››
  የመረጃ ምንጩን ባይጠቅሱም ከመጠነኛ አሰሳ በኋላ እንደተገነዘብኩት መረጃውን ያገኙት ከGlobalFirePower.com ነው፡፡ የዌብሳይቱን የደረጃ አሰጣጥ ስልት ከተረዳሁ በኋላ ግን መስፍን ጽሑፋቸውን በችኮላ እንደጻፉት ደመደምኩ፡፡
  ከGlobalFirePower.com ደረጃዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት ላቅርብ፡-
  * የእያንዳንዱን ሀገር ጠቅላላ የጦር አይሮፕላን (ጀት፣ ሔሊኮፕተር፣ ወዘተ) ብዛት በመቁጠር፡- በአየር ሀይል ለኢራን 5ኛ፣ ለሳውዲ አረቢያ 11ኛ፣ ለግብጽ 14ኛ፤ ለእስራኤል 20ኛ ደረጃ ይሰጣል፡፡
  * በባሕር ኃይል (ሁሉንም የባህር ላይ የጦር ተሸከርካሪዎች በመቁጠር) በሰጠው ደረጃ ግብጽ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ከቱርክ ከፈረንሳይ ከጣልያን ከሕንድና ከእንግሊዝ ትበልጣለች፡፡
  * በታንክ ብዛትም የግብጽ ደረጃ ከህንድ ከሩሲያና ከፈረንሳይ በላይ ነው፡፡
  * የግብጽ ወታደር ብዛትም (ግማሽ ሚሊዮን ቋሚና 1 ሚሊዮን ተጠባባቂ ወታደር በመያዝ) ከፈረንሳይ ከእንግሊዝና ከእስራኤል ይበልጣል፡፡
  ይህን የደረጃ አሰጣጥ መሠረት አድርጎ የወታደራዊ ሀያልነትን መመዘን አሳሳች መሆኑ ለማንም ግልጽ ስለሆነ ብዙ አልልም፡፡
  ያም ሆነ ይህ ግን የኢትዮጲያ ጦር ሀይል የወታደር ቁጥር እና የበጀት መጠን ውስን እንዲሆን የተደረገበት ሳይንሳዊ መነሻ ሲኖረው፤ ግብጽ ደግሞ የጦር ሀይል ብዛትና ወጪ ማብዛት የፈለገችበት የፖለቲካ ምክንያት ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ከቆየው ከፊል-ወታደራዊ ስርአቷ ባህርይ ጋር ይያያዛል፡፡
  ይልቁንስ ፕሮፌሰሩ ሊያነሱ ይገባ የነበረው ጥያቄዎች፡-
  * በዚህ ዘመን የጦርነት መነሳት ሆነ ውጤት በጥይት ብዛት ነው እንዴ የሚመሠረተው? (የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ፣ የinternational public opinion ወዘተ ወሳኝ ሚናስ)
  * እኛ እና ግብጽ የጋራ ድንበር ስለሌለን፤ ግብጽ ሺህ ኪሎሜትሮች ተጉዞ ለሚደረግ ጦርነት በቂ ክህሎት፣ ልምድ፣ ድርጅት እና ሎጂስቲክ አላት ወይ?
  * ሱዳን ወይም ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠር የግብጽን ሠራዊት ለማስፈርና ለማሳለፍ ይፈቅዳሉ ወይ?
  አንዳንድ ሰዎች፣- ውስን የዓየር ወይም የኮማንዶ ጥቃት(surgical attack) ሀሳብ በማንሳት የመስፍንን ጽሑፍ ለማሻሻል ይሞክራሉ፡፡ እዚህ ላይም የቴክኖሎጂ ጥያቄ አለ፡፡ ከካይሮ ተነስቶ ኢትዮጲያ ደርሶ የሚመለስ አይሮፕላን ግብጽ አላት? (ስለሌላትም) የሱዳንን ዓየር ክልል ጥሶ መብረር ብቻ ሳይሆን ማረፊያም ማግኘት ትሻለች፡፡ እናስ ሱዳን ትፈቅዳለች?
  አንድ ነገር ልብ በሉ፡- ግድቡ ሲያልቅ ለማፍረስ ጥቂት ከባድ ቦንቦች ወይም ፈንጂዎች ሊበቁ ይችላሉ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ማጥቃት የሚያስፈልገው እንዳለ የፕሮጀክት ሳይቱን ይሆናል፡፡ (ገና በጅምር ላይ ያለን ቤት ማጥቃት እና ተሠርቶ ያለቀን ቤት ማጥቃት አድርጋችሁ እዩት)
  እነዚህንና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች ሳይመልሱ ታንክ መቁጠር ግልብ ትንተና ይሆናል፡፡
  ለማንኛውም ከሀይማኖት ወይም ፈሪሀ-እግዚያብሔር በመነሳት በድፍኑ ‹ጥጋብ ውርደት ያስከትላል› ብሎ መናገር ቢቻልም፤ የፕ/ር መስፍን ጽሑፍ ግን የመንግስት ሀላፊዎች ‹ጠግበው› ለጦርነት መቀስቀሳቸውን ሆነ ‹ጥጋባቸው› ‹ውርደት› እንደሚያስከትል በበቂ አላስረዳም፡፡
  እርግጥ የግብጹ Al-Jamaa al Islamiya መሪ ኢትዮጲያ በአባይ ላይ የምትሠራው ሥራ የጦርነት አዋጅ ነው በማለት አፀፋውን ለመመለስ ዛቻ ብጤ አሰምቷል፡፡
  ፕ/ር መስፍን የ‹ጠገቡ መሪዎች ለአጉል ጀብደኛነት ዝና› እየነዱን እንዳሉ አድርገው የቆጠሩት የሕዳሴ ግድብ ሥራን ይሆን እንዴ?I taken from http://danielberhane.com/2013/06/09/mesfin-woldemariam-nile-issue-commentary/

 8. Siltan says:

  ስለማይድን ድንቁርና ከዚህ ከፕሮፌሰሩ ጽሁፍ የበለጠ ሌላ ማስረጃ ይገኝ ይሆን? ፕሮፌሰሩን የተቹት ሰዎች ያነሱት ጉዳይ እኮ ትክክል ነው። ገና የግብጽ ፖለቲከኞች የጦርነት ነጋሪት እንደጎሰሙ ፕሮፌሰሩ ተነስተው የግብጽ ጦር ሃይል ጠንካራ ስለመሆኑ አሃዝ ጠቅሰው አተቱ፤ ያውም ዛቻው ከኢትዮጵያ ወገን የተሰነዘረ አስመስለው። ይህም የችኮላ ዘለፋቸው ለሃገራቸው መንግስት ካላቸው ጥላቻ እና ለታህሪር ካላቸው ናፍቆትና ፍቅር የመነጨ ስለመሆኑ ትንተናቸው ያሳብቃል። በተለይመ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ደንታ እንደሌላቸው ራሳቸው እማኝነተ ሰጥተዋል። ብዙ ኢትዮጵያውያንም የፕሮፌሰሩን አካሄድና ሃሳብ ነቀፉ፤ አሪፍ ግጥሞችና መጣጥፎችም በፌስ ቡክ ተለቀቁ። ይሄኔ ፕሮፌሰሩ ስህተታቸውን ለማረምና ሃሳባቸውን በተሻለ መልኩ ለማብራራት እድሉን ከሚጠቀሙበት ይልቅ የጥላቻ ሎሌ ሆነው ወደተለመደው ዘለፋቸው ነጎዱ። የሚገርመው ደግሞ ተቺዎቻቸውን አንዱን ጣሊያናዊ ለማስመሰል ሲጥሩ ሌሎቹን ደግሞ ጅምላ ጠቅልለው ወደአንድ የሚጠሉት ብሄረሰበ ማእቀፍ አስገብተው በጅምላ ረገሙ። ድንቁርናንም በዚህ መልኩ ወደሚጠሉት ወገን ሊያራግፉ ይህንን ጽሁፍ ጻፉ። የማይድን ድንቁርና ይሏችኋል ይህ ነው።

 9. gedeyon says:

  yodit enesu yetu gare challenge aderguachu??? yesachewun tsehufe eko challenge madrege be merega ..ezih gare endi yalut lekaydelem edezih newu… ezya gare endezi… belewu silu nebere.. en alula eko endewu bedefenawu prof. mesfen selesafut becha lemekawom newu . selezih bemerega yemayamnene denkoro .. denkoro neh maletu menne yaswekesachewal profesoren. demom yaltu bemulu tekekele newu bemeregaja yetdegefe!! selezih menged meriwochen atazenagun maletu atbeke edegefalehu..professor.. egzibeher endemen tena yestotena yezechen hager tensae yasayot professor mesfen . engzer yetebekot.

 10. Wehab Rebi Abdul Aziz says:

  “Trash?!”ha ha ha….Daniel Berhane,you’re cracking me up…..phew…The professor just like making the Woyane small minds jump.It is fun. So, Dani go and jump like ከበሮ መች…

 11. Pingback: Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር | Danielberhane's Blog

 12. yodit sissay says:

  ይህ ከላይ የሚነበበው መልስ challenge መደረግን ከሚፈራ ተራ ሰው ሊደመጥ የሚችል አንጂ ከአንድ ፕሮፌሰር የሚጠበቅ መልስ በፍትፁም አይደለም :: ከርሶ የሚጠበቀው መልስ, ግለሰቡ በሰጠው አስተያየት ላይ, የተሳሳተ ነው ብለው ያመኑበትን ሃሳብ አስመልክቶ, ቀጥተኛ መልስዎን መስጠት; ወይም ስሀተት ነው ብለው ባመኑበት ሃሳብ ላይ ያሎተን ትክክለኛ ማስለጃዎች ለኣንባቢያኑ ማቅለብና ፍርዱን ላንባቢያኑ መተው; አንጂ, ሰው የርሶን ሃሳብ ስለተቃወመ ብቻ, የግለሰብን ማንነት በዚህ መልኩ ማጥቃት; መሳደብና የትለያዩ ስሞች በመስጠት ማጣጣል … ለአንባቢው በጣም የሚያስደንቅ ከመሆኑም አልፎ, በራስዎ አቅዋም ላይ ያሎትን አለመተማመን
  የሚያመላክትበት ሁኔታን ይፈጥራል::
  ( by the way, i`m surly not የአኢሃዴግ ካድሬ )!!

 13. Andinet says:

  ተስፋዬ ገብረአብ በጻፈው የጋዜጠኛው ማስታወሻ መጽሀፍ መነሻ በወያኔው ሴኮ ቱሬ ሙሉ ለሙሉ በዘለፋ የታጨቀ ምላሽ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ተስፋዬ ገብረአብ ለሴኮ ቱሬ ምላሽ ሲሰጥ የጻፈው ቃል በቃል ባላስታውሰውም ሃሳቡ እንዲህ የሚል ነበር፡፡
  “ ውብ ስነ ጽሁፍ ኮለል ብሎ በሚፈስ ንፁህ የኩሬ ውሃ ይመሰላል፡፡ በውብ ቃላት የአንባቢን ስሜትንና ቀልብን ይዞ የሚፈለገው ውጤት ጋር ይደርሳል፡፡ መጥፎ ስነ ጽሁፍ ግን በጎርፍ ውሃ ይመሰላል፡፡ የማይዘው ትርኪ ምርኪ የለም – የበሰበሰ ቆርቆሮ፡ ቆሻሻ ላስቲክ፤ ግንዲላ፤ የሞተ ውሻ……………….”
  እስቲ ለገንቢ ውይይት ጽሁፎቻችን እና አስተያቶቻችን እነደ ጎርፍ ውሃ ሳይሆን እነደ ኩሬ ውሃ እንዲፈሱ እናድርጋቸው፡፡

  • Kidus says:

   እኔ ምለው ኩሬ ውሃ ይፈሳል እንዴ

   • Andinet says:

    ይቅርታ ኮለል ብሎ በሚፈስ ምንጭ ወይም ጅረት ልትለው ትችላለህ፡፡ ዋናው ሃሳቡን ከተረዳህ በቂ ነው፡፡ ከሃሳቡ ይልቅ ቃላቱን የምትፈልገው ከሆነ ግን ተስፋዬ ገብረአብ ያለውን ፈልገህ ብታየው የተሻለ ነው፡፡

 14. Andinet says:

  የፕሮፌሰሩም የፊልሞንም ጽሁፎች በዘለፋ የታጨቁ ናቸው፡፡ ልዩነቱ ከሁለቱም ጽሁፎች ዘለፋዎችን ስናወጣ የማሪዮ ባዶ ይሆናል፡፡ምክንያቱም የጻፈው ስለ ፍሬ ሃሳቡ ሳይሆን ስለ ፕሮፌሰሩ ብቻ ነው፡፡ በሃሳብ መሞገት የሚያቅተው ሰው ትክክለኛ ባህሪ ይህ ነው፡፡ የፕሮፌሰሩ ግን በውስጡ ከዘለፋዎቹ ጋር እውነታን የያዘ ቁምነገር አለው፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደሱ ዘለፋ ውስጥ ባይገቡ ኖሮ ብዙ ቁምነገሮችን ያካፍሉን ነበር፡፡

  • fer says:

   What a low-life.

  • Lambadyna says:

   minuu gariii???? eskii ezhi gari belina melise site alebalezya Erashine newii emimeleketeweiii

  • infinity says:

   Daniel Berhane: where did you get your law degree….I hope it is not from TRASH University. You should first know at least the ethics of being a lawyer.

  • Teddy says:

   አይዞህ ዳንኤል! ይህ ለአንተ አይነቶች፤ ሆድ አደር ሰዎች የተጻፈ ነው። ዘልፈህ ዘወር ከምትል ይልቅ፤ መንገድህን ፈትሸህ፤ ያን የማይረባ ብሎግህን ሕይወት ብትዘራበት መልካም ነው። ካለበለዚያ ግን፤ የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማሽን መሆን፤ ዋጋ የለውም!

  • Beniyam says:

   Aye Daniel Berhane, endante yale, ende gari feres gera ena kegn yemayay, minalbatim lehodu yadere ayche alawkim. Kesihitetih yemitimar eyemeselen bizuwochachin beza blogih lay asteyayet eneset neber, Ahun gin tesfa koretkubih. Gin limkerih, ebakih tinish anbib- Addis raiye metsehetin bicha sayhone, leloch behasab yemileyutin anbib. Sele getochih yechaka nuro ena maninet tinish anbib, sele tarik tinish anbib, keza aynih yigelet yihonal.

  • Senait says:

   Daniel, you are supposed to show us how this article is trash rather than insulting the Prof.

   ድንቁርና መጥፎነቱና አደገኛነቱ ከኋላውም ሆነ ከፊቱ የሚያይበት ዘዴ አለመኖሩ ነው፤ ለዛሬ፣ ለሆድ ብቻ መኖርን ዕለታዊ ዓላማው የሚያደርግ ነው፤ አንጎሉ በድንቁርና የተሞላ ለምንም ሌላ ነገር ቦታ የለውም፤ ይህ ድፍን ወይም ፍጹም ድንቁርና ነው፤ ተስፋ-ቢስ ነው፤ አንጎሉ ውስጥ ድንቁርና ያልደረሰበት ትንሽ ቦታም ቢሆን ከአለ የእውቀትን ዘር ለመዝራትና ብርሃን ለመፈንጠቅ ዕድል ይኖራል፤ አለዚያ ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡

 15. Teddy says:

  ክቡር ፕሮፌሰር፤ ለመጣጥፍዎ አመሰግናለሁ። ሆኖም ግን፤ እንዲህ አይነት መልስ አያስፈልግም ከሚሉት ውስጥ ነኝ። በእርስዎ ላይ የሚደረገውን ዘመቻ፤ ህሊና ያላቸው ኢትዮጵያውያን ጠንቅቀው ያውቁታል። አይናችን እያዬ፤ እነ እስክንድርን የመሰለ ብዕረኛ፤ እነ አንዷለምን የመሰለ ወጣት ፓለቲከኛ፤ እነ እርዮትን የመሰለ እንስት ብዕረኛ፤ የአሸባሪነት ታርጋ ለጥፎ፤ እንዴት እያሰቃያቸው እንደሆነ እናውቃለን!!! ሰለዚህም፤ ለእንቶ ፈንቶ ቅርሻታቸው መልስ በመስጠት፤ ጊዜዎንና ጉልበትዎን አይጨርሱብን። እኛ ከእርሰዎ የምንፈለግገው፤ እንዴት አድርገን፤ ከእነዚህ እፉኞች አገራችንን ነጻ እንደምናወጣ፤ አቅጣጫ መሪ፤ መንገድ ጠቋሚ ጽሑፎችዎን ነው።
  እድሜና ጤና ይስጥልኝ።

 16. yonas says:

  በቅርቡም በባድመ ጦርነት ፉከራውና ሽለላው ወደእፍረት ሲለወጥ አይተናል፤ ድንቁርና የሚደነድነው እውነትን፣ ከእውነት ጋርም እውቀትን እያፈነ ነው፡፡

 17. Wehab Rebi Abdul Aziz says:

  ጤና ይስጥልኝ የኔታ!
  የዛሬዋ ጦማርዎ “We are all born ignorant,but one must work hard to remain stupid.”የምትለዋን የቤንጃሚን ፍራንክሊንን እድሜ ጠገብ መልእክት አስታወሰችኝ::ለነገሩማ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ደናቁርት ከቀድሞዎቹ ቢጤዎቻቸው የሚለዩት በማንበብና መጻፍ ክህሎታቸው ብቻ መሆኑን ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው::የዘመናችን ደናቁርት የሚጽፉና የሚያነቡ ነገር ግን የሚጽፉትን የማያውቁ የሚያነቡትን የማይረዱ የምድራችን ጉዶች ናቸው::ከደናቁርት የዛገ አዕምሮ ፈልቀው ባልተባ ብዕራቸው ተከትበው በሚነዙ መርዞች ሌሎች እንዳይበክሉ ሁሉም የበኩሉን ማድረግ ይጠበቅበታል::
  ወሀብ ረቢ ዓበደል አዚዝ
  ሙሱል
  ኢራቅ

 18. Araya says:

  ጎበዝ አሁን ለመስፍን እርገጤ ምን ተብሎ ነው መለስ ሊሰጥ የሚችለው? ከተለጠፈው ጽሁፍ ጋርስ ምን ያገናኘዋል? ማንም እብድ እየተነሳ የሚጽፈውን አስተያየት በተለይ ከአርእስቱ ጋር ግንኘነት የሌለው ከሆነ በግል ዲያሪው ላይ ይለጥፍ እንጅ አድሚኑ ሊፈቅድለት አይገባምም ለዚህ ብሎግም አሉባልታዎችን ማስተናገድ አይመጥንም!!

 19. mesfin Ergete Azbitie says:

  ምስኪን መስፍን ወልደማርያም ከነመርዙ ሊሞት በጣም ጥቂት ጊዜያት ብቻ ቀርቶታል ጥላቻ የሚባል ህመም ተጠናውቶት ሲዘባርቅ ይኸው እኛም ደረስንበት አክሊሉ ሃብተወልድንና ስድሳ ጉዋድኞቻቸውን አስገድሎ በዓሉ ግርማን በልቶ በስተርጅናም የጥላቻ መርዝ ሲተፋ ይኖራል

  • engida says:

   በዚህ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በታሪክ ተከራክረው መልስ መስጠት ሲያቅታቸው ፣ ወደ ስድብ ይገባሉ ፡፡ በተለይ ደግሞ ለመሳደብ ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት የተጸውኦ ስም ወይ የአማራ ወይም የኦሮሞ ነው ፡፡ ይህ እጅግ የተበላ ኋላ ቀር ብልጠት ነው ፡፡ አያትህን ቀና ብለህ መሳደብህ ኒሻን ያገኘህ መስሎህ ከሆነ ፣ የተከናንብከው ክብረት ሳይሆን ውርደት ነው አዝብጤ

   • Siltan says:

    Dear Ingida, I think, Azbite has presented facts, not insults. either the professor or his fans need to disprove it with concrete evidence that shows otherwise. It is not helpful to to reject ones opinion and views by labeling him or guessing his ethnic origin (BTW: it is interesting that you and the professor are obsessed with one thing, i.e., blaming the Tigrayans for everything, just like Hitler did for the Jews).

  • jhon says:

   ለምንድን ነው ግን እውነት የማይዋጥልን፡፡ ይህ ጽሁፍ ለተረዳው ነገሮችን በማስተዋልና በእውቀት መናገርን እንዲሁም መጻፍ እንዳለብን ነው፡፡ ስለ አክሊሉ ሀብተወልድና 60ዎቹ ስትናገር አንድ የምነግርህ ነገር ለነሱ ተቆርቁረህ አይደለም !!!!!!! ፕ/ር መስፍንን ለመዝለፍ ስለፈለክ ነው፡፡ አክሊሉ ሀብተወልድና 60ዎቹ ማን እንደገደላቸው(እንዳስገደላቸው) ማወቅ ከፈለክ አንብበህ የምትረዳ ይመስለኛል? ከመሬት ተነስቶ ሰውን መዝለፍና ማንቋሸሽ ከማን እንደተማርከው ማወቅ ቀላል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተራነትን የሚያሳይ ነው ስለዚህ አንድ ምክር ልምከርህ ወደ ሆድ የምታስገባውን ቀንስና ወደ ጭንቅላትህ የምታስገባውን ጨምር….በእኔ ይሁንብህ ከዛሬው ጀምር

  • Nolawi says:

   ውዳጄ
   mesfin Ergete Azbitie ስድብ የደደቦች ወይም የተሸናፊዎች መፍክር ነው፡፡ ሰኪ በ21ኛው መ.ዓመት ደርሰሃል ኒባቢን ልማድ አድርግ እንደ ገደልማሚቶ ዝም ብለህ የተጮኸውን አታስተጋባ ብቻ ፕሮፌሰርን ያቆይልን፡፡ ድሮም ከዝንብ ማር ማንም አይጠብቅም፡፡

  • realistic says:

   Andinet ! bezu kebaterk kelebu endehone yasasebeh eskaluleh tebelaleh lebanda bandanetun kemenger wchi min endibal tefelegaleh?mesfin Ergete Azbitie Ante gin bequmeh motehal

 20. Araya says:

  በኔ አስተያየት ይህ ጉዳይ እኮ ፐሮፍ ካነሱት የሀይል አሰላለፍ በዘለለ የግድቡን ዕቅድ ግልጽነት የጎደለውና በቂ ውይይት ያልተደረገበት (በተለይ ከግብጽ መንግስት ጋር) በመሆኑ የግንባታው መቀጠል እና ለዚህም የሚከፈለው መሰዋእትነት በኔ እይታ አላስፈላጊ እና አጉል ጀብደኝነት ነው፡፡ ምናልባትም ይህን ለመረዳት “አደጋ ያናዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” በሚለው የፕ/ር መስፍን መጽሀፍ ላይ የተቀመጡትን ካርተዎች ብቻ በማየት መረዳት ይቻላል፡፡ አብዛኛው የግብጽ ህዝብ አሰፋፈር እና ኑሮው የተመሰረተው በአባይ ዙርያ ከመሆኑ አንጻር የአባይ ጉዳይ ከኛ ከኢትዮጵያውያን በተለየ ለግብጾች የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ሁነት ተነስተን ደግሞ የግንቦት 20 ቀን “የአባይን አቅጣጫ አዞርነው” የሚለው ዜና (ገና ለገና ቀሽም የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ለመስራት) በግብጽ ህዝብና መንግስት ላይ ድንጋጤ ይፈጥራል (ከፕሮጀክቱ ግልጽ ካለመሆን አንጻር)፡፡ ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያ አባይን ለመጠቀም የግብጽ ይሁንታ ያስፈልጋታል ማለት አይደለም! መጀመሪያውን በቂ ውይይት አልተደረገበትም፤ እንኳን ለግብጾች ለኛ ለኢትዮጵያውያኖች እንኳ ዱብ እንዳ ነው የሆነብን ለማለት ነው፡፡
  በሌላው አቅጣጯ ለማየት ደሞ ስሞክር አሁን ሀገሪቷ ያለችበት ሁነት የውስጥ ፖለቲካው ጫፍና ጫፍ መወጠሩ፣ የድሀነት ደረጃችን የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሱ፣ የወያኔና የሻቢያ ጦርነት ጠባሳ ገና ያልደበዘዘ መሆኑ፣ ሶማሊያ ውስጥ ገብተን የሰራነው ወንጀል እና በዙሪያችን በአረብ ሊግ ማህበር እንደመከበባችን የመሳሰሉትን ችግሮች ተሸክመን ስለጣርነት መለፈፍ ስለሀገር መቆርቆር ሳይሆን አጥፍቶ መጥፋት ነው የምለው፡፡ እስቲ መረጃ ያላችሁ ንገሩን ያቺ ትላንት ከኛ ጉያ የወጣች ኤርትሪ ጋር እንኳ የተደረግው ጣርነት ስንት ወጣት ገበረ፣ ሰንት ቢሊዮኖችን በላ፤ እንኳን እንደ ፕ/ር መስፍን አይነት ምሰሶ ይቅርና ማንም ማንም ሰው ሀገሩን ወሮ ለመጣ ወደኋላ የሚል የለም፡፡ ግን ምርጫ አለ መጀመሪያ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብም (ቦንድ መሸጥ ብቻ አይደለም) ሆነ ከግብጽ እና ከአባያ ተፋሰስ ሀገሮች ጋር ተጠይቀው ብቻ ሳይሆን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄደው እስከመጨረሻው ጠብታ መደራደርና ማስረዳት ይጠበቅበታል፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለአካባቢው ሰላም ሲባል፡፡ እነዚህን ችግሮች ይዘን እና መደረግ ያለባቸው ሳይደረጉ ዘራፍ ብሎ መደንፋት ፕሮፍ እንደሚሉት ድንቁርና ካልሆነ ምን ይባላል!!!

  • yonas says:

   እስቲ መረጃ ያላችሁ ንገሩን ያቺ ትላንት ከኛ ጉያ የወጣች ኤርትሪ ጋር እንኳ የተደረግው ጣርነት ስንት ወጣት ገበረ፣ ሰንት ቢሊዮኖችን በላ፤

 21. Pingback: ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል | yabedew / ያ - በደው

 22. enidew hagere meche yihon dehina lehageru kelibu enije ke hodu yemayicheneke mihur yemiwetalat says:

  yiha sewiya yetemarewin neger hulu ejinaw adenkurotal meselegne kesu yemayitebeke neger new yemiyaweraw

  • Lambadyna says:

   Ere friend erasihine atasifogire kelaye Eyetenegerihiii kesire minime ekoo manibebi ena meredatii endematichile eyasayehii newi. Eskii ezihi garii yalewii hasabii ……bilehiii techii eeskii. Erigite andine hasabi betigisite adimito weye anibo emigebaweini melise mesitetii yeayimoro sirani yiteyikalei kedimomo yetedeladele yehasabi meseretii yasefeligaleii yeha hulu kelele demoo kelelochi eyetemarooo erasine mabikati yichalalie ekooo?

 23. Gerazmach Chilomader says:

  የኔታ
  መዳን ይችላል ግን ለህክምናው ፈቃደኛ ሆኖ ለሚታከም የድንቁርና ታማሚ አለበለዚያ የሀኪሙን ጊዜ እና እውቀት ማባከን ነው ድንጋይ በሂደት በጠብታ ውሃ ወደ ስብርባሪ ኮረት ይቀየራል ግን አንድ አንድ ድንጋይ ወይ ፍንክች እናም ተስፋ አንቆርጥም እንሞክራለን እውነትን እውቀትን ትህትናንን እንሰብካለን

Comments are closed.