ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ

መስፍን ወልደ ማርያም

ሰኔ 2005

በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።

ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል።

አሜሪካ በግብጽ ላይ የተከለው ጥፍሩ ሲነቃነቅ መነቀሉ አለመቅረቱን ስላወቀው ሌላ የሚተክልበት አገር ይፈልጋል፤ በአካባቢው የግብጽን ነፍስ የሚነካ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም፤ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ስትመረጥ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፤ በመሀከለኛው ምሥራቅ የአረቦችን የተባበረ ኃይል ለመቋቋም የተመረጡ ሦስት አረብ ያልሆኑ አገሮች — ቱርክ፣ ኢትዮጵያና ፋርስ (ኢራን) — ነበሩ፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ኃይል መሰማት በጀመረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ከከበቡአት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር የነበርዋትን የቆዩ ውዝግቦች ለመቋቋም የአሜሪካ ድጋፍ በጣም አስፈላጊ ነበር፤ አሜሪካን ከአውሮፓ አገሮች ጋር እየመዘኑና እያመዛዘኑ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተደረገው ዲፕሎማሲ (ዓለም-አቀፍ የሰላም ትግል) የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት በእውነት ከሚያኮሩት ተግባሮች አንዱ ነው፤ ይህንን ትግል አምባሳደር ዘውዴ ረታ ምስጋና ይድረሰውና የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሐፉ ግሩም አድርጎ አሳይቶናል።

ምናልባት ገና ያልተጠና ጉዳይ በዘመኑ ኢትዮጵያ የነበራት ታሪካዊ ክብር ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪክና ዝና ጋር ተዳምሮ በአፍሪካ ተደማጭነት ነበራት፤ ይህንን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገሮች ላይ የነበራትን ጫና (የዛሬውን አያርገውና) በመጠቀም አሜሪካ አፍሪካን በሙሉ ለዓላማዋ ለማሰለፍ ኢትዮጵያን መሣሪያዋ ለማድረግ ትሞክር ነበር።

እየቆየ የኢትዮጵያ መንግሥት የነጻነት መንፈስን በማሳየት ለአሽከርነት አልመች በማለቱና ለአሜሪካም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች (የእውቀት ጥበቦች) በመፈጠራቸው ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ አስፈላጊነትዋ በመቀነሱ አሜሪካ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ጀመረ፤ የ1966 ግርግር ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑን ጠለቅ ብሎ ማጥናት ያስፈልጋል፤ በዚህ መሀልም የሶቭየት ኅብረት ዓለም-አቀፋዊ ጉልበት እየተሰማ በመሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን ዓላማ ቀስ በቀስ እየለወጠ ሄደ፤ ከዚህም ጋር የሶቭየት ኅብረት ተጽእኖ እያደገ ሄደ፤ የአሜሪካ አያያዝ እየላላ ሲሄድ የሶቭየት ኅብረት አያያዝ እየጠበቀ ሄደ፤ 1966 የአሜሪካ መውጫና የሶቭየት መግቢያ ሆነ ለማለት ይቻል ይሆናል፤ ከዚሁ ጋር አብሮ የሚታየው በኢትዮጵያ የባህላዊው ሥርዓት መሰነጣጠቅና የቆየው ትውልድ መዳከም ነው፤ የአሜሪካ መዳከም ሶቭየት ኅብረትን ሲያጠነክር፣ የአሮጌው ትውልድ መዳከም አዲሱን ትውልድ አጠነከረ፤ ይህ ማለት አሮጌው ትውልድ ከአሜሪካ ጋር የተያያዘውን ያህል አዲሱ ትውልድ ከሶቭየት ኅብረት ጋር ተያያዘ፤ የኢትዮጵያ የውስጥ ሁኔታ ብቻውን ለውጥ እንዳላመጣና ዓለም-አቀፍ ሁኔታዎችና የልዕለ ኃያላኑ ተጽእኖም ምን ያህል እንደነበረ አመላካች ነው።

የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መውደቅና የአሜሪካ ተጽእኖ መዳከም በአንድ በኩል፣ የደርግ መፈጠርና የእነኢሕአፓና መኢሶን በአጋፋሪነት መውጣት ከሶቭየት ኅብረት ተጽእኖ መጠናከር ጋር በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ሁኔታን ፈጠሩ፤ የአዲሱን ሁኔታ አዲስነት በግልጽና በትክክል መገንዘብ ያስፈልጋል፤ በኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዓመታት ተከብሮና ታፍሮ የቆየው የዘውድ ሥርዓት ተናደ፤ ተዋረደ፤ በኢትዮጵያ ስር እየሰደዱ የነበሩ መሳፍንትና መኳንንት ከስራቸው ተመነገሉ፤ አዲስ የመሬት አዋጅ ወጣና የመሬት ከበርቴዎችን ሙልጭ አውጥቶ ገበሬውን በሙሉ እኩል ባለመሬት አደረገው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ ወጣ ባይባልም የኢትዮጵያ መሬት ነጻ ወጣ፤ ወታደር፣ ገዢ ሰላማዊው ሕዝብ ተገዢ ሆነ፤ ትርፍ መሬትና ትርፍ ቤት ሁሉ ተወረሰ፤ ቤትን የሚያከራዩ የኪራይ ቤቶችና ቀበሌዎች ብቻ ሆኑ፤ ደሀዎችንና መሀከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ኑሮ ለማቃለል ከሦስት መቶ ብር በታች የነበረው የቤት ኪራይ ሁሉ ተቀነሰ፤ ደርግ በሁለት ዓመታት ውስጥ የአብዛኛውን ገበሬ ኑሮና የአብዛኛውን የከተማ ነዋሪ ኑሮ የሚነኩ መሠረታዊ ለውጦችን አወጀ፤ እያደር ደርግ አስከፊ እየሆነና እየተጠላ ቢሄድም እነዚህ ሁለት አዋጆች ብዙ ኢትዮጵያውያንን እስከዛሬ ድረስ ለደርግ ባለውለታ አድርገዋል፤ እነዚህ አዋጆች ወያኔ ገና አፍርሶ ያልጨረሳቸው የደርግ ሐውልቶች ናቸው።

በውጭ አመራር ደግሞ የአሜሪካ ተጽእኖ ክፉኛ ተበጠሰ፤ አሜሪካ ማለት ስድብና ውርደት ሆነ፤ አሜሪካ ማለት በዝባዥነትና የቄሣራዊ ተልእኮ አራማጅ ማለት ሆነ፤ የአሜሪካ ማስታወቂያ ቢሮ ተዘጋ፤ ብዙ የአሜሪካ እንደወባ መከላከያ ያሉ የተራድኦ ድርጅቶች ተዘጉ፤ አሜሪካ ለዩኒቨርሲቲዎች ሲያደርግ የነበረውን እርዳታ አቋረጠ፤ በዚህ በተለይም የዓለማያ ዩኒቨርሲቲ በጣም ተጎዳ፤ የወባ ቢምቢም ከ‹‹ኢምፒሪያሊዝም›› ጭቆና ነጻ ወጣችና  አዲስ አበባ ደረሰች! ይባስ ብሎም አለማያ ዩኒቨርሲቲ ያፈራቸው አሉ የተባሉት በተለያዩ የእርሻ ሙያዎች የተካኑት አብዛኞች ሙልጭ ብለው ከአገር ወጡ።

አሜሪካ ከደርግ ጋር እየተጋገዘ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ክፉኛ አዳከመው፤ አያይዞም በኢትዮጵያ ዳር ዳር የሚነደውን እሳት አቀጣጠለው፤ በአንድ በኩል የውስጥ ተገንጣይ ቡድኖችን — የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት፣ የኤርትራ ነጻ አውጪ ድርጅት፤ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅት — በሌላ በኩል በድንበርም ሆነ በሌላ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር የሚፋለሙትን አገሮች ሶማልያንና ሱዳንን በግልጽ መርዳት ጀመረ፤ እንዲያውም ከግብጹ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር እየተመካከረ ኢትዮጵያን ለማዳከም ሞከረ፤ ከመሞከርም አልፎ ኤርትራን አስገነጠለ፤ የኢትዮጵያን ዙፋን ለወያኔ አመቻቸ፤ አሜሪካ ኮሚዩኒስት ነኝ የሚለውን ወያኔን በጎሣ ፖሊቲካ አስታጥቆ ቀለቡን እየሰፈረ በኢትዮጵያ ላይ ሠራው፤ ደርግ በሰይፍ ብቻ አንድነትን ለማምጣት መሞከሩና ሕዝቡን ለጦርነት ማነሣሣቱ አሜሪካንን አስደንግጦታል፤ ለአሜሪካ ደርግ የቀሰቀሰው የአንድነት ብሔራዊ ስሜት የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ የሚፈስስ መስሎ ታየው፤ በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያን የአንድነት ብሔራዊ ስሜት የማፈራረስ እቅዱን አወጣ፤ የሚያሳካለትንም ቡድን አገኘ።

 

ጣህሪር አደባባይና ዓባይ

ስንት ሰዎች በካይሮ ያለው አደባባይ ከዓባይ ጋር ግንኙነት አለው ብለው ያምናሉ? እስቲ ጠጋ ብለን እንመርምረው፤ ጣህሪር አደባባይ የግብጽ ሕዝብ የነጻነት ጥሪ ነበር፤ በአሜሪካ አጋዥነት ተጭኖት የነበረውን አገዛዝ ለማውረድ ቆርጦ መነሣቱን የገለጸበት አደባባይ ነው፤ የጣህሪር አደባባይን ማእከል ባደረገ ቆራጥ ትግል አገዛዙን አንኮታኩቶ አወረደው፤ በሰላማዊና ሕጋዊ ምርጫ የግብጽ ሕዝብ አዲስ መንግሥትን መሠረተ፤  የእስልምና ወንድማማቾች የሚባለው ቡድን አሸናፊ ሆኖ መውጣቱን አሜሪካም ሆነ እሥራኤል በጸጋ የተቀበሉት አይመስልም፤ ስጋት አላቸው፤ ለግብጻውያን ከአገዛዙ ጋር የሚወርድ ሌላ ጭነት አለባቸው፤ አሜሪካ ለራስዋም ዓላማ ሆነ ለእሥራኤል ዓላማ በግብጽ ላይ የምታደርገውን ከባድ ጫና ማንሣት ከትግሉ ዓላማዎች አንዱ ነበር፤ አሜሪካንና እሥራኤልን ያሰጋው የለውጡ ዓላማ አገዛዙን መጣሉ ሳይሆን በእነሱ ጥቅም ላይ ያነጣጠረውን ክፍል ነበር፤ በጦር መሣሪያ በኩል ግብጽ የአሜሪካ ጥገኛ ነች፤ ቀደም ሲል የሶቭየት ኅብረት ጥገኛ ነበረች፤ በአሁን በአለው የጊዜው ትርምስ አሜሪካ ግብጽ አንዳታመልጠው ይፈልጋል፤ ስለዚህም ስጋት አለው።

ግብጽን ሰንጎ ለመያዝና ለማስጨነቅ ከዓባይ የበለጠ ኃይል የለም፤ ዓባይን ሰንጎ  ግብጽን ለማስጨነቅ ከኢትዮጵያ  የበለጠ  ምቹ  አገር  የለም፤ በተጨማሪም ኡጋንዳን፣  ኬንያንና ደቡብ ሱዳንን ከአሰለፈ ለአሜሪካ ሁኔታው ይበልጥ ይመቻቻል፤ ጫናው በግብጽ ላይ የጠነከረ ሊመስል ይችላል፤ አሜሪካ የግብጽን ወዳጅነት ለዘለቄታው ለማጣት ይፈልጋል? ለእኔ አይመስለኝም፤ አሜሪካ የአረቦችን ሁሉ ጠላትነት ይፈልጋል? ለእኔ አይመስለኝም፤ ታዲያ እስከምን ድረስ ነው አሜሪካ ግብጽን ለማስጨነቅ የሚፈልገው? ዋናው ጥያቄ ይህ ነው

ትልቁ የአስዋን ግድብ ሲሠራ የነበረውን ውዝግብና መካካድ ለማንሣት ይዳዳኛል፤ ግን ሰፊ በመሆኑ አልገባበትም፤ አንዳንድ ሁነቶችን ብቻ ልጥቀስ፡– የምዕራብ ኃይሎች በተለይም አሜሪካና ብሪታንያ ለግድቡ ሥራ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ ሀሳባቸውን ለወጡ፤ የሶቭየት ኅብረት አንድ ቢልዮን ተሩብ ያህል ዶላር ለማበደር ዝግጁ ሆነ፤ ግብጽም ብድሩን ለመክፈል እንድትችል በዓለም-አቀፍ ኩባንያ ይተዳደር የነበረውን የስዌዝ ቦይ ብሔራዊ ሀብትዋ አድርጋ አወጀች፤ ይህንን በመቃወም ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና እሥራኤል ግብጽን ወረሩ፤ በተባበሩት መንግሥታት ግፊት (አሜሪካና የሶቭየት ኅብረት በተባበሩት መንግሥታት መድረክ ላይ በአንድ ላይ የቆሙበት ብርቅ ሁኔታ ነበር፤) ወረራቸውን አቁመው ከግብጽ ወጡ፤ በኋላ ነገሩ ሁሉ ተገለባብጦ ግብጽ ሶቭየት ኅብረትን ትታ የአሜሪካ ወዳጅ ሆነች!

አሜሪካ የሶርያን ሳይጨርስ፣ የኢራንን ሳይጀምር ከግብጽ ጋር ውዝግብ ቢጀምር ምን ጥቅም ያገኛል? ደግሞስ በዓባይ ጉዳይ በኢትዮጵያና በግብጽ ውዝግብ የሚያሸንፈው አሜሪካ መሆኑ ያጠራራል ወይ? አሜሪካ ሲያሸንፍ ግን ከኢትዮጵያና ከግብጽ አንዳቸው ይወድቃሉ፤ ወይም ይቆስላሉ፤ ሁለቱንም እኩል አያቅፋቸውም፤ ደርግ አሜሪካንን በማስቀየሙ በአለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ መሬትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያስከተለው መዘዝ እያሰቃየን መሆኑን ልንረሳው አይገባንም

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያና በግብጽ መሀከል ያለው ጉዳይ አህያ ላህያ ቢራገጥ ዓይነት አይመስለኝም።

 

 

 

 

 

 

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

31 Responses to ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ

 1. elsa says:

  አምላክ ረጅም ዕድሜ ከጤንነት ጋር ለእርሰዎ ይስጥልን፡፡

 2. gebrey abrha says:

  ፕሮፌሰር የግልጋሎት እድሜቻው ስለኣበቃ ሙዜም ቢገቡ ይሻላል እጂ የሃገርን ታሪክ እያቆሾሹ ብሄር ከብሄር እየለያዩ ሃገርን ማፍረስ ነው ዓላማቸው።

 3. Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ ከ ፕሮፌሰር መስፍን | ktamirat

 4. Siltan says:

  ተጨማሪ እድሜ ይስጥልን፤ ለፕሮፌሰር !

  ፕሮፌሰር “ብየ‐ነበር” ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታይ እውነታ ላለመቀበል የሚያደርጉት ሽሽት ማቆሚያው ሰማይ ሳይሆን አይቀርም። የህዳሴ ግድብ ሲጀመር “የሃሳቡ አመንጪዎች እኛ፣ የገንዘብ ምንጭ እኛ፣ ባለሙያዎች እኛ…” ተብሎ በኢትዮጵያውያን እንደሚሰራ በይፋ ሲነገር “የውስጥ ፖለቲካ ለማስቀየስ ካልሆነ አባይ አይገደብም” ብለው እየተማረሩ አላገጡ። በቅርቡ ደግሞ ግራ የገባው የግብጽ መንግስት ግድቡ ከተሰራ ኢትዮጵያን እንወጋለን ሲል ፕሮፌሰሩም ግብጽ ሃያል ሀገር እንደሆነች የሚገልጽ አሃዛዊ ሃተታ አቅርበው በባዶ ሜዳ ኢትዮጵያውያንን አቅመቢስ ጦረኛ አስመስለው ለእስላማዊቷ ግብጽ ጥብቅና ቆሙ። በዚህ ሲነቀፉም ከመታረም ይልቅ አብሮአደጉ ዘለፋቸውን አዥጎደጎዱ። አሁን ደግሞ ግድቡ እንዲሰራ የፈለገችው አሜሪካ ናት በማለት ምክኒያቱንም አባይን በመቆጣጠር ግብጽን ለመቆጣጠር ስለምትፈልግ ነው ሲሉ ውሉ ወደሳተ የሴራ ንድፈ ሃሳብ (Conspiracy Theory) ገብተው ተጠልለዋል።

  መቼም ሰውየው “ብየ‐ነበር” ማለት እንደማይታክታቸው ሁሉ ከእውነታ መሸሽም አልሰለቻቸውምና ነገ ደግሞ ግድቡ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ እንዲህ ሊሉ ይችላሉ፦ “እግዚአብሄር እኔን ማናደድ ስለፈለገ ግድቡ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ወያኔን ታሪክ ሰሪ አደረገው፤ አምላክ ለሱ ባያዳላ ወያኔማ ከየት አምጥቶ ይሰራው ነበር!”። ፕሮፌሰሩ ይህ ግድብ ተሰርቶ እንዲያዩ አምላክ ትንሽ እድሜ ቢያክላቸው ብንጸልይ ምን ይመስላችኋል?
  ከወልደብርሃን ስሁል

 5. Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ |

 6. ነቢዩ ሲራክ says:

  እንደኔ እንደኔ የፕሮፊሰር መዝፍን ትንታኔ አስደስቶኛል። በአጭሯ ማስታዎሻቸው የሰፊውን ጉዳይ አንኳር አንኳር ጉዳይ ዳስሰውታል ። እርግጥ ነው አሜሪካኖች ወንድማማች እስላሞች የግብጽን መራሔ መንግስት መንበር ከያዙ ወዲህ እና ዛሬ አሜሪካኖች በግብጽ አየር ስር አንደፈለጉት መሆን አይችሉም። ከትልቁ ሁስኒ ሙባረክ ጀምሮ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚዎች ብልጣብልጦቹ የጦር ጀኔራሎች ታንታዊ እና ሳሚ በቦታቸው የሉም! አናም በግብጽ በኩል የሃይል ሚዛኑ አስተማማኝ አይደለም። የስዊዝን መሿለኪያ፣ የፍልስጥኤም የትጥቅ ትግል እና ከአዲሱ የግብጽ አመራር ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ለአሜሪካኖች ራስ ምታት ነው። በዚህና በተዛማጅ ጉዳዮች ከእስራኤል ጋር ኩታ ገጠም የሆነችው የግብጽ ግንኙነት ጉዳይ በአሜሪካ በኩል እንደ ቀላል ጉዳየሰ የሚተው አይደለም ። የታጣን ቦታን ለማስተካከል በሉት ሃይል ሚዛኑን ለማስተካከል ደግሞ አሜሪካ ቀዳዳ መፈለጓ የግድ ነው ። ይህን አሳምሬ የማውቀው ሃቅ በመሆኑ የፕፊሰር መስፍን ትንተና ተስማምቶኛል። እንዲህ የፓለቲካውን አንድምታ አቀጣጫን በወግ በወጉ ላሳዩን አባት የአደባባይ ምሁር ምስጋናየ ወደር የለውም!
  ጀሮ ያለው ይስማ!
  ነቢዩ ሲራክ
  ከሳውዲ አረቢያ

 7. MUSSIE WUBSHET says:

  I AGREE WITH U

 8. miki says:

  እና ምን ይሁን? የሀገራችን ምሁራን የሚጎላችሁ መሰረታዊ ጉዳይ ነገሮችን በፈለጋችሁት አቅጣጫ መርታችሁ አመክኖይ ያለው ካስመሰላችሁ በኋላ ምንም ሳትሉ መቅረታችሁ ነው። ምንም የማትሉት ደግሞ የእኛ ጉዳይ አይደለም በማለት ሳይሆን ችግሩን ከመሰረቱ በጥልቀት ስለማትፈትሹትና ከራሳችሁ የፖለቲካ ፍላጎት አንጻር ስለምትቃኙት ነው። ከዛስ ጠብ የሚል ነገር የለም። የፕሮፌሰሩም ጽሁፍ ይሄው ነው።

 9. Andinet says:

  በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ የሚያራምዱትን የፖለቲካ አካሄድ ታሪክን መሰረት በማድረግ ግሩም የሆነ ትንታኔ አቅርበውልናል፡፡ በዚህም ታሪክ ተረት ብቻ እንዳልሆነ ይልቁንስ በደንብ ከተረዳነው የወደፊቱን ልንተነብይ እንደሚያስችለንና ልንማርበት እንደምንችል ያሳዩበት ጽሁፍ ነው፡፡
  በቀጣይ ጽሁፎ በተለይ በዓባይ ጉዳይ በኢትዮጵያና በግብጽ ውዝግብ ወደፊት ምን መልክ እነደሚኖረው በጥልቀት ቢዳስሱት እና የመፍትሄ ሃሳብ ቢያቀርቡበት የበለጠ አስተማሪ ይሆናል ብዬ አስባለሁ ፡፡
  ረጅም ዕድሜ ከጤንነት ጋር እመኝሎታለው፡፡

  • haq says:

   አንድነት እንደኔ እይታ ዙሪያውን የሚዞሩት መተንተን ጠፍቷቸው ሳይሆን ስላልፈለጉ ብቻ ነው! ይልቅ እኔ ሰሞኑን ያነበብኳቼውን አሪፍ ትንታኔዎች ላስነብብህ!In the 1970s, when the Arabs and the Tel Aviv Government were in a state of hostility, a man enveloped by a depressing anxiety over the future of the waters of the Nile named Boutros Boutros-Ghali was writing articles pointing to a possibility of a pact between Egypt and the Tel Aviv Government. Boutrous Boutros-Ghali was less concerned for the general Islamic Arab cause, for he was a “Christian” Copt living beneath an Islamic shadow, but in the heat of the hostility he saw an opportunity his country, Egypt, could exploit. He knew the Tel Aviv Government needed softened Arabs, which he figured was in Egypt’s power to forge; but he also knew Egypt could get handsome rewards from the Tel Aviv Government and the West in return, particularly the protection of the flow of the river Nile, which was the primary matter his articles were drafted for. His articles captured the attention of authorities in the pinnacle of Egypt’s government. Under the umbrella of the Ahram Center he was allowed to meet with personalities from the Tel Aviv Government and to hold symposiums[4] to assess the extent to which Tel Aviv would embrace Egypt’s desires in a deal. Through these meetings and symposiums Egypt’s leaders learned that they would be able to live without fear regarding the Nile if they made a pact with Tel Aviv and the West.

   Suddenly, in the midst of the Arab-Jewish tempest, Egypt’s leader Anwar Sadat sought to deal with the Tel Aviv Government while no compelling grounds for such action appeared to exist except one: the Nile. A new military government in Ethiopia was threatening to build dams and Egypt sought the help of the West to stop it. The Egyptian foreign minister, Isma’il Fahmi was pushed aside and Boutros Boutros-Ghali came on board and gave Anwar Sadat a company as acting foreign minister to his visit to Tel Aviv. Subsequently, Boutros Boutros-Ghali took part in the Camp David talks and in the “peace” treaties that followed. In the Camp David agreement Egypt garnered the backing of Western powers on its side to do all harm it could on Ethiopia. For over 30 years since, the unarticulated sacrificial lamb that is ethiopia was doomed. !ስለዚህም ግብፆች ከማንኛውም ነገር፣ ሌላው ቀርቶ ከሃይማኖታቸውም በላይ አገራቸውን ያስቀድማሉ” ይባላል፡፡ አገራቸው አገር የሆነችው ደግሞ በናይል ወንዝ አማካይነት ነው፡፡ ይህ አባባል እውነት ከሆነና ግብፆች ለናይል ሲሉ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ ከሆነ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ጦር ከመማዘዝ የቀለለ አንድ አማራጭ በእጃቸው አለ፡፡ እርሱም እ.አ.አ. በ1978 ከእስራኤል ጋር የተፈራረሙትን የካምፕ ዴቪድ ስምምነት (Camp David Accords) አረረ መረረ ሳይሉ በማክበር ከእስራኤል ጋር ያላቸው ወዳጅነት ፀንቶ እንዲኖር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህንን አያደርጉትም ማለት አይቻልም፡፡ ሲያደርጉት ደግሞ አባይን መደራደሪያ ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ የግብፁ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት የሲናይ በረሃን ከእስራኤል በማስመለስ በግብፅ ሕዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ሲል የአረብ አገራትን በሙሉ ጥሎና የፍልስጥኤምን ጥያቄም ችላ ብሎ የካምፕ ዴቪድ ስምምነትን እንደፈረመ ስናስብ፣ ግብጻውያን ለአባይ ውሃ ሲሉ እስከምን ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ መገመት አያዳግተንም፡፡ ግብጾች ይህንን ካደረጉ፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳረፍ አቅም ያለው የአሜሪካውያን ይሁዲዎች ማኅበር (AIPAC) እና ሌሎችም የጽዮናውያን ድጋፍ አሰባሳቢ ቡድኖች (The Zionist Lobby) ኢትዮጵያ የግብጽን ጥቅም የሚጎዳ አንዳችም ነገር እንዳትሠራ ታደርግ ዘንድ በአሜሪካ መንግሥት ላይ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ የምታካሂደው የኃይል ማመንጫ ግንባታ ፈተና ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡የካምፕ ዴቪድ ውል በሚባለው የተደረገው ስምምነት የግብጽ መንግሥት በአይሁድ መንግሥት ላይ፣ የአይሁድ መንግሥት ደግሞ በግብጽ መንግሥት ላይ ጦርነት እንዳይከፍቱ ነው ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት ከእስራኤል ጋር ሲደራደሩ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ጦርነት የምንገባው በውኃ ምክንያት ነው በማለት በግብጽ ከሰላሳ ዓመታት በላይ ሲገነባ የኖረው የጥፋት መሣሪያ ኢትዮጵያ ላይ እንዲውሉ ታስቦ መሆኑም ግልጽ ነው ።ኢትዮጵያ ሀገሬ! ህዝባችን! ኢትዮጵያ! እያልን የምንጮህ ሁሉ፤ የአባይ ጂኦ-ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ከእኛ አልፎ የሰሜንና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትንና እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ላይም ትልቅ ተፅእኖ እንዳለው ማስተዋል የመጀመሪያው ታላቅ መረዳት ነው። በመቀጠልም የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያጎላና ታላቅ ሁለገብ ጠቀሜታ የሚያመጣላት መሆኑን በመረዳት ሁለተኛው ታላቅ ግንዛቤ ነው። በመሆኑም የውስጥና የጋራ ችግራችንን በጋራ በመፍታት ለ አባይ ጉዳይ በህብረት ካልተነሳን በስተቀር፤ በግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ ደርሰን፤ እያሰብን የምንኖር ሰዎች ለመሆናችን ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን በርግጥ የሰብእና ጉድለት የሌለብን ሰዎች ለመሆናችን በሚገባ መመርመር አለበት ።ይኸውም ህዝባችንን ከሺ አመታት ድንቁርናና ርሀብ ከማውጣት ይልቅ ምናልባት የግል ስምና የፖለቲካ ዝና ወይም የግል ጥቅም በልጦብን፤ በታሪካችን እንደተለመደው እርስ በርስ መቆራቆዝ ስንጀምር ሌላው በእኛ ለመጠቀምና የእኛን ሀብት እየበላ ለመኖር የሚፈልግ ሁሉ የምንጨራረስበትን መሳሪያ ያቀብለናል። ስለሆነም “ከእኔ በላይ አዋቂና ለሀገር አሳቢ ለአሳር ነው” ወይም “ከእኛ ወዲያ ፉጨት አፍ ለማሞጥሞጥ ነው” ከሚባለው ሀገርኛ ጎጂ አባባል ነፃ በመውጣት የመቻቻልና የመደራደር ተስማምቶም ለመስራት የእውቀትን ክህሎት ብቻ ሳይሆን፤ በተግባር እንነሳና አባይን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በርካታ የልማት ስራዎችን እንስራ። “የእኔ መንገድ ብቻ ትክክል ነው” (my way is the high way) የሚለው ያረጀና ያፈጀ በግሎባላይዜሽን ዘመን የማይሰራ የግልና የቡድን አስተሳሰብ “ የጋራ ውሳኔያችን ትክክል ነው” በሚለው መተካት ያለበት አሁኑኑ ነው። ስለሆነም ከአባይ ግድብ ግንባታ በፊት “ሰብአዊ መብት ይከበር! ዲሞክራሲና ፍትህ ይገንባ !!! ” የምንልም ሰዎችም እንሁን፤ ወይሞ ደግሞ “ታላቁን ጠላት ድህነትን አስቀድመን እንዋጋ !!! ዲሞክራሲ እህል ከጠገብን በሁዋላ !!! ” የምንል ሁላችን፤ የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ያንድ ወገን (ግሩፕ) ወይም ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን፤ የሁላችንም የጋራ ጉዳይ ነውና፤ በአባይ ጉዳይ ማንም ማንንም እንዳያገልል ሁላችንም እንጠንቀቅ አጥርተንም እንመልከት አርቀንም ለትውልድ እናስብ ዘንድ ይገባል። taken from Nasrudin-Ousman and mulugeta zerfu and yosief werku articles

   • getachew says:

    I wish I could believe the writer of the article above. There is one basic misinformation to directed on porpose to divde us .Let us be ware of these people who are tring to extend the life of the brutal fascitic woyanes. I choose prof.mesfen’s analysis.It is like when europians brought civilzation you also learn to be what you do not want to be.Democracy gives us power. It librates our brain to think freely and invent civilization tailord to our needs.Repression should come to an end first then we will tame our rivers.

   • Andinet says:

    Good Analysis but hasty generalization!

 10. Addis says:

  እግዚአብሄር ይስጥልን፡፡

 11. haq says:

  እውነት በውነት ፕሮፌሰር ምናልባትም የኢሉሚናቲዎች ሴራ ነው ቢሉኝ አምንዎት ነበር… አንድ ወዳጅ አለኝ ሁሉን ነገር ኢሉምናቲ እያለ ልቤን ድክም የሚያረግ እውነት ግን የአባይ ግድብ በግብጽ ላይ የተደግ የusa ሴራ ነው? ፕሮፌሰር የሚሉት እውነት ከሆነ ግን …. ይቺ አመሪካ መውጊያዋ ምንድን ነው?እንድል እገደዳለህ ! አመሪካ ሆይ መውጊያሽ የታለ!ተብሎ እስኪቀለድባት ድረስ..እስከዚያውስ…. እስከዚያማ ራእ 13:4 አመሪካ ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያልን እንስገድለት!? እኔ ግን ፕሮፌሰር የሳቱ ይመስለኛል አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው። መዝ 74፥14 በተባለበት አገር ላይ አማሪካ …

 12. Good for Ethiopia says:

  Whatever one says, no one can deny this is the best time to build the dam. If we miss this chance we will regret it forever and live a life of blame and counter blame.

 13. Me says:

  Just so you have the latest information about what is going on in Ethiopia. This is a leaked recording of Dr. Berhanu Nega confirmed the financial and operational ties between the Eritrean government, Ginbot 7 and ESAT. Here is the link http://www.awrambatimes.com/?p=8639
  The audio contains 6:12 minutes long speech by Berhanu Nega – apparently a briefing to “Ginbot 7” officials about organizational matters.
  Ginbot7 is a political group aiming a violent regime-change and has been designated as terrorist by Addis Ababa and the regional inter-governmental body IGAD.
  In the audio, Berhanu Nega discloses that they had requested the funds for the next “tranche” to be released by submitting a budget proposal of half a million US dollar.
  Berhanu indicated the budget has been approved and described the approval process went “very smoothly and very positively”.
  It was handled by “the second-ranking official”, since the “chief guy (Pres. Isaias Afeworki?) was not available”. The official said there is need not give thanks because “we are doing it for our own interests”, according to Berhanu.
  It is not clear who the ultimate source of the money, though Egypt, Libya and Qatar has long been considered the primary patrons of the Asmara regime. However, the first two are believed to have aborted or downsized their role since 2011, while Qatar has recently improved ties with Ethiopia.
  The audio record of Berhanu’s speech, however, reveals the allocation of the budget.
  ESAT
  Berhanu Nega indicates, in the audio, that 200,000 dollars is earmarked for “ESAT activities”.
  Though it is widely believed that ESAT (EthSat.com) is owned by Ginbot 7, it journalists and some western rights-groups maintain it is an independent media without directly addressing the claims made by former confidants and allies of Berhanu Nega.
  The US State Dep. Human Rights report of 2011 had described EAST as: “Ethiopian Satellite Television, based in Amsterdam and supported by the Ginbot 7 group, which espouses violent overthrow of the government, reported periodic jamming of its service in Ethiopia, beginning in May, at the start of broadcasting”.
  There are claims that the alleged jamming caused dispute between the Egypt-based Nile-Sat and the Ethiopian government. There have been reports that Nile-Sat denied service to Addis Ababa, though there is no report of Egyptian officials’ involvement in the matter.
  ESAT’s programs openly promote right-wing insurgent groups, especially Ginbot 7, and shy away from news unfavorable to Asmara, such as the mutiny against Isaias Afeworki last January.
  Transformer
  Berhanu’s speech, in the leaked audio, indicated progress with regard to a certain previous plan made with the Ministry of Information of Eritrea. Their agreement “to build” a “powerful transformer with all its accessories” has been delayed because the equipment “very expensive”, Berhanu Nega explained.
  However, now, Berhanu said, the equipment are acquired without disclosing how and indicated that will be “completely directed towards Ethiopia”.
  While “the transformer” appears to be for broadcasting purposes, it is not clear whether it is intended for ESAT transmissions or not.
  “Military and Intelligence works”
  Berhanu Nega claimed 200,000 US dollars will be spent on “military and intelligence works”, which appears to a euphemism for terror acts as well as its newly formed “Ginbot 7 popular force” stationed in Eritrea.
  Berhanu Nega also disclosed that a group terrorists are on the move.
  He claimed “six men” has arrived from South Africa, while “three men” from Kenya and South Sudan are expected soon. Once the later three arrive, they will include “men from inside there” and “will form a ‘ganta’ (a military unit)”, then “we will proceed to the next step”.
  The destination is not disclosed in the speech, though it appears to be Eritrea or Ethiopia.
  Berhanu’s speech indicates that Ginbot 7′s effort to establish military presence in Eritrea has faced resistance from other insurgent groups. He said that “as expected EPPF and the so-called Amhara’s organization have been unwilling to recognize Ginbot 7′s popular force as expected”.
  However, “the Eritrean official who handles the matter” decided in favor of Ginbot 7, since the latter “is not part of the agreement….those who want can join it”. It seems there is a sort of cartel set by the existing insurgencies with regard to members recruitment.
  “Peaceful struggle” and “Diplomacy works”
  The rest 100,000 US dollars will be used to finance “peaceful struggle being conducted” in Ethiopia and for diplomacy works, according to Berhanu’s speech on the leaked audio.
  It is not clear how Berhanu is conducting the “peaceful struggle” and whether he finances legal political parties and press outlets operating in Addis Ababa.
  Berhanu reveals that they have agreed with the Eritrean officials “to coordinate” in the “diplomacy works” and has already started “concerted effort” in US and Europe.
  He appeared less hopeful about US State Department saying “there is not much we can do there…but we can work on the Congress and through lobby groups”.
  He disclosed the strategy with regard to the Congress and US think-thanks will be creating “serious doubt and question” about the Ethiopian government. This will succeed if “we work effectively” and “comparing notes”, Berhanu added.

  • Andinet says:

   Just for your information, here is an Article by Abe Tokichaw on the issue:

   by Abe Tokichaw
   ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስራቸውን እየሰሩ ነው ማለት ነው!

   ሰሞኑን ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዘመድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙ የሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ገንዘብ ከየት እንደተገኘ እርስ በርሳቸው ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ አንዳቸው ከኤርትራ ነው ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ከግብፅ ነው ይላሉ፡፡ በደንብ ጆሮ ጣል ብናደርግ ከኢህአዴግ መንግስት ነው የሚልም አይጠፋም፡፡

   ወዳጆቻችን ያጋሩን ድምፅ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሆነ ቦታ የተገኘውን ብር፤ ለእንትን ይሄን ያህል፣ ለእንትና ይሄን ያህል እያሉ ሲናገሩ ያስደምጣል፡፡ በዚህ ላይ ያስደነቀኝን ልናገር እና እመለሳለሁ ቆይ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ፡፡
   ዶክተሩ የሆነውን ብር እዛው ለመከላከያ እና ደህንነቱ የተበጀተ ነው፤ ሲሉ ሰማናቸው፡፡ ይሄኔ በተለይ እንደኔ በኢህአዴግዬ ፍቅር የተለከፈ ሰው ክው!!! ማለቱ አይቀርም፡፡ ደህነነት እና መከላከያችን ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ውጪ በግንቦት 7 ደግሞ ሌላ በጀት አለው ማለት ነው፡፡ ይቺን ነው መፍራት፤ ዶክተሩ ስራቸውን ቀጥ ለጥ አድርገው እየሰሩ ነው ማለት ነው፡፡

   ታድያ ለዚህ ነዋ የኢህአዴግዬ ገመናዋ ሁሉ ቀድሞ አደባባይ የሚሰጣው!!! እኔ ልሰጣ … ልበል ወይስ አልበል! (በቅንፍም ይቅርብኝ እነ እንትና ሳይሉ እኔ ቀድሜ ልሰጣ… ብል እነሱን ማሳጣት ሆንብኛል!) ከቅንፍ ስንወጣም ለኢሳትም የሆነ ብር ይሰጣል ሲሉ ዶክተሩ መናገራቸውን አዳመጥኩ፡፡ በእውነት ዶክተርዬ የተባረኩ ኖት፡፡ … እንዴ… በአሁኑ ጊዜ ማን እንደዚህ ያደርጋል… የምር እኮ ኢሳትን ሁሉም መርዳት አለበት፡፡ ግንቦት 7 ከረዳው በጣም ጥሩ ጅምር ነው፡፡ እንኳን ሌላ ቀርቶ ግንቦት 20 ም ራሷ ኢሳትን መርዳት አለባት፡፡ እንዴ ኢቲቪ የማይሰራውን በሙሉ የሚሰራው ኢሳት አይደለ እንዴ…! ታድያ እንዲህ እንዲተጋገዙ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ ምን ችግር አለበት!
   ወደ ዋናው መስመር ስመለስ ወዳጆቻችን “ፈልፍለው” ይፋ ባደረጉት መረጃ ዶክተሩ ለካስ አልተኙም ብለናል፡፡ እና ይበርቱ ልንላቸው ይገባል፡፡

   ገንዘቡ ከግብጽ ነው፤

   ግብፅ የምር ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ተጃጅላለች ማለት ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ኢህአዴግ እንኳ ያንን ሁላ አድርጋለት አልተመለሰላትም፡፡ በእውኑ ሌሎቹማ ከኢህአዴግ የበለጠ ለሀገራቸው ተቆርቋሪ አይደሉምን…!

   ገንዘቡ ከኤርትራ ነው፤

   ወይ…. ኤርትራ….!!! አሁን ማን ይሙት ኤርትራዬ ከራሷ አልፋ ለሌላ ሰው ይሄንን ያክል ብር መስጠት ትችላለች…! ይሄንን ሃሳብ የሰነዘሩ ሰዎች በእርግጠኝነት ኤርትራዊያን ናቸው፡፡ አላማውም የኤርትራም መልካም ገፅታ ለመገንባት ሳይሆን አይቀርም ብለን እኛ ጠርጣሮቹ እንጠረጥራለን!

   የትም ፍጪው ኢህአዴግን አስወጪው፤

   ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ መስርተው ሁለገብ በሆነ ዘዴ ኢህአዴግን ወግድ እለዋለሁ ብለውናል፡፡ ግንቦት 7 ይህ ከሆነለት የዘመናት ብሶት የወለዳቸው ሁሉ ተሰባሰበው ዋንጫ እንደበላ ሰው “የእርግብ አሞራ” እያሉ የሚጨፍሩለት ደስታ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ታድያ ለዚህ አላማ ገንዘብ ከየትስ ቢያመጡ እኛ ምን አገባን…!?

   • Me says:

    Andinet,
    The main problem here isn’t the fact that he is willing to work with the most ardent and historical enemy of our motherland Ethiopia, since he explicitly said he will work with the devil to get hold of power so many times in the past. As Prof. Mesfin said our history is full of Bandas so it doesn’t really surprise me. The real issue here is,
    1) It clearly shows that his organisation is evidently infiltrated, so no wonder why he has been shooting himself in the foot for the last five years. This also means trust is nearly impossible to establish and only the ‘fools and idiots’ will work for such a man as Susan rise put it eloquently.
    2) He has clearly been misinforming and lying to the public claiming ESAT is independent while it is being funded by the Muslim brotherhood. So instead of ESAT being the ‘eye and ear of the Ethiopian people’, it is now the ‘eye and ear of the Muslim brotherhood and Shabia’.
    3) He has been advocating for civil war in Ethiopia while he and his family live in comfort and luxury here in the US. It stinks a tiny bit of duplicity and hypocrisy to ask those in Ethiopia to do something you clearly isn’t willing to do. He sends his kids to private schools while he wants to send other people kids to war so he can get the power he desperately craves.
    4) Above all he claimed that he is funding and using the peaceful opposition in Ethiopia, which is now going to make their life difficult. This clearly is going to be the lasting implication of the secret tape’s revelation.

    In conclusion, the political landscape in Ethiopia has been brutalised and tortured by a generation of egotistical, know it all, deceivers, fraudsters and cheats in all camps. So it is time for these none achiever generation to evacuate the political scene with their poison chalets, to the young generation. The young generation should also be forceful in its conviction to force the dead weight generation out of Ethiopian politics as their achievement is something to be embarrassed about. From overseeing the greatest loss of human life throughout the history of human beings due to famine, to ethnic polarisation and deep seated hatred etc… These are the legacy the dead generation is passing to the young generation. We should say, we are ashamed and embarrassed of you and now it is our turn to overturn and reverse your shameful legacy so we can pass, a prosperous, democratic and just Ethiopia to our kids.

    God bless Ethiopia!

   • what is happening to us? says:

    Wesha Bebelaber yechohal Ayder yemibalew. hahahah!

   • History says:

    Andinet,
    Unfortunately our history is full of Bandas who sold their country for the highest bidder, in this case the lowest bidder. Come On, surely Ethiopia is worth more than $500,000, I think Egypt got a bargain. Birhanu, even a 5 year old can do better.

    By the way, that is why our fathers sang ‘Ethiopia hagere Mogn nesh telala, yemoteleshe kerto yegedeleshe Bela’, it means, On motherland Ethiopia must be a fool as those who killed her are benefiting while those who died for her lost out.

    Thank God we now know who is selling out and how is a patriot.

  • Andinet says:

   Dear Me and History,
   I think you are trying to divert the discussion issue to D.r Birhanu because you have no logical justification to argue the professor’s Article. I love to say more about D.r Birhanu, but just for the sake of not diverting our discussion from the Professor’s point; let us focus our discussion on the relation between the Abay dam and the US policy.
   As hash said in his comment “It is not a coincident that the question of Abay Niel came just after the crises in Egypt. Abayin megedeb kalebin egna sinfelgina akmachin sifekd enji manim silken mehon yalebetim!! ”.

 14. tassew says:

  የፕሮፌሰሩ ፅሁፍ አልገባኝም…. ማስፈራራቴ አይደለም ይላሉ…… ጦር ህይልን ያነፃፅራሉ…….. ኢትዮጵያ ብቻዋን ናት ይላሉ ተሳሳቱ ብቻዋን አይደለችም አግዚአብሄር አለላት፡፡ ድሮስ ግን ማን ነበራት….. እና አያሥፈራሩን፡፡ እጅና እግራችችንን አጣምረን ድህነትን የሙጥኝ እንበል? አልፈራንም ለወደፊቱም አንፈራም ትእቢትም አይደለም.

 15. geezonline says:

  ቀናኹብዎ! [ታዲያ “ቅንዑ ለእንተ ተዐቢ ጸጋ” ባለው መንገድ ነው።] በእውነቱ በርስዎ ያልተቀና በማን ይቀናል? ያስተያየትዎ ስፋት፤ የምርምርዎ ጥልቀት!

  ብዙዎች ምድጃ ከበው የመንደር ወሬ ሲያወሩ፤ ርስዎ እንዲህ በአእምሮ ኅዋ ከጽንፍ ጽንፍ እየተዘዋወሩ በያደባባዩ የሚዶለተውን በማየት፤ ያዩትንም፦ ልቡ በስተግራው የኾነ ጠማማ ኹላ ካልኾነ በቀር፤ ልቡ በቀኙ የኾነ ማናቸውም ብልኅ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው በሚችል ግልጽ ቋንቋ ሲያቀርቡት እንዴት አያስደሳ?! [ስለልብ አግጣጫ የጠቆምኹት ባዮሎጂውንም ኾነ የቀኝ/ግራ ፖለቲካውን ሳይኾን መጽሐፈ መክብብን መሠረት አድርጌ ነው፦ “ልቡ ለጠቢብ ውስተ የማኑ፤ ልቡ ለአብድ ውስተ ጸጋሙ” የሚለውን]

  በበኩሌ “ኦ ንስር ዘእሙር በብርሃነ-አዕይንቲከ” እንዲሉ፤ ዐይኑ ጽሩይ በመኾኑ ሽቅብ ወጥቶ ረቦ ሳለ ቊልቊል በተመለከተ ጊዜ የሰናፍጭ ቅንጣት ታኽል ሥጋ ብትኾን እንደማትሰወርበት ንስር፤ [ያውም በዚህ ክፉ ዘመን] የኀላፍያትም ኾነ የመጻእያት ምስጢር ካልተሰወረባቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ መኾነዎን ከተረዳኍ ቆይቻለኍ። ዕድሜ ይስጥልን!

 16. Gebru says:

  what a non-sense. You believe that the US has a remote control to every thought of every one, all the time. It is unbelievable that the good professor can’t measure the pros and cons of a big project like Abay Dam in terms of Ethiopian interests.
  It is sad

 17. hash says:

  It is not a coincident that the question of Abay Niel came just after the crises in Egypt. Abayin megedeb kalebin egna sinfelgina akmachin sifekd enji manim silken mehon yalebetim!!

 18. Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ | yabedew / ያ - በደው

 19. Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ | Time for change

 20. ASHENAFI says:

  GOOD I FOLOW IT

 21. Amen says:

  እንደተለመደው በጣም ጥሩ ግንዛቤ የሚሰጥ ትንታኔ ነው። ታዲያ ከዚህ ዓለማቀፍ ሁኔታ አትራፊ ሆኖ ለመውጣት ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

 22. Abraham says:

  ፕሮፌሰር፣ አምላክ ረጅም ዕድሜ ከጤንነት ጋር ለእርሰዎ ይስጥልን፡፡

Comments are closed.