አይ አበሻ! አበሻና ልመና፤ ሁለት

መስፍን ወልደ ማርያም

ኅዳር 2006

ልመና ሳይሰርቁና ሳይቀሙ የሌላውን ሰው ንብረት ፈልቅቆ ለመውሰድ የተፈጠረ ዘዴ ነው፤አንዳንዴ ትልቅ ነገርን ሲመኙ ትንሽ ነገር መስጠት የልመናውን በር መክፈቻ ይሆናል፤ እነዚህ የልመና ስጦታዎች ስሞች አሉአቸው፤ እጅ መንሻ፣ ወይም መታያ ይባላሉ፤ የጌቶችን ፊት ለማየት፣ ወይም ጌቶችን እጅ ለመንሣት፣ ሲፈቀድም እግር ለመሳም የሚቀርብ ስጦታ ነው፤ ያለው ሰንጋ ወይም ሙክት ይሰጣል፤ ሴቶች ፈትል ወይም ስፌት ይሰጣሉ፤ ይህ እንግዲህ ትንሽ ሰጥቶ ብዙ የመቀበያ የልመና ዘዴ ነው፤ በዘመናችን በተለይም በከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጉቦ፣ ሙስና፣ ንቅዘት የሚባሉ ክፉ ስሞች ለክፉ ተግባር ተሰጥተዋል፤ ልመናን ከዚህ ርካሽ፣ መናኛና ወራዳ ተግባር ጋር እንዳናዛምደው፤ ልመና የተራቀቀ ማኅበራዊ ዝቅጠት ነው፤ ሙስና የወራዳና የስግብግብ ግለሰቦች ጸረ-ሕዝብ ሌብነት ነው፤ ልመና ማኅበረሰቡ ሥራን ችላ ብሎ የሚሰማራበት ነው፤ ሙስና ጥቂቶች ሰዎች የማኅበረሰቡን አጥንት እየጋጡ በዱለትና በቁንጣን ነፍሳቸውን፣ አእምሮአቸውን፣ በመጨረሻም አካላቸውን የሚያጡበት ሥልጣንና ሀብትን አምላካቸው ያደረጉ ሰዎች የማይጠግብ ወይም የማይሞላ የወንጀል ተግባር ነው፡፡

ማማለድም አለ፤ በቀጥታ መለመን የሚፈራ ወይም የሚያፍር ሲሆን የሚለምንለትን የሚለምንበት ዘዴ ነው፤ ስለዚህም አማላጅ ማለት አስለማኝ ወይም የለማኝ ወኪል ማለት ይሆናል፡፡

ልመና በሰው ላይ ልዩ ጠባይን ያሳድራል፤ አጥንት እንደሌለው ነገር ልፍስፍስ፣ ስብርብር፣ እያሉ መቅለስለስና መለማመጥ የልመና ጥበቦች ናቸው፤ በነዚህ ጥበቦች ያልሠለጠነ ልመናው ሊሳካለት አይችልም፡፡

አበሻ ከልመና ውጭ በሰማይም ሆነ በመሬት የሚያገኘው ምንም ነገር የለም፤ አስተዳደር በልመና ነው፣ ገበያም አንኳን በልመና ነው፤ የሎተሪ ቲኬት የሚሸጡትን ልብ ብላችሁ አስተውሉአቸው፤ ሴት በልመና ነው፤ በእኔ ዕድሜ አበሻ ሆኖ የማይለምን ንጉሥ፣ ፕሬዚደንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትር፣ ሹም አላየሁም፤ ብዙ ጊዜ በተዋረድ ያለውን ለማኝነታቸውን አናስተውለውም፤ ተራው ሠራተኛ የቀጥታ አለቃው ለማኝ ነው፤ ቀጥታ አለቃው ደግሞ የመምሪያ ኃላፊው ለማኝ ነው፤ የመምሪያ ኃላፊው ለዲሬክተሩ፣ ዲሬክተሩ ለሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከበላዩ ላለው ለማኝ እየሆነ በመሰላሉ ላይ ይንጠለጠላል፤ እንዳየነው ልመናቸውን የሚሰማቸው ሲጠፋ ከመሰላሉ ይወድቃሉ፡፡

በታላላቆቹ ለማኞችና ጭርንቁስ ለብሰው በየመንገዱ በሚታዩት ለማኞች መሀከል ያለው ልዩነት አፍአዊ ብቻ ነው፤ ታላላቆቹ ለማኞች የሚለምኑት በሕዝብ ስም ነው፤ ትንንሾቹ ለማኞች የሚለምኑት ለየራሳቸው ነው፤ ትልልቆቹ ለማኞች የሚለምኑት በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በዱባይ፣ በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ … ፎቅ ቤቶች ለመሥራትና ምርጥ መኪናዎችን ለመግዛት ነው፤ ተራ ለማኞቹ ግን የዕለት እንጀራቸውን ብቻ የሚሹ ናቸው፤ ስለዚህም የታላላቆቹ የልመና ከረጢት ሰፊና የማይሞላ ከመሆኑ ሌላ አንድ ሰው የሚሸከመው አይደለም፤ ደሀው ለማኝ ከዕለት ጉርሱ በላይ መሸከም አይችልም፡፡

ልብ ብሎ ላስተዋለ ከመንግሥት ጀምሮ ወደታች እስከደሀው ድረስ ለተመለከተ የማይለምን አበሻ የት ያገኛል? መንግሥት የሚባለው ድርጅት በልመና እንደሚኖር የታወቀ ነው፤ የናጠጠው የአበሻ ሀብታም ለማኝ መሆኑን ብዙዎቻችን የምናውቅ አይመስለኝም፤ ሀብታሙም አበሻ የለየለት ለማኝ ነው! ለመሆኑ ስታስቡት በለማኞች አገር ሳይለምኑ ሀብታም ለመሆን እንዴት ይቻላል? አንድ ቀን በጠዋት ተነሥቼ የኤንሪኮ ቡና ቤት እስቲከፈት በእግሬ ስዘዋወር አንድ ሰው ከውስጥ ነጠላ ለብሶ፣ ካፖርት ደርቦ ባርኔጣ አድርጎ ከታክሲ ሲወርድ አይቼው የት እንደማውቀው ሳንሰላስል ትንሽ ቆይቶ ጭርንቁስ ለብሶ ከዘራውን እየተመረኮዘ ብቅ አለ! ማን እንደሆነ አወቅሁት!

እንደአበሻ ሀብታም ለማኝ አለ እንዴ! ከባንክ ብድር ለማግኘት፣ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት፣ ካስወጣ በኋላ ግብር ለማስገመት፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት፣ ግብር ለመክፈል ለምኖና እጅ ስሞ ነው፤ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የአበሻ መሥሪያ ቤቶች ሁሉ በአበሻ ላይ ልመናን የዘለዓለም ባህል አድርጎ ለመጫን በተካኑ ሰዎች የሚመሩ ናቸው፤ መንግሥት የሚባለውም ሆነ ሀብታሙ፣ ደሀውም ሆነ ተማሪው የሚለምኑት ቸግሮአቸው ይመስላችኋል? አስቡበት! ግን አንድ ነገር አትርሱ፤ በአበሻ የልመና ሥርዓት የሚለምን ሁሉ ያስለምናል፤ አበሻ የሚወዳት አዙሪት!ሲለምን ያጣውን ክብር ሲያስለምን መልሶ የሚያገኘው ይመስለዋል፤ አይ አበሻ!

አበሻ ልመናን ወደተራቀቀ ጥበብ አድርሶታል፤ በግጥም፣ በጮሌ አፍ፣ ድምጽን በማቅጠን፣ አንገትን በማቅለስለስና አጥንት የሌለው በመምሰል፣ ‹አግኝቶ ከማጣት ያድናችሁ፤ … አዱኛ ጠፊ ነው፣ መልክ ረጋፊ ነው፤ ዓለም አላፊ ነው፤ ቀኑ አይጨልምባችሁ፤ …፤› እያለ ሲለምን የሰውን ልብ ለማራራት ብቻ አይደለም፤ ስውር ማስፈራራትም አለበት፤ የድሬ ዳዋ ለማኞች ትንሽ ለየት ይላሉ፤ አንዱ ጠጋ አለኝና ‹አንድ መቶ ብር ስጠኝ!› አለኝ!

‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል›፤ የተባለውን አበሻ የተገነዘበው ‹ለምኑ ታገኛላችሁ፤› በሚል ትርጉም ነው፤ ማንኳኳት ትንሽ ጉልበትም፣ ትንሽ ወኔም ያስፈልገዋል፤ አበሻ ጎመን በጤና ብሎ ጉልበቱንም፣ ወኔውንም የሚቆጥብለትን ልመና ይመርጣል፤ ያላቸው ቢሰጡ ሰጡ፤ ባይሰጡ የሚጎዱት እነሱ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት አይገቡ!

Advertisements
This entry was posted in አይ አበሻ!, አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

7 Responses to አይ አበሻ! አበሻና ልመና፤ ሁለት

 1. Jote says:

  Prof: I’m glad you brought this issue to the open for public discussion. I agree with your thesis. Some people blame the government. Yes, we know that most (if not all) Ethiopian government higher officials are corrupt, narrow minded, and incompetent. But we also failed as a society and developed culture of begging. As you said, in one way or another, most of us became beggars–we beg ferenjii, arab, cadres, “amlak”, habtam etc. Some people might be offended with your writing. And they have every right to refute your view and debate in a civilised manner. In the name of culture and “Ethiopiawenet”, some might still went to continue foll themselves. I take off my hat for being couregeous and bring this disease, limena, into the open. Jotee

 2. walelign5 says:

  ዉስጤን እንድፈትሽ ስለረዱኝ ፕሮፌሰርን (ዎይም በለው! ባማርኛ እንደጠራቸው ሊ/ጠበብት መስፍን ወ/ማሪያምን) ላመሰግናቸው እዎዳለሁ። በጽሁፉ ጭብጥ ላይ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ ነገር ግን በጽሁፉ ዉስጥ ሃበሻ እየተባለ የተጠቀሰዉ ሙሉ በሙሉ ሃበሻ (የሃበሻ ዘር) በሃበሻነቱ የልመና አባዜ አለበት ለማለት ስለሚመስል፤ ይህ ደግሞ በንደዚህ አይነት ጠንካራ ሂስ ሲታጀብ ሃበሻነትን እስከመጥላት ሊያደርስ ስለሚችል ሃበሻ የሚለው ቃል “ይህ ትውልድ እና ልመና” ዎይም በሌላ ቃል ተተክቶ ቢለዝብ ደስ ይለኛል።

 3. በለው! says:

  “በልመና ፈረስ እየተጋለቡ…ጋላቢውን ሳይነኩ…ተቺውን ልጓም ያዝ ማለት! ”አይ መሬት ያለ ሰው!”
  የመፃፍ ችሎታ ያለው አንብቦ ከመረዳትም ችሎታ ይለያል ?**አበሻና ልመና!
  -አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ መብላት ክብር ነው፤
  -ቄሶቹ ምንም ይስበኩ በተግባር እንደሚታየው ጽድቅ የሚገኘው በልመና ነው እንጂ በሥራ አይደለም፤ ሥራኮ ለአበሻ ከእርግማን የመጣ ነው፤ አበሻ አልተረገመ፤ ታዲያ ለምን ብሎ ይሥራ! አሁን እንደሚሰማውና እንደሚመስለኝ አገዛዙም እንደተቀበለው የቻይና ሰዎችም እንደመሰከሩለት ከሥራ ጋር ጠብ አለው፤ ደግሞስ ለምን ይሥራ! ለአንድ እንጀራ?
  -ደግ ሰዎች መጽውተው እንዲጸድቁ በግድ ለማኞች ያስፈልጋሉ፤ ለመጽደቅም መለመን ያስፈልጋል፤ ጸሎት ልመና መሆኑን አትርሱ፤ (የዕለት አንጀራችንን ስጠን ለዛሬ! እነኳን ቀርቶ (አባቱ እናቱ እስቲ ለጉርሻ የሚሆን!)ይላሉ።
  ********************************************
  **ድሃ ሊኖር ሀብታም ያስፈልጋልና ሀብታሞች ልመና ዓለም አቀፋዊ(ግሎባል)(ግሎባሌኢዜሽን)በሊ/ጠበብት መስፍን ወልደማርያም ቋንቋ( ሙሉዓለም)በኢትዮጵያ ሀብታም ኢንቨስተርና ካድሬ ሆድ-አደር የምሁር ትርጓሜ (ዓለም አንድ መንደር ሆነች እንደሚሉት!)ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን አሜሪካም አውሮፓም ለማኝ አለ ለማለት ነው።
  -ብልጦቹ እግዚአብሔርን የሚለምኑት ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት ነው፤ አንድ ቀን ተነሥተው እግዚአብሔር ሥልጣን፣ ሀብትና ጉልበት እንደሰጣቸው ያውጃሉ፤ አውጀውም በሕዝብ ራስ ላይ ይወጣሉ፤ በራሱ ላይ ወጥተውም ይጨፍራሉ፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው መለየት ይሳናቸዋል፤ ሰውን ከመሬቱ፣ መሬቱን ከሰው ያጣላሉ፤
  ********************************
  ደካሞቹ ለማኞች ፈጣሪያቸው ይወቅሳሉ፡ያለቅሳሉ፣ ይጮሃሉ፣አቅም ሲያጡ እራሳቸውን ያጠፋሉ ከሀገር ይጠፋሉ!
  እግዚአብሔር ለእናንተ ብቻ እንዴት ሰጣችሁ? እግዚአብሔር እኛን ለምን ነፈገን? – ሲሉም ያጉረመርማሉ፣ብረቱዎቹ ለማኖችም እየደበደቡና እያቃጠሉ፣ እየገረፉና እያራቆቱ በዝምታ እንዲገዙ ያደርጓቸዋል፤
  *********************
  ” ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” አለ ለምን? ቢለው “ሲዘል ይሰበራል ብዬ…እነኛ ብልጥና ብርቱ ለማኞች እግዚአብሔር እየቆጠረ የማይመዘግብ ይመስላቸዋል፤ የጠጠረ ጉልበታቸው ዓይኖቻቸውን አውሮ፣ ኅሊናቸውን አፍኖ እግዚአብሔር በዕዳ እንደሚይዛቸውና በጥጋባቸው ያደሉትን መከራና ስቃይ፣ የወረደውን እንባና ደም ከነወለዱ እንደሚያስከፍላቸው መገንዘብ ያቅታቸዋል። ይባሱንም አድር-ባይ፣ ሆድ-አደር፣ካድሬ፣ዲያስፖራ፣ኢንቨስትር፣ ፭በ፩ የሚታቀፉና የሚቀፈቀፉ… በተዋረድ የለማኞችን ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ሕዝብ ሁሉ ከነዚህ የለማኞች ሠራዊት በአንዱ ውስጥ ለመግባት በፉክክር ይተላለቃል፤ ሠራዊቱ ውስጥ በመግባት የሚገኘው ጉርሻ ልጆቻቸውን እንኳን ከረሀብ የማያድን መሆኑን ሳይገነዘቡ መብታቸውን እያስረገጡ የሌሎችን መብት ለመርገጥ መሣሪያ ይሆናሉ፤ እነዚህ እንግዲህ ልመናን በማኅበረሰቡ ውስጥ ተክለው እየኮተኮቱ የሚያስፋፉት ናቸው፤ ልመናን ባህል የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው፤ ልመናን ታሪካችን ያደረጉት እነዚህና ከነሱ የቀደሙት ገዢዎቻችን ናቸው።
  ******************
  “በእኛ ባህል የራበውን በማብላት ጽድቅ ይገኛል፤ ስለዚህም ለምኖ መብላት ይቻላል፤!አዎን! ሲወጡ ሲወርዱ የምናያቸው መንግስት መሳይ ቡድኖች ትውልዱን አድናቂ ለማኝ አድርገው ይኖራሉ…ሞተውም በባዶ ሳጥን ላይ ለሀጭና ንፍጥ ያዝረከርካሉ፣ከሟች ሚስት በበለጠ የራዕይ ወራሽ ሆነው በአደባባይ ይንፈቀፈቃሉ፣ ባነር ወጥረው በጥቁር ልብስና ጥቁር መነጽር ተቆራፍደው፣ ድንጋይ ጭነው አፈር አልብሰው ታጋይ አይሞትም! ሲሉ ለማኞቻቸውን ያበረታታሉ!።ስለዚህ የተረገሙት ሲሠሩ ያልተረገሙ የሚመስላቸው ይለምኑ፤ ለሌላው ዓለም ልመና የችግር ምልክት ነው፤ ለአበሻ ግን ልመና የጽድቅ ምልክት ነው፤(መብራት ውሃ በልመና፣ ምግብና መኖሪያ ቤትና ሥራ በልመና፣መንቀሳቀስና መዘወዘወር መሰብሰብ በማሳወቅና በልምና በማስፈቀድ፣ለሀብት ማፍራትና ሞቶ ለመቀበር በልምና ነው።አራት ነጥብ።
  -የጨዋ ልጅ፣ ማለት በልመና በሰዎች ላይ ሥልጣንን ከአግዚአብሔር አግኝቻለሁ ብሎ የሚያምን፣ አይሠራም፤ ቀን ቢጥለውም የጨዋ ልጅ በእጁ ሠርቶ ከሚበላ ለምኖ ቢበላ ይሻለዋል፤ ሆድ የተፈጥሮ ነው፤ ረሀብም የዕለት ከዕለት የተፈጥሮ ግዳጅ ነው፤ ስለዚህም ለአበሻ የተፈጥሮን ሆድና የተፈጥሮን ረሀብ በልመና መወጣት የተፈጥሮን ሥርዓት መከተል መስሎ ይታየዋል። የፊውዳሉ (የእጅ መንሻ)፣የደርግ (ጉቦ)፣ የህወአትሻቢያ/ኢህአዴግ/ወያኔ (ሙስና) እንደሆነ ሁሉ በተለያዩ ሥርዓትና አደረጃጀት ልመናም ይዘምናል….ቀፈፋ(ቀፋይ)፣ቀላዋጭ(ገበታ አስደንጋጭ)፣እርጥባን፣ ደጅ መጥናት፣ በአጭሩ ኑሮ ማለት ልመና ነው፤ ልመና ማለት ኑሮ ነው። ይህ በቧገታ የተቋቋመ ቀለበትና አሳላጭ ያለው እድገት ምን ያህል ለማኝን እንዳከበረ ባይታወቅም፤ የአፍሪካን ድረሻ ፳፭ከመቶ ድራጎት እቦጨቁ የትውልድ ትውልድ ከፍሎ በመይጨርሰው ብድር ተውጦ፣ ፴፭ ከመቶ ዕድሜው ከማምረት መመገብ የሚጠብቅ የህዝብ ቁጥር ይዘን፣ መሥራት ከቻለው ፵፭ከመቶ ሥራ-አጥ በሆነበት፣ ደም ተፍቶ እየሰራ የኑሮና የመኖር ምንነት ግራ የጋባው ሕዝብ፣ሲመሽ የነገን እንጀራ፣ ሲነጋ የማታ እንጀራውን የሚለምነውን ምን እናድርገው!? ሳይሰሩ በልመና የተሳካላቸውም ልቦና ይኑራቸው ሠርቶም የሚለምነውንም ያስቡ፣ የሥራ ክቡርነትን በልመና ክቡርነት ለውጦ እራሱን የማያነቃና አስለማኝን እንቢኝ የማይል ትውልድ መኖር የለበትም!የአዋጁን በጆሮ አትስደቡን ብሎ ከመለመን አንሰደብም ብሎ አስለማኝን ልጓሙን መያዝ ይሻላል በለው!
  በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ!(ለአቶ ዳኛቸው ቢያድግልኝ ትችት ከሰጠሁት አስተያየት የተወሰደ)

 4. Muleta says:

  Shame on you. Shame on both the Father and daughter. Both of you are educated without paying a single penny. Ethiopia paid it for you. Ethiopians (Habeshas ) paid it for you .

  • SABA says:

   Fiyel wediya kezemzem wedi, endit endit nwe metiregiwe ? kezi beft Professor yawetute etem ale erisu ” YASTESASEB HEGEN KALTEBIKEN MEGIBABAT ANCHILEM ” sileze ahun anchi hegun tebeke!. Betirefe Enem biteshufu azegnalwe Professor em yazenu yemesilgnal. Habisha Gudu eyweta nwe akim yalwe erasun yelwet yelelwe degimou EWENITUN YASTWELEW..

 5. NU NU 1 says:

  የፕሮሰር ጽሁፍ ብዙ አንብቢውለው የማጠተገብ የማይሰለች እና ጥልቅ የሆነ መልእክት ያለው ሊካድ የማይቻል ሃቅ ያለበት እውነት ነው ካዛ ባለፈ የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል ነው ነገሩ ፕሮፊሰር ከምር ካለማጋነነ አይ አበሻ ልመን ቁጥር 1 እና 2 ደግግሚ ከ 3 ግዚ በላይ አነበብኩት ያውም ሆዲን እያመመኝ ስስቅ ማለት ነው እነደውም ለብዙ ፈስ ቡክ ጓደኟቺ ላኩላችው በሂ ጽሁፍ ደስ ያላላቸውንም ወገኖች ጽሁፍ አንብቢያለው ያ ረራሱ መብት ነው አለመቀበል በዪ ለማለፍ ውጭ እውነታው ግን ፕሮፊሰር አስፍረውታል ቁጥር ሶስት እየጠበኩኝ ነው ከልቢ የውደድኩት ልናማር ልንለውጥ ይግባል ልመና ይብቃ እላለው

 6. wegderes says:

  thanks prof
  edmie ena tena yistwo

Comments are closed.