የቴዎድሮስ ካሳሁን  (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

መስፍን ወልደ-ማርያም

ሰኔ 2006 ዓ.ም

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር  የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣  ስሙ  እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤

ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው  «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣»  (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤  በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦

 1. ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
 2. ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
 3. ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
 4. ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣

ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።

ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣  አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ  እንኳን የሌላቸው ናቸው።

ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤  እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?

አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤  የጨለማዎቹም  ሰዎች እንደገና ተነሡ፤  ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም  ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤  አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች  በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።

የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።

በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤  የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

7 Responses to የቴዎድሮስ ካሳሁን  (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

 1. በለው ! says:

  “አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።! ” አንድን አዋቂ ነኝ ባይ ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣የሌላውን ባለሙያ ድካምና ጥረት ሥራውን ቢያንቋሽሽ ወይም ቢተች ወይም ግላዊ ሃሳቡን ቢሰጥ ባለሙያ አይባልም፣ ማንነቱንና ምንነቱን አስካፈረበት ድረስ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ጉዳዩ ከዚያው ከምቀኝነትና ከድንቁርና አያልፍም።
  **በአንድ ወቅት ቴዎድሮስ ካሳሁን የመንገድ ላይ ተዳዳሪ ወጣት ገጨ ተብሎ እሰከማሰርና ፍርድ ቤት አስከማንገላታት ከፍተኛ ዘመቻ ነበር። በዚህ ጉዳይ አንድ አስቂኝ ጉዳይ የነበረው የክሱ ጭብጥ ከመጠናበሩና ከማጥበርበሩ ማጭበርበሩ በዝቶ …አደጋ ደረሰ የተባለው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ሆኖ ተጎጂው ዳግማዊ ምንይልክ ሆስፒታል ስምንት ሰዓት ከአሥራ አምስት ደቂቃ ደርሷል።ለመሆኑ አንቡላንሱ ቴዎድሮስ ወጣቱን እንደሚገጨው አውቆ ቆሞ ይጠባበቅ ነበር? አንቡላንሱ ክንፍ አለው? ሌላው በዚያ ፍጥነት ግለሰቡ እንዴት መሐል አስፋልት ላይ ተገኘ? ወይ አስፋልቱ ላይ አንጥፎ ተኝቶ ነበር? ወይንም ሌላ ሰው ገድሎት መሐል ሜዳ አስቀምጦት ሄዷል? ግን ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ!
  **ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ሐጢያትና በሁሉም ሃይማኖቶች የተወገዘ ነው። የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ሌላው ነው፤ፖለቲካ ተንታኝ (በታኝ) የጭፍን ፖለቲካ መር! “ቦይ ኮት” የሚሉ ከእርዳታ ሰጪ ሀገራት ከአፍ በወደቀች ቃል ተወስውሰው እንዴት ጠግቦ በማይበላ፣ ሆዱ በአልቅት በተቆዘረ፣ የልጆቹ ፊት በዝንብ በተወረረ፣ ህዝብ ላይ አመፅ ብጥብጥ የአርስበእርስ የሜንጫ መጨፋጨፍን ለድሃው ሕዝብ እየሰበኩ ። እነሱ ሰላምና ምግብ በሞላበት ሀገር ተቀምጠው ሌት ተቀን የድሃውን ልጅ ጭዳ ሊሉ ሲለፋደዱ ይደመጣሉ።
  ***አሁንም እንደልማዳቸው ከኮካኮላ ኩባንያ ጋር ያለውን ውል ለማፋረስ ምላሳቸውን ሥለው ሜንጫቸውን አንግበው ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤ የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።

  >>>”የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?ሲሉ ሊቀ-ጠበብት መስፍን ወልደማርያም ተገርመዋል?
  ***እንግዲህ የዘርና የቋንቋ ክልል, አንደከብት በአንድ ቦታ መታጎር የሚፈጥረው ብዥታ, የማንነትና የምንነት መሳከር፣ እንደፋሲካ በግ የተገዛ፣ የተሸጠ፣በጥቅም የተለወጠ ለመሆኑ የማንና የየት ክልል ተንቀሳቃሽ ከብት መሆኑ በባንዲራና በብሔር በቀበሌ መታወቂያው በሚናገረው ቋንቋ እየተመረጠ ተቧድኖ የሚንቀሳቀስ ጠባብ አመለካካት የሚፈጥራቸው የትንሽነት ምልክት…የመጥፎ ሀገራት የተረሳና የዘቀጠ ፅንፈኝነትን ኩረጃ…ዘረኝነት…ኋላቀርነት ተደምረው ከሀገር ሉዓላዊነት ይልቅ የክልል ሉዓላዊነት ..ከሕዝብ ይልቅ ጠባብ ጎሰንነት..ከአንድnት ይልቅ መበታተን…ከተጨባጭ ታሪክ ይልቅ ወሬ…አሉባልታን ማናፈስ የሚፈጥራቸው ሽብር በደም ውስጥ የሰረፀ ብልሹ ሥነ-ምግባር በእርግጥ መንግስትና ህግ ቢኖር በወቅቱ ማረምም ከምንጩም ማድረቅ ይቻል ነበር። ሆኖም ያለው መንግስት የራሱን ሥልጣን ዘመን ለማራዘም ታላቁን ሀገር የማጥፋት ተልዕኮ ለማሳካት ተከታዮችን (የጨለማዎቹን ሰዎች) ለአመፅ፣ ትውልድ በማምከንና በማባከን ሥራ ላይ ለ፳፫ዓመት በሚገባ እየሰሩ ከዚህ መንግስት ልዩ ተጠቃሚ ሆነው የአዞ እንባ እያነቡ እንደ ቁራ እየጮሁ ተልዕኮአቸውን በጋራ አሳክተዋል ።አራት ነጥብ። እንግዲህ ሥለ ሀገር ሰላም፣ አንድንት፣ እኩልነት፣ ፍቅር፣ አብሮ መኖር፣ ጀግነት፣ ዳር ድንበርና ሰንደቅ፣ የሚናገርም የሚቆረቆርም አይኖርም! ትውልዱ ወኔውም ሞራሉና ማንነቱ ተሰልቦ በቁሙ የሞተ ሆኗል ወጣቱና ሴቶች ካልነቁ ሀገር በነበር ይቀራል። አዎን! ስለ ሰላም የሚሰብኩ ይከበሩ ዘፈንን ብቻ መውደድ ሳይሆን ለሞተ ደረት መድቃት ባነር መወጠርና በፀሀይ መነፅር ተከልሎ ከመወጠር ከዜጋም ጋር አብሮ መቆም ይልመድብንው! በቸር ይግጠመን

 2. Dear Pseudo Professor,
  I am not surprised to read such a stupid commentary from a pseudo professor like you…I think you haven’t changed a little, a bit towards respecting Oromo people. We Oromo people won’t retreat an inch to defend our right to self determination!! What a shame to hear when the so called ‘professor’ uses such ‘dirty words’ to refer to the Great Oromo people. Shame upon you!!

 3. Robel Ayalew says:

  የቴዲ ጥፋት እንደማንም ክክ ዘፋኞች ለስርዓቱና ለራሱ ጥቅም አለማሸርገዱ ነው….፡፡ I always stand with tedy

 4. Yehonal says:

  ክቡር professor: በበኩሌ Tewodros ጎበዝ musician መሆኑን ኣልክድም:: የ ስለ ፍቅርም ሆነ human right violation ተቃውሞ ሲዘፍን ወድለታለው:: በተረፈ ኣንድ ሃገር ውስጥ ሚዘፍን ሰው ሁሉንም ዜጋ ማክበር ያለበት ይመስለኛል:: እንኳን ብዙ ህዝብ ኣደለም a small group of people እንኳን ይሄ ሰው የኔ ጠላት ነው እያለው የራህ/ሽ ጉዳይ ብሎ ክርር ብሎ ደጋግሞ ስለዛ ሰው በሙዚቃ መጮህ በራሱ ወንጀል ባይሆንም smart way ኣይመስልም:: ልጁ ለህጻናት ክርክርና ንትርክ ከሚያስተምር ፥ የተቀየሙትን ሰወች ይቅርታ ጠይቆ ፍቅር ፍቅር የሚለውን ስብከቱን ቢቀጥል it makes sense. otherwise ዕሱ ራሱ እዚም እዛም ጠላት እያፈራና እርቅንም ሳይፈጽም ፍቅር ፍቅር ማለት fake personality ነው:: ለርሶ እጅግ ብዙ ኣክብሮት ኣለኝ። እየተፈጸመበት ነው ያሉት ተንኮልም ኣለ። ያው ሁሉም ሰው ላይ ሚደርስ ያለ ነው። መብቱ ያልተነካ ኢትዮጵያዊ ጥቂቱ ነው። መብቱ ቢሆንም እኔ ግን ነጻ ሃገር የሆነችውን Eritreaን ሁሌ ከሚያነሳብግኝ ስለ ኢትዮጵያዊያኑ Benishangul, Gambella, Somali እና Afar ትንሽ ቢዘፍን ደስ ይለኝ….እግዛቤር እድሜ ይስጦት።

 5. Salam Lee says:

  My dear friend,
  it is not because we don’t understand “love” that we reject Teddy. Oromos enjoyed many of the songs of Amharas and Amharas enjoyed Oromo song for centuries, Because Amhara songs by other artists showed us the beauty of Amhara culture. In Teddy’s you see the ugliness of Amhara. Imagine the dead kings he sings for are among other things are those who have been so bad to Amharas themselves are overthrown by Amharas as well!. So, this Amahars simply driven by emotion failed to realize how much they are cheated by Teddy. We have no reason to hate him otherwise.Tell us any other Amhara artist that a single Oromo hates. But since the time Teddy came on stage our division increased as he simply dug up the stinky stories. Regarding this senile professor I won’t be saying much. In an attempt to make his writing attractive he always makes annoying remarks, no saying the haters of Teddy have not yet evolved into humanity. He is more stupid than Teddy himself.

 6. dagmawi says:

  Teddy’s only crime is that he preaches LOVE and UNITY and the enemies of Love and Unity such as OLF and TPLF are working hard to demoralize him and so far they tried every thing to harm him cause OLF Oromos are bent on eliminating Amharas from the surface of the earth here Teddy sings about the unity of Amhara and Oromo people and that stands on their way of their future plan of creating a civil war between Oromo and AMHARA
  professor as you put it The pro unity Ethiopians especially Amhara elites do not want to do anything to individuals and artists and the killing and displacement of Amhara people therefore OLF extremists are getting the upper hand against any body who preaches for love and unity

  • Salam Lee says:

   My dear friend it is not because we hate love that we reject Teddy. Oromos enjoyed many of the songs of Amharas and Amharas enjoyed Oromo song for centuries, Because Amhara songs by other artists showed us the beauty of Amhara culture. In Teddy’s you see the ugliness of Amhara. Imagine the dead kings he songs for are among other things are those who are overthrown by Amharas as well!. So, this Amahars simply driven by emotion failed to realize how much they are cheated by Teddy. We have no reason to hate him otherwise.Tell us any other Amhara artist that a single Oromo hates. But since the time Teddy came on stage our division increased. Regarding this senile professor I won’t be saying much. In an attempt to make his writing attractive he always makes annoying remarks, no saying the haters of Teddy have not yet evolved into humanity. He is more stupid than Teddy himself.

Comments are closed.