የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2006

ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ዱሮ በልጅነታችን ጭራቅ የሚሉት ማስፈራሪያ ነበረ፤ በአለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት አማራ የሚባል ጭራቅ ማስፈራሪያ፣ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ቋት እንደሆነ ሲነገር ቆየ፤ መለስ ዜናዊም እየደጋገመ ‹አከርካሪቱን ሰብረን ሁለተኛ እንዳያንሰራራ› እናደርገዋለን እያለ እንደዛተ የተሰበረውን አከርካሪት ሳያይ ሞተ፤ በሕይወትም እያለ ቢሆን መለስ ዜናዊ አከርካሪቱን እሰብረዋለሁ የሚለውን አማራ የተባለ ስያሜ እንደሹመት ለነበረከት ስምዖንና ለነተፈራ ዋልዋ ይሰጥ ነበር፤ የክብር ጎሣ እንበለው! ራሱም ቢሆን ከዚህ የክብር ጎሣ ቤተሰብነት አልራቀም፤ አከርካሪቱ እንኳን ሊሰበር አልተገኘም!

ስንት ሺህ ሰዎች አማራ ናችሁ እየተባሉ ከስንት ስፍራ ተፈናቀሉ? አማራ ማለት እነዚሁ የተፈናቀሉት፣ በየጫካው የተገደሉትና የተሰደዱት ብቻ ናቸው? ሌሎችም ካሉ የጎሣ ዝምድና ሳይስባቸውና ከተፈናቀሉት ጋር አብሮ ለመቆም ለምን አልቻሉም? በጋምቤላ በደረገው ጭፍጨፋ የተጨፈጨፉት ጎሣዎች በጣም ትንሽም ቢሆኑ ከካናዳ እስከ አውስትራልያ ዓለምን ያዳራሱት የጎሣ ዝምድና ስሜት ለምን ለእነዚህ አማራ ለተባሉት ተፈናቃዮች አልሠራም? እንግዲህ አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉትና የሚሰቃዩት ዘመድና ደጋፊ የሌላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው፤ ሰውነታቸውም ቢሆን በሕግ ያልተረጋገጠላቸው፣ ሕግ የማይመክትላቸው ናቸው ማለት ነው፤ ይህንን ክርክር ከገፋንበት ዜግነታቸውንም የምንጠራጠርበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ደርግ በጎሣ ላይ የተመሠረተ የውትድርና ሥልጠና ያደረገ ይመስለኛልና በዚህ ጉዳይ ላይ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ በተለይም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ቀን የሚነግሩን ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።

አጥቂና ጨቋኝ ነፍጠኛ የሚባለው ሕዝብ ሲጠቃና ሲበደል ከኡኡታ በቀር ድምጹ የማይሰማው ትርጉሙ የህልውና ነው? ወይስ የወኔ? በሌላ አነጋገር አማራ የሚባል ጎሣ በእርግጥ አለ? ወይስ የለም? ከአለ የሚወራለትን ነፍጠኛነትና ወኔ ምን ዓይነት ብል በላው? ይህ ክርክር ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ጎሣ አለ ብለው የሞገቱኝን ሰዎች (የሞተውን መለስንና ያሉትን ጓደኞቹን ጭምር)፣ የመላው አማራ ይባል የነበረውን ድርጅት፣ ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት መሠረተ-አልባነት ለማሳየት እንጂ የሌለውንና ከዚህ በፊት ተቆስቁሶ ያልተነሣውን ጎሣ ለማነሣሣት አይደለም፤ የሌለ ነገር ቢቆሰቁሱት አይነሣም,

በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን፣ የሚገደሉትን፣ የሚሰቃዩትን ሁሉ ‹‹ሰዎች›› ብናደርጋቸውና ሰዎች ብንላቸውስ? ሰው መሆን የተፈጥሮ ነው፤ ልለውጥህ ቢሉት አይለወጥም፤ ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ ይሞታል፤ ሰው መሆናቸውን ወንጀል የማድረግ ዝንባሌ የሚኖረው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል።

ወይም አማራ የክርስቲያን ሃይማኖትን ተከታይነት የሚገልጽ ስያሜ አድርገን ብንወስደው የእነዚህ ሰዎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።

እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።

አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው ወደሚል መደምደሚያ በግድ መድረሳችን ነው፤ ያዋጣል ወይ?

ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

5 Responses to የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

 1. በለው ! says:

  ******የአማራ ጉዳይ አማራ አለ? ወይስ የለም? ብአዴን አማራ ነው?
  >>>በመለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት አባይ ፀሃየ፣ ከህወሃት፣ ህላዊ ዮሰፍ፣ ብአዴን ተብሎ ተወሰነ።የኢህዴን ጉባኤ ተጀመረ። ለአንድ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ከተወያዩ በኋላ በሁለተኛው ቀን ፩ኛ) የብአዴን አማራውን የሚወክል (አርማና ባንዲራ) ማጽደቅ፣ ፪ኛ) የብአዴን አመራር መምረጥ ሲሆን በአንደኝነት የተጠበቀው አልተዘጋጀም ተብሎ ለ፪ኛ ጉባኤው ሲተላለፍ፣ መረጣው ግን ቀጠለ። ከዚህ በታች የሚታየው ስም ዝርዝር የአማራ ህዝብ አመራር ናቸው። ከአማራው ህዝብ አብራክ የተወለዱት አማሮች እንደመሆናቸው አማራውን ይመሩታል በማለት በህወሓት የማጭበርበር ዘዴ መለስና አባይ እየተቀባበሉ ተናግረው ምርጫው ቀጠለ።(የግድ የዚያ ነገድ ባይሆኑም በአመለካከት ይወክሉት)ተጠፍጥፈው የተሰሩ!
  ተ.ቁ- ስም- ከነ አባት -የትውልድ ቦታ – ሃላፊነቱ
  1) ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ) -ከንባታ -የብአዴን ሊቀመንበር
  2) በረከት ስምኦን -ኤርትራ -ም/ሊቀመንበር
  3) አዲሱ ለገሰ -ሂርና-ሐረሪ(አደሬ)
  4) ተፈራ ዋለዋ -ሲዳማ -ፕሮፓጋንዳ ቢሮ
  5) ዮሴፍ ረታ -ኤርትራ
  6 መለሰ ጥላሁን- አማራ- ትግሬ
  7 ህላዊ ዮሴፍ -ኤርትራ -የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
  ተ.ቁ -ተለዋጭ -ማ/ኮሚቴ- ስም ከነአባት- የትውልድ ቦታ
  1 ታደሰ ካሳ -ትግራይ
  2 ሙሉአለም አበበ -አማራ
  እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በጉባኤው ተመረጡ። ኢህዴን የሚለው ስም ተለውጦ ብአዴን (ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ተብሎ ተሰየመ። የአማራ መሪ ድርጅት ሆነ። ቀደም ብለው የተነሱ ጥያቄዎች ብአዴን ማን ነው? ከየትስ መጡ? እነማንስ ናቸው? ወዘተ ለሚሉትጥያቄዎች መልሱ ይህ ነው። እውነተስ ብአዴን የአማራውን ሕዝብ ይወክላል? መልሱ ፈጽሞ አማራውን የሚወክል ድርጅት አይደለም ነው።
  **መስከረም 1982 እንደርታ አውራጃ ሰምረ ወረዳ ባኽላ ቁሽት ግዞተኛ የነበረው ብአዴን አመራሩ በሙሉ ተጠርተው መቀሌ ገቡ። የመጡበት ምክንያት ለስብሰባ መሆኑ ተነገራችው። ስብሰባው ሁሉም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አርከበ እቁባይ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገ/መድህን እና ጻድቃን ገ/ተንሳይ ሲሆኑ፤ በብአዴን በኩል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዌ ዮሴፍና ተደሰ ካሳ ናቸው። በዋናው አጀንዳ ከተነጋገሩ በኋላ በመጨረሻ ብአዴን የህወሓት አጋር ደርጅት መሆኑ ተገለጸላቸው። በዚህ መሰረትም ህወሓትና ብአዴን በመሆን ኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር) ተብለው እንደሚጠሩ ተወሰነ። የቀኑ ውሎ ሁኔታ እንደመግቢያ ተደርጎ “ድምፂ ወያነ” ልክ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ታወጀ፣ በጽሑም ተበተነ።አዲሱ ለገሰ በተወለደበት አካባቢ ይኖሩ የነበሩትን አማሮች በአሰቃቂ ግደያ አጥፍቷቸዋል። ከንብረታቸው አፈናቅሎ ለመከራና ችግር የዳረጋቸው የብአዴን መሪ ነው።መለሰ ጥላሁን ባደገበት የአማራው ቦታ በህወሓት የታጠቁ ሃይሎችን በመምራት በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈጸመ የብአዴን መሪ ነው። በረከት ስምኦን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚና መሪ ባደገበት ወሎ አካባቢ በሱ የሚመራው የህወሓት ታጣቂ ገዳዮች በመያዝ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ የፈጸመው የብአዴን መሪ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነው።የዚህ ወጀል ፈጻሚዎች ቅጥረኛ ባንዳዎች ኦህዴድ፣ ደህዴን በሌላ ቦታዎች፣ ራሱ ህወሓት በቀጥታ በመግባት ግድያ፣ ዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል ከግብረአበሮቹ ጋር ሆኖ እየፈጸመው ይገኛል። “የአማራ ሕዝብ ተነስ ስንለው ይነሳል፣ ተኛ ስንለው ይተኛል፣ አድርግ ስንለው ያደርጋል በማለት የተናገረው የአማራው ህዝብ ለ፳፫ ዓመታት እንደ ባርያ እየገዙት፣ መብቱ እየተረገጠ፣ እንዴት በእነዚህ የብአዴን ቅጥረኞች ዘሩ እየጠፋ፣ ከየቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ ሊኖር ነው? መልስ የሚሰጠው የነፃነት ግዴታው የሆነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። (አማራ አለ? ወይንስ የለም?) ህወሓት ለራሱ ትግል የተነሳው ኤርትራን አስገንጥሎ የትግራይ መንግሥት እናቋቁማለን ብሎ ነው ፕሮግራሙን አዘጋጅቶ የካቲት/1967 ደደቢት በረሃ የወረደው። በምን መልኩ ነው ደመኛ ጠላቴ ለሚለው አማራ ድርጅት ብአዴንን ሊፈጠርለት የቻለው? ህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው? ማንስ ሰጠው? ህወሓት ይህን ሁሉ የፈጠረው የአማራውን ህዝብ ከዘር ማንዘሩ ሊያጠፋልኝ ይችላል ብሎ ነው የብአዴንን ቅጥረኞች “mercenary” የፈጠረው። ሌላውም ህወሓት ለአማራ ድርጅት መፈጠር ቅንጣት የምታክል መብት ፈጽሞ የለውም። ስለዚህ ብአዴን ፀረ- አማራ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።
  (ክቡር ገብረመድክን አርዓያ ብአዴን ማነው? ከአውስትራሊያ ሚያዚያ 2006ዓ.ም ከፃፉት ተወሰደ)

 2. zeab says:

  መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።

 3. Kassa Hailu says:

  Dear Professor Mesfin –
  I can’t write enough to show the respect I have for you and your thoughts. In fact, the very set of ideas you have is behind the deep hatred TPLF and followers have towards you. The argument you are making about amara’s ‘non-existence’ is solid and [if I may say] has already been made by a few people before you – not necessarily explicitly. Readers and TPLF (+followers) find the argument thorny simply because it unsettles the very essence of their ethnocentric belief and politics. The discussion is revolving around the ‘amara’ people for apparent reasons; nonetheless, the argument is transferable and hence the politically motivated identities [be it oromo, tigre, gurage, wolaita/wolamo, kembata, agew, etc] do not exist. The difficulty of answering a very simple question like “what makes someone an oromo or gurage or tigre?” shall make it clear to this generation the hollowness of the political ideology prevailing in this poor country.
  I always believed that the whole concept of ethnic groups and/or ethnicity makes no sense and it is simply a political fabric entirely misconstrued and ill-designed. TPLF elites – like many others of that crazy generation – thought socialism was fool-proof and hardly made any effort to see what is in the details. They just copied and pasted (at the wrong place) the passage on the rights of nations and nationalities up to secession. Over the last 23 years, TPLF committed all kinds of atrocities on all Ethiopians and particularly Ethiopians they call ‘amara’ with the pre-text that the ‘amara’ ethnic group was the ‘colonial power’ over the last 100 years [TPLF’s age of Ethiopia]. The sad thing about it is that they don’t know how to define ‘amara’. I have talked to some people who call themselves ‘tigre’ and asked them about how they would identify someone as tigre. What I heard was a laughing stuff.
  Anyway, I have always enjoyed your arguments and it is a matter of time before Ethiopians understood the message you are trying to convey. Let me share with you an excerpt from an email I wrote to Yonas Belay Abebe (Tigray people: the revolutionaries and the bandits) just to show you how deeply your teachings have influenced me.

  “The point you have been making throughout the book is that what you call ‘Tigre’ is being misunderstood by others – particularly ‘Amaras’. The strong language you used to criticize Prof. Mesfin W/Mariam is an example. This is a common mistake people make when they have their own bias before they read what is written or listen to what is being said. Mesfin and many other Ethiopians are saying the very concept of nations and nationalities has always been misconstrued by TPLF and its cronies not necessarily to benefit what they and you call ‘Tigre’ rather to cling to power as long as possible. Apart from very few Ethiopians, people do know what is happening and what it means. I am from Harar – too far from Tigray I guess – but I know what is happening in this country [including Tigray]. So, the assumption that others do not know is fatal. Nonetheless, people who call themselves ‘Tigre’ for political reasons are benefiting because the political elite needs commodores. Mesfin and others are arguing that such people are making the best out of this rogue system and we [including ‘Tigre’] need to open our eyes and see the truth that ethnicity is not a biological concept rather a political concept meant only for egocentric reasons of people like Meles, Azeb, Bereket, Sibhat, Tewodros, Siye, etc.”

  Stay blessed –
  Kassa Hailu (PhD)

 4. gezahegn says:

  So what relevance this post has for those who are receiving all kinds of atrocities because of their ascribed identities.

Comments are closed.