የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል

መስፍን ወልደ ማርያም
ታኅሣሥ 2008

በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤–
አንድ፡– ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?
ሁለት፡– የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ?

አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤ ሁለተኛው ውጤት የልየነቱ በላቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፤ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡
አደጋው ወደሁለተኛው ጥያቄ ይመራናል፤ ገብቶኝ እነረደሆነ የግርግሩ ምክንያት ሁለት ናቸው፤ አንዱ ከቤት-ንብረት መፈናቀል ነው፤ የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ነው፤ ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች ሚደፈጥጡ ናቸው፤ ልብ በሉ የኦሮሞን የዜግነት መብቶች ይደፈጥጣል አላልኩም፤ የኢትዮጵያውያንን ሁሉ መሠረታዊ መብቶች የሚደፈጥጥ ነው፤ ይህ የማያጠራጥር እውነት ነው፤ ይህንን ከተቀበልን ጉዳዩ የኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ ግርግሩም የኦሮሞ ብቻ አይደለም፡፡
ትልቁ አደጋ ያሁንን ግርግር የኦሮምያ ብቻ ካደረግነው ወደፊት ያው ጉዳይ በሌሎች ጎሣዎች መሀከል ሊነሣ ነው፤ ሌሎች ግርግሮች ሊያስፈልጉ ነው፡፡
ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው፡፡

Advertisements
This entry was posted in አዲስ ጽሑፎች. Bookmark the permalink.

One Response to የሰሞኑ ‹‹የኦሮምያ ግርግር›› ግራ ገብቶኛል

 1. በለው ! says:

  አዎን! ግርግሩ ግራ ያጋባል….!?
  (ግርግር ለሥልጣን ያመቻል ግን ጭቆናን ለውጦ ጨቋኝን ያቀያይር እንደሆን እንጂ መፍትሔ አይሆንም።)
  (፩) – ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ?
  ** ሠልፈኛው ለብቻ!..ፖለቲካ ተንታኙ ለብቻ! ነፃ አውጭው ለብቻ!… ግራ የገባውና ያልገባው ለብቻ!..የገባውና መግቢያ የሚፈልገው ለብቻ! …ሳይገባው ግራ የሚያጋባው ለብቻ! መግለጫው(መላጫው) ለብቻ!ግራ ተጋብቶ የሚያግባበው ለብቻ! ማስፈራሪያና ዛቻ አዘል ፅሑፍ የሚለቀው ለብቻ! አንድንት ኅብርት አሁን በአስቸኳይ ዋ! በኋላ የሚሉና እንደ ኢህአዴግ አስበው እንደ ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኛ ተውነው ብሔራዊ አመፅ የተጠናበረባቸው…. በቋንቋና ብሔር ተኮር በመፈቃቀድና መፈቃቀር በደስታ ኖረው ከፌደራል መንግስት በጉርብትና እንኖራለን እንጂ በፌደራል ሥርዓት አንመራም የሚሉ!?(ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል?) በአትድረሱብንና በድረሱልን መካከል ያለው ውዥንብር፣ይህ በበኩሌ የራስን ድክመት በሌላው ለጥፎ መጯጯህ(የጨረባ ተስካር) በጭራሽ ሊታረምም ሊወገድም ያልቻለ የዓርባ ዓመት አዙሪት ነው።
  ** አንደኛው “የጋኔልና የሰይጣን የጥንቆላና መልክተኛ ሰልፍ” ሲል ሌላው “የቡዳ ፓለቲካ” ሲል ያደምቀዋል። ሕገመንግስቱ ይከበር ሲሉ ይጮሃሉ…ትነአግ/ኢህአዴግ እያስከበርኩ ነው ሲል ሌላው ተነስቶ ተከፋፈልን ተለያየን ይልና ያለቅሳል…ያላቅሳል፡ከተማ ሲስፋፋ ማንነታችን ይጠፋል ባሕልና ቋንቋችን ይበከላል ሲል ይፎክራል! ወዲያው ቋንቋችን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ይሁን ያለ ውድድር ምክር ቤቱም ፖለቲካል ኢኮኖሚውም እኛ ካልገባን ቃል የተገባልን ልዩ ጥቅማጥቅማችን ይከበር ይላል ። ‘ልዩነታችን ውበታችን’ ሲባል ሁሉም ይጨፍራል!! ቀጥሎ አንከፋፈልም አናሳ ብሔር በትልቅ ብሔር አይገዛም! ይላል…ይህ የእኛ ያም የእኛ! ‘ሐጎስን’ ንቀለው ‘ቶላን’ ትከለው ሲል ሌላው የእኔ ቱ ነው? የእነሱ የእኔ አደለምን ማለት ነው!? ሲል የተነሱበትን ንፋስ እረስተው ሌላ እሳት ጭረው ቀጠሉ… ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ‘ተከልሎና ተከልክሎ’ የመፈክሩ መልዕክት እንኳ ለጎረቤቱ ሳይገባው ሕፃናት ከፊት አሰልፎ ሕዝባዊ ንቅናቄ በፍልጥ እነጨትና ድንጋይ ወታደሩን መተነፋፋሻ አሳጣው አተረማመሰው!አርበደበደው!(ልክ ተስፋዬ ግበረእባብና ጀዋር ሙድ!)ነፃ አውጭው ምንሊክ ቤተመንግስት ሊቆጣጠር ፳ ኪሜ ቀረው! ታይቶም፣ ተሰምቶም፣ የማይታወቅ አብዮት (እራስን ማድነቅ! )እና መጃጃል። ታዲያማ እነ አጅሬዎችም (ሙስና መሮች፣አድርባዮች፣አውርቶአደሮች፣ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ቤተሰባዊ ደላሎች ስለ ሚ/ሩ ብለው መፈረም አቅም ያላቸው) ይችን ይዘው ጦራቸውን ጭነው ከተፍ አሉ የድሃ ልጅ በባዶ ሆዱ ኢላማ ሆነ ማን ተጠተቀመ?…. “ያልታደለች አፍሳ ለቀመች”
  …” ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሕዝብ አያገባውም ማለት ይሆናል፤ ሁለተኛው ውጤት የልዩነቱ ባለቤቶችና ተፋላሚዎች ኦሮሞዎችና ትነአግ/ ህወአት ብቻ ናቸው ማለት ነው፡ ይህ ትልቅ አደጋ አለበት፡፡(፩) ከቤት-ንብረት መፈናቀል(፪) የዜግነት መብትና መገለጫ የሆነውን መሬት ማጣት ሁለቱም መሰረታዊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነትን የዜግነት መብቶች የሚደፈጥጡ ናቸው።ግርግሩን የኦሮሞ ብቻ ማድርግ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከትነአግ/ኢህአዴግ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ጉዳዩ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሆነ ትግሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ መሆኑ ታምኖበት ቁርጠኛ ትግል! ቁርጠኛ ዓለማ! ቁርጠኛ ስልት! ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል።አራት ነጥብ።
  **” የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም ሲባል “ሲፈጀኝ በማንኪያ ሳይፈጀኝ በጄ” ዘላቂ ትግልና ዘላቂ አስተማማኝ ለውጥ ማግኘት በጭራሽ አይቻልም። በሁለቱም ጎራ “ልታስጠብብ ሄዳ አሰፍታ መጣች!” እንዳይሆን አደራ! አደራ! ስለ ሀገረ ኢትዮጵያ ሠላም የሚያስቡ ሠላም ይክረሙ!!

Comments are closed.